ኢትዮጵያ በጥንት ግሪካውያን አጠራር (ክፍል ሦስት) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, October 12, 2019

ኢትዮጵያ በጥንት ግሪካውያን አጠራር (ክፍል ሦስት)


. ኢትዮጵያ በጥንት ግሪካውያን አጠራር
  ጥንት ግሪኮች ፤አውሮፓውያን የስልጣኔ የመጀመሪያ ሕዝቦች ናቸው፡፡
  ከሁሉም በላይ በጥንታዊ ፍልስፍናቸው የሚታወቁት ግሪካውያን ግዛታቸውን በማስፋት በታላቁ እስክንድር ዘመነ መንግስት ሰሜን አፍሪካን ሳይቀር ተቆጣጥረዋል፡፡
  ግሪካውያን በታላቁ እስክንድር ስያሜ የወጣሌን የግብጽ ከተማ          (እስክንድርያን ) ማዕከል በማድረግ ሲኖሩ ከግብጻውያን ጋር የባህልና የንግድ ልውውጥ ከነበራቸው ሌሎች ጥንታውያን ሕዝቦች ጋር ለመተዋወቅ አጋጣሚው ተፈጥሮላቸዋል፡፡
  በዚህ ወቅት ግሪካውያን የአፍሪካውያንንአህጉር የሚያውቁት ስያሜዎች ነበር፡፡
  ይኸውም ከግብጽ በስተ ምዕራብ የሚገኘውን የአፍሪካ ሰሜናዊ ክፍል ሊቢያ በማለት ሲጠሩት ሁለተኛውን ደግሞ ከግብጽ በስተደቡብ አጠቃላይ የምስራቅ አፍሪካ ክፍል‹‹ኢትዮጵያ›› በማለት ያውቁት ነበር፡፡
  ‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውን ስያሜ በመጠቀም ጥንታውያን ግሪኮች የመጀመሪያዎች እንደሆኑ መረጃዎች ሲጠቁሙ ኢትዮጵያ የሚለው ቃልም በቀጥታ ከሁለት ግሪክኛ ቃላት ጥምር እንደሆነ ይታመናል፡፡
  እነዚህም ቃላት ‹‹አይቶ››ጥቁር ወይም ጠየም አደረገ‹‹ኦጵስ››ፊት የሚሉት ናቸው፡፡
  በጥቅሉ ኢትዮጵያ ማለት ለጥንት ግሪካውያን ፊታቸውን ፀሀይ ያቃጠለው ወይም ጠያይም መልክ ያላቸው ሰዎች አገር እንደ ማለት ነው፡፡
  ከዚህ በመነሳት  አገሪቱን ‹‹ኢትዮጵያ ያሰኘው የሕዝቡ ጠይምነት ነው የሚለውን አስተሳሰብ ብዙዎች ይደግፋሉ፡፡
  ‹‹ኢትዮጵያ››የሚለውን የአገራችን መጠሪያ ሁለት ታላላቅ የግሪክ ጸሀፊዎች በድርሰቶቻቸው ገልጸውታል፡፡እነርሱም ሄሮዱቶስና ሆሜር
  አገራችን ‹‹ኢትዮጵያ››ተብላ ለመሰየሟ ሌሎች ሁለት ትውፊታዊ ግምቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የካም ልጅ ኩሽ ‹‹ኢትዮጵስ›› በሚባል ሌላኛው ስሙ ይታወቅ ነበር፡፡
  ስለሆነም ‹‹ኢትዮጵስ›› በሚለው ስሙ የአገሪቱ አቅኝዎች አገሪቱን ‹‹ኢትዮጵያ›› በሚል ስያሜ መጥራት ጀመሩ የሚል ነው፡፡
  ሁለተኛው ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፈት ከነበሩት በርካታ ነገሥታት መካከል ‹‹ኢትዮጵስ›› የሚባል ንጉሥ ስለነበር አገራችንም የዛሬዋን ስያሜዋን ከዚህ ንጉስ በኢትዮጲስ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜን አግኝታለች
  . የጥንታዊት ኢትዮጵያ ሌሎች መጠሪያዎች
Ø ከጥንት ግብጻውያንና ግሪካውያን ስያሜዎች በተጨማሪ አገራችን በሌሎች መጠሪያዎቿም ትታወቅ ነበር፡፤ከነዚህም መካከል አቢሲኒያ፣የሳባ ምድር፣ብሔረ አግዓእያንና ምደረ ሐበሻ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
Ø የቤተ ክርስቲያን ትውፊትን መሰረት በማድረግ አንዳንድ ሊቃውንት እንደሚናገሩት ‹‹አቢሲኒያ‹‹እና ‹‹የሳባ ምደር››ተብለው የሚታወቁት የአገራችን ጥንታዊ መጠሪያዎች ‹‹አቢስ››እና ‹‹ሳባ›› ከሚባሉት ሁለቱ የኩሽ ልጆች የተወሰዱ ናቸው፡፡
Ø ኢትዮጵያን ያቀናው የካም ልጅ ኩሽ ‹‹አቢስ››እና ‹‹ሳባ›› የሚባሉ ልጆች ስለነበሩት የእነርሱን ስም በመውሰድ ኢትዮጵያ በአቢሲነያ በሳባ ደግሞ የሳባ ምድር ተብላ መጠራት ጀመረች ይባላል፡፡
Ø አስቀድሞ እንደተገለጠው በአባታቸው ‹‹ኩሽ›› ስም ደግሞ ኢትዮጵያ ‹‹የኩሽ ምድር ተብላም ትታወቅ››ነበር፡፡
Ø ብዙ የተለመደ ባይሆንም አገራችን ብሔረ አግዓዚያን ተብላ መጠራቷ ደቡብ አረቢያ ፈልሰው እንደመጡ በሚነገርላቸው ነገደ አግዓዝያን በተባሉ የሴም ዘሮች እንደሆነ ይነገራል፡፡
Ø አግዓዝያን ቋንቋቸው ጥንታዊ ‹‹ግዕዝ›› እንደነበር ሲነገር ‹‹አግዓዝያን››የሚለው ስምም የተሰጣቸው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው፡፡
Ø የመጀመሪያው እነዚህ የሴም ነገዶች  ወደ አገራችን ከመግባታቸው በፊት ብራሕማ የተባለ የህንድ ንጉሥ የኩሽ  ነገዶችን ድል በማድረግ ኢትዮጵያን በወረራ ይዞ ነበር፡፡
Ø በኋላ ግን እነዚህ  የሴም ነገዶች ኢትዮጵያን የወረረውን የሕንድ ንጉሥ ድል አድረገው አገሪቱን ነጻ አድርገዋታል የሚል ነው፡፡
Ø ከዚህ የተነሳ ነገዶችን ‹‹ነፃ አውጭዎች›› ለማለት በግዕዝ ቋንቋ ‹‹አግዓዝይን››የሚል ስያሜ ተሰጠቷቸዋል ይባላል፡፡ አገሪቱም(ኢትዮጵያ) ‹‹ብሔረ አግዓዝያን›› ተብላ መጠራት ጀመረች፣በግዕዝ ቋንቋ ‹‹አግዓዘ››ማለት ነጻ አወጣ ማት ነውና፡፡
Ø ሁለተኛው ምክንያት ‹‹ግዕዘ››የሚለው የግዕዝ ቃል ትርጉሙ ‹‹ተጓዘ››ማት ሲሆን በዚህ መሰረት እነዚህ ነገዶች ከደቡብ አረቢያ ተጉዘው ወደ ኢትዮያ መምጣታቸውን ለመግከለጽ ‹‹ተጉዘው መጡ›› በማለት ፈንታ ‹‹አግዓዝያን››ተብለዋል የሚል ነው፡፡
Ø ምደረ ሐበሻ የሚለው ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለጠው ዓረቦች የቀይ ዳማነት ማዕከል ያደረገው የተለያየ የኢትዮጵያ መልክ(ቀለም) በመውሰድ ድብልቅ ወይም ቅልቅል ለማለት የተጠቀሚበትን ‹‹ሐበሽ›› የሚለውን ቃል በመውሰድ ነው፡፡
Ø እንዲህ ነው ለመግለጽ የሚያስቸግረው የኢትዮጵያውያን የቆዳ ቀለም/መልከ ጠይምነት/ በካምና በሴም ዘሮች ሕብረ መልክእ ምክንያት ነው፡፡

ይቀጥላል……

Post Bottom Ad