ኢትዮጵያ በቅዱስ መጽሐፍ (ክፍል ሦስት) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Tuesday, October 22, 2019

ኢትዮጵያ በቅዱስ መጽሐፍ (ክፍል ሦስት)



     የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የክርስትና ሃይማኖት ታሪክ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን በታሪክ ምንጭነት መጠቀሙ የግድ ነው፡፡ቅዱስ መጽሐፍ በተደጋጋሚ ስማቸውን ከሚጠራቸው አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከ40 ጊዜ በላይ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡በተለይ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር የንግድ፣ የባህልና የሃይማኖት ግንኙነት እንደነበራት ከጥቅሶቹ መረዳት አያዳግትም፡፡ከእስራኤል ሌላ ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ የተጠቀሰችው በየዘመኑ ከነበሩት ታላላቅና ገናና መንግስታት ከግብጽ፣ከአሶር፣ባቢሎን፣ፂሮሽና የመሳሰሉት ጋር ነው፡፡ከዚህ ባሻገር በመጸሐፍ ቅዱስ ተደጋግማ የተወሳችው ይህች አገር የዛሬዋን ኢትዮያን እንደሆነ እንጅ ሱዳንን/ኑብያን/ እንዳልሆነ የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለአብነት በመውሰድ በትክክል መገንዘብ ይቻላል፡፡
ዘፍ 2፤13 ‹‹የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፡እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል፡፡››
ዘፍ12፡1 ‹‹ሙሴም ኢትዮጵያዊቷን አግብቷልና……በኢትዮጵዊቷም ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ››
መዝ 68፡31‹‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች››
መዝ 72፡9‹‹በፊቱ ኢትዮጵያውያን ይሰግዳሉ፡፡››
መዝ 74፡14‹‹ለኢትዮጵያ ሰዎች ምግባቸውን ሰጠሃቸው
ኤር13፡23‹‹በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን››ኢሳ 18፡1 ፣ኢሳ 43፡3፣ኢሳ 35፡14፣ኤር 38፡7-12፣አሞ 9፡7፣ሶፎ 3፡8 የሐዋ 8፡27-29
በአጠቃላይ በአፍሪካ የቅድመ ቅኝ ግዛት ታሪክ የየአገሮች የድንበር ወሰን ብዙም ትኩረት የማይሰጠው እንዳልነበርና የእገሌ ሀገር ድንበር ከዚህ እስከዚህ ተብሎ የሚወሰን እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡በጥንቱ ጊዜ የአንድ ሀገር ኃያልነትና በሌሎች ላይ የነበረው የበላይነት ብዙውን ጊዜ የሚታወቀው ግብር በማስገበር እንጅ ጠቅልሎ ድንበር ውስጥ በማስገባት እንዳልሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡
ስለሆነም የድንበር ጽንስ ሃሳብ ባልነበረበት ጥንታዊ ዘመን የኢትዮጵያ ወሰነ ክልል ከዚህ እስከዚህ ድረስ ነበር ብሎ በድፍረት ለመናገር አይቻልም፡፡ሆኖም ግን በጥንት ዘመን ከነበሩት ኃያላን መንግስታት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ስለነበረች አልፎ አልፎ ኑብያን (የዛሬዋን ሱዳንን አካባቢ)  እና ደቡብ ዓረቢያን እንዲያም ሲል እስከ ግብጽ ድረስ ግዛቷ እንደነበር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡እዚህ ላይ የአክሱም ዘመነ መንግስት ሁለት ታዋቂ ነገስታትን የሐውልት(የድንገይ) ላይ ጽሑፎች መመርመር በቂ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡እነዚህ ነገስታት በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ኢዛናና በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ካሌብ ናቸው፡፡የንጉስ ኢዛና የሐውልት ላይ ጽሑፍ በግእዝ፣በግሪክና በሳባ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን ኢዛና የአክሱም፣የሂሚያር፣ የረይደን፣የሐበሻ፣ የሰልሄን፣ የየመን፣ የቤጃ እና የካሱ ንጉሰ ነገስት መሆኑን ይገልጻል፡፡በድንጋይ ላይ የተጻፈው የዓፄ ካሌብ ስመ መንግስትም ተመሳሳይ መረጃ የያዘ ሲሆን ዐፄ ካሌብም የአክሱም፣የሂሚያር፣የረይደን፣የሰልሄን፣የየመን፣የትአም፣የቲሃምት፣የራባ፣የቤጃ፣ የኖባ እና የአራባት ንጉስ እንደነበር የሚገልጽ ነው፡፡በሁለቱም ነገስታት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች የተጠቀሱት ግዛቶች ከፊሎቹ በደቡብ ዓረቢያ ይገኙ የነበሩትን ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከአፍሪካ ቀንድ እስከ ግብጽ ድረስ ባለው ክልል እንደሚካተቱ ይታመናል፡፡
 የኢትዮጵያ እምነት በሕገ ልቡና ዘመን
ሕገ ልቡና ለሰው ከጥንተ ተፈጥሮው ከልዑል እግዚአብሔር የተሰጠው የመጀመሪያ ሕግ ነው፡፡ይህ ዘመን ከአዳም እስከ ሙሴ ያለውን አራት ሺ ዘመን ያጠቃልላል፡፡ ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና ዘመን ሀገረ እግዚአብሔር ነበረች፡፡ሌላው ዓለም /ከእስራኤላውያን በስተቀር/ በአምለኮተ ጣዖት በሚባዝኑበት ዘመን ኖኅና የልጅ ልጆቹ የአባታቸውን እምነት ወደ አትዮጵያ ይዘው በመግባታቸው አገራችን በአምልኮተ እግዚአብሔር ልትታዎቅ ችላለች፡፡ ከኖኅ ሦስት ልጆች መካካል ኢትዮጵያን ያቀናው ካም እንደነበር ትውፊታዊ መረጃዎች  ይጠቁማሉ፡፡
በሕገ ልቡና ኢትዮጵያ በአምልኮተ እግዘአብሔር እንደነበረች የሚያመለክቱ  ማስረጃዎች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች፤
Ø ሊቀ ነቢያት ሙሴ ኢትዮጵያዊቱን ማግባቱ ፡፡ዘፍ12 ይህም ሙሴ በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተመረጠ  ታላቅ ነቢይ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷን ያገባው በሕገ ልቡና በአምልኮተ እግዚአብሔር ስለምትመስለው ነው፡፡
Ø ንግስት ሳባ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ማድረጓ፡፡1ኛነገ10 ይህም ንግስት ሳባ ጠቢቡ ሰሎሞንን ባገኘቸው ጊዜ ‹‹ አንተን የወደደ፣የእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላከህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን…››› በማለት መናገሯ ኢትዮጵያ በአምልኮተ እግዚአብሔር የነበረች ሀገር ለመሆኗ ምስክር ነው፡፡
ለ/ ምዕራባውያን የታሪክ አባት ብለው የሚጠሩት ሄሮዶቶስ ‹‹ የኢትዮጵያ ሰዎች ርኅራሄቸው እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡በሰፊው ሜዳ ለመንገድ አላፊዎች ድግስ ይደግሳሉ፤ምንም በሆን መንገደኛ የሚበላውን አያጣም ፡፡ ክፉ ነገር በሀገራቸው የተጠላ ነው፡፡›› በማለት በድርሰቱ ላይ ጽፏል፡፡ይህም ኢትዮጵያውያን በወቅቱ በሕገ ልቡና እየተመሩ የአብርሃም አምላክ እንደሚምኑና አባታቸው አብርሃም የሚሰራውን በጎ ምግባር በተግባር ይፈጽሙ እንደ ነበር የሚያሳይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ እምነት በሕገ ኦሪት ዘመን
ትውፊትና መሰረት ያደረገው የኢትየጵያ ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ሂደት ንግስተ ሳባ ወደ እየሩሳሌም  ያደረገችው ጉዞ በአገራችን የብሉ ኪዳን እምነትና የሕገ ኦሪት ስርዓት እንዲገባ መሰረታዊ ምክንያት መሆኑን ያትታል፡፡ የንግስተ ሳባ ጉዞ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያው መጽሐፈ ነገስት የተመዘገበው ነው፡፡ሁኖም ግን በንግስተ ሳባ ማንነትና ታሪክ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በብዙዎች የሚነሱ ሁለት አዎዛጋቢ ጉዳዮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው አረቦችና ኢትዮጵያውያን ሁለቱም ንግስቷን የእኛ ናት የእኛ ናት በማለት የሚሰሙት ክርክር ነው፡፡ ሀለትኛው ደግሞ በስግስት ሳባና በንጉስ ሰሎሞን ጋር ታያይዞ በአገራችን ሚተረከው ነገር እውነት ወይስ ተረት (Legend)ነው የሚለው ነው፡፡
1) ንግስተ ሳባ ኢትዮጵያዊት ወይስ ዐረባዊት(የመናዊት)
መጽሐፍ ቅዱስ ንግስቷን ስም ሳይጠቅስ በደፈናው የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) በማለት ታሪካዊ የእየሩሳሌም ጉዞዋንና ከንጉስ ሰለሞን ጋር ደረገችውን ግንኙነት በዝርዝር ያትታል፡፡ ዐረቦች ድግሞ ከእስልምና በፊት በየመን አካባቢ (ደቡብ ዐረቢያ) ሳባ (sheba) የሚባል መንግስት እንደነበረ ስለሚነገር ንግስቷን የኛ ነች በማለት ይከራከራሉ፡፡ ሌሎች በርካታ ትውፊታዊ መረጃወች ደግሞ ንግስቷ የኢትዮጵያ ንግስት ሁና ሳለ ንግስተ ሳባ ተብላ በቅዱስ መጽሐፍ መጠቀሷ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሊሆን እንደሚችል ይመለከታሉ፡፡
የመጀመሪያዊ አስቀድሞ እንደተገለጸው በጥንት ጊዜ ኢትዮጵያ ‹‹የሳባ ምድር›› ተብላ ትጠራ እንደነበረ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ኢትዮጵያን ያቀኗት የኖህ የልጅልጅ የኩሽ ዘሮች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው ሳባ ደግሞ የኩሽ Yመጀመሪያ ልጁነው፡፡ ዘፍ17) ስለዚህ ኢትዮጵያ በአቅኝዋ በሳባ የሳባ ምድር ተብላ መጠራት ጀመረች፡፡
ሁለተኛው ከጌታችን ልደት በፊት አንድ ሺ አመተ አለም ገደማ ከደቡብ ዐረቢያ ፈልሰው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የሴም ዘሮች እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል፡፡ እነዚህ የሴም ዘሮችም ብዙዎቹ ሳባ ተብሎ ይጠራ ከነበረው የየመን ክፍል እንደመ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ምጻተኛ ሴማውያን ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ በአገሪቱ ቀድመው ከነበሩት የካም (የኩሽ) ዘሮች ጋር በመቀላቀል በባህል፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ህይወትና ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ለውጦች እንዲፈጠሩ አድርገዋል፡፡ የሳባን ቋንቋ ለኢትዮጵያ ያስተዋወቁትም እነሱ ናቸው፡፡ የሳባ ቋንቋ ከግእዝ በፊት ኢትዮጵያዊያን ይጠቀሙበት እንደነበረ እስከዛሬ ድረስ በአገራችን ከሚገኙ በርካታ የድንጋይ ላይ ጹሑፎች መረዳት ይቻላል፡፡ እንግዲህ ‹‹በእነዚህ ከሳባ(የመን) አካባቢ መጥተው በኢትዮጵያ ምድር በሰፈሩ ሴማውያንና በሳባ ቋንቋ ምክንያት ንግስቷን ንግስተ ሳባ ተብላ ልትጠራ ትችላለች›› የሚለው ሌላኛው አስታየት ነው፡፡
ሦስተኛው ታሪኩ በተፈጸመበት ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት በታም ሰፊ እስከ ደቡብ ዐረቢያ ድረስ ዘልቆ የየመን ግዛቶች ሳባንና ሌሎችን ያተቃልል ስለነበር ንግስቷን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግስተ ሳባ ብሎ የጠራት ሳባ የተባለው ቦታ ራሱ የኢትዮጵያ ግዛት ስለሆን ነው የሚል ነው፡፡ ለምሳሌ ንጉስ ኢዛና ክርስትና ከመቀበሉ በፊትም ሆነ በኋላ በሐውልቱ ላይ የጻፈው ጹሕፍ (Ezana & inscription) ከምንለው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡
<<Ezana …. King of Aksum and of Himary and of Raydan and of Saba and of Salhen and of Seyamo and of Bega and of kassu, king of king….>> ትርጉሙም የአክሱም ንጉስ፣ የሂምያር፣ የረይዳን፣ የሳባ፣ የሳልሄን፣ የሰያሞ፣ የቤጃ እና የካሱ ንጉሰ ነገስት የሚል ነው፡፡ ከነዙህ ቦታዎች (ግዛቶች) መካከል አንዳንዶቹ በደቡብ ዐረቢያ(የመን) አካባቢ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሳባም በደቡብ ዐረቢያ በንጉስ ኢዛና ስር ከነበሩ ግዛቶች ውስጥ አንዷ በመሆኗ ኢዛና ‹‹የሳባ ንጉስ›› (king of saba) ተብሎ እንደ ተገለጸ እንመለከታለን፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ንግስቷ ንግስተ ሳባ (Queen of sheba) ተብላ መጠራቷም ዐረባዊ ሁና ሳይሆን ያ አካባቢ ግዛቷ ስለነበረ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ በተጨማሪም ምንአልባት ንግስቷ የሰሎሞን ጥበብ ለመረዳት ከኢትዮጵያ ተነስታ በግዛቷ በሳባ በኩል አድርጋ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ ተጓዘች ንግስተ ሳባ ተብላ ለመታወቅ ችላ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅደስ የንግስቷን ስም ባይጠቅሰውም በኢትዮጵያውን ትውፊታዊ መረጃዎች (Traditional source) መሰረት ማክዳ በመባል ትታወቃለች፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ንግስተ አዜብ በማለት የጠራታል፡፡ ንግስተ አዜብ ማለትም የደቡብ ንግስት ማለት ነው፡፡ ‹‹ንግስተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ተፈርድበታለች፡፡ የሰሎሞን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና እንሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ፡፡›› (ማቴ 12፤42) ንግስተ ሳባ ኢትዮጵያዊት ንግስት ስለመሆኗ የሚያስረግጡ ማብራሪያዎች፡፡
       ሀ) የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እራሱ ዋነኛ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አካል ነው፡፡ የንግስተ ሳባ ታሪክ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በቀዳማዊ ነገስት በሚገባ ተግልጻል፡፡ (1ኛ ነገ10፤1-13)፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያትተው ንግስተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ወደ እየሩሳሌም ተጉዛ ከማየቷ በፊት አገሯ ላይ እያለች በዝና ታውቀውና ትሰማው እንደነበረ እንዲህ በማለት ገልጻል፡፡               ‹‹ንጉሱንም አለችው ስለነገርህና ስለጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው;; እኔም መጥቸ በአይኔ እስከማይ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር;;አሁንም ጥበብህና ስራህ ከሰማሁት ዝና ይበልጣል፡፡ (1ኛነገ.10፤1) በዚህ ንግግር ላይ ብዙ ቁምነገር መረዳት ይቻላል፡፡
ከእነዚህም መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ንግስቷ ኃያል እንደነበረችና በዚያ ዘመን በእርሷና በሰሎሞን ግዛት መካከል የተበቀ ግንኙነት እንደነበረ ይጠቁመናል፡፡ ይህ ታሪክ በተፈጸመበት ዘመን ከደቡብ ዐረቢያን መንግስታት ይልቅ ኢትዮጵያ ሰፊ ግዛትና የነበራትና ከኃያላን አገሮች መካከል አንዷ ሆና ከእስራኤልም ጋር በንግድ ፣ በባህልና በሐይማኖት የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራት መጽሐፍ ቅዱስና ጥናታውያን መዛግብት ያረጋግጣሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በንግግሯ ከእስራኤል ጋር ግልጽ የሆነ የሐይማኖት አንድነት መኖሩን ያሳያል፡፡ ለምሳሌ ‹‹የሳባም ንግስት በእግዚአብሐየር ስም የወጣላትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች፡፡›› 1ኛ ነገ.10፤1
‹‹አንትን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመተ አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘላለም ወዶታልና፤ ስለዚህ ጽድቅና ፍርድን ታደርግ ዘንድ ንጉስ አድርጎ አስነሳህ፡፡›› 1ኛነገ.10፤2 ጌታችንም በሀዲስ ኪዳና ‹‹ንግስተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትፈርድበታለች›› (ማቴ 12፤42)ብሎ የተናገረው የንግስቷን እምነትና ማንነት ለመግለጽ ጭምር ነው፡፡ በሌላ በኩል ንግስተ ሳባ የሰለሞንን ጥበብ ለማየት ወደ እስራኤል ስትጓዝ ለጥበበኛው ንጉስ ካበረከተቻቸው ስጦታዎች መካከል ሽቶ፣ ወርቅ፣ የከበረ እንቁ፣ ተንከራ ዘኢትዮጵያ የሚባል የሽቶ አይነት የሰንደል እንጨትና የመሳሰሉት ከደቡብ ዐረቢያ ይልቅ በብዛት በኢትዮጵያ እንደሚገኝ በርካታ ጠቋሚ ነገሪች አሉ፡፡
ለ) ክብረ ነገስት፡- ንግስተ ሳባ በአገሯ ‹‹ማክዳ›› ትባላ እንደምትታወቅ ኢትዮጵያዊት ንግስት ሁና የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ እየሩሳሌም እንደተጓዘችና ከዚያም በኋላ ያለውን በንጉስ ሰሎሞንና በንግስተ ሳባ መካከል የነበረውን ግንኙነትና የግንኙነቱን ፍሬ በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ወደ እየሩሳሌም ከመጓዟ በፊት ስለ ጥበበኛው ዝና ይነግራት የነበር ታምሪን/ ዘምሪን/ የተባለ ነጋዴ ነበር፡፡ ያኔ ንጉስ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ ለመስራት በዝግጅት ላይ ስለነበር ለቤተመቅደሱ ማሰሪያም ብርቅና ድንቅ ዕቃዎችን የቀርቡለት ከነበሩት ነጋዴዎች ምካከል ኢትዮጵያዊ ታምሪን እንደነበር ክበረ ነገስት ይገልጻል፡፡
ሐ) ትውፌታዊ የጥንት ጥናት መካናት (Archaeological sites) በአገራችን መገኘታቸው
ከንግስተ ሳባ ማንነት ጋር ተያይዞ እስከ አሁን ድረስ በደቡብ ዐረበቢያ በአርኪኦሎጅ ጥናት ምንመ ዓይነት ፍንጭ እንዳልተገኘ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ከንግስተ ሳባ ጋር የተያያዘ በርካታ ተውፊታዊ የጥንት ጥናት መካናት በአገራችን ተገኝተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የንግስተ ሳባ ቤተ መንግስት፣ የንግስተ ሳባ መቃብር፣ የንግስተ ሳባ መታጠቢያ ገንዳና የመሳሰሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
ንግስተ ሳባ ወደ ሰሎሞን የደረገቸው ጉዞ ያበረከተው አስተዋጽኦ
የተጓዘችባቸው ዋናዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
Ø በወሬ ትሰማውና በዝና ታውቀው የነበረውን የንጉስ ሰሎሞንን ጥበብ በዐይኗ አይታ ለማረጋገጥ፡፡
Ø ንጉስ ሰሎሞንን በእንቆቅልሽና በምሳሌ ለመፈተን
Ø ለጥበበኛው ብርቅና ድንቅ ስጦታዎችን ለማቅረብ፣
Ø በእርሷና በንጉስ ሰሎሞን መንግስት መካከል የነበረውን ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ ነበር፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ ማነው?
የንግስተ ሳባና የንጉስ ሰሎሞን ታሪካዊ ግንኙነት ለቀዳማዊ ምኒልክ መገኘት ምክንያት እንደሆነ ይገለጣል፡፡ንግስተ ሳባ ከንጉስ ሶሎሞን ምኒልክን ጸንሳ ወደ ሀገሯ እንደተመለሰች ጻሪክ ያስረዳል፡፡በክበረ ነገስትም ‹‹ቦይነ ለሐኪም››ተብሎ ተገልጧል››በእብራይስጥ‹‹ቦን ሀሐካም››በዓረቦች‹‹አብንኤል ሐኪም››የሚል ስየሜ ሲኖርው ፍችውም በሁሉም ዘንድ ‹‹የጠቢብ ልጅ››እንደ ማለት ነው ግእዝ፣ዕብራይስጥ እና ዐረብኛ የሴም ቋንቋ ክፍል ስለሆኑ በመካከል ተመሳሳይነት እነዳላቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ትርጓሜ ምኒልክ የሚለውን ይተካል፡፡ትውፊቶች እንደሚመለክቱት በግዕዝ ‹‹መኑ ይልህቅ››ከሚለው ተወሰደ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ትርጓሜውም እንደርሱ  ትልቅ ማን አለ ማለት ነው፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ በሀገሩ(ኢትዮጵያ)ተወለዶ ካደገ በኋላ አባቱን ለመተዋወቅ ወደ እስራኤል ሄዷል፡፡ንጉሥ ሶሎሞንም ልጁ ሮብኣም ገና ስድስት ዓመቱ ስለነበር ምኒልክን አልጋ ወራሹ ሊያደርገው ቢያስብም ምኒልክ ወደ አገሩ መመለስ ስለወደደ ፈቃደኛ አልሆነለትም ንጉሱም በካህኑ ሳዶቅ ቅብዓተ ንግሥ አስፈጽሞለት ከበኩር እስራኤላውያን ልጆች ጋር ወደ አገሩ ላከው፡፡ካህናቱም ጥላተ ሙሴን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ኢትዮጵያም በእግዚአብሔር ፈቃድ የታቦተ ጽዮን መንበር ሆናለች፡፡
ኢተዮጵያ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ባለቤት ሆና ሥርዓተ ኦሪት በአገራችን መፈጸም የተጀመረው ከዚህ ጊዜ በኋላ እንደሀነ ይታመናል፡፡ምኒልክ ከተመለሰ በኋላ ንግስናን ከእናቱ ተቀበሎ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀምሯል፡፡ የብለይ ኪዳንነሰ የኦሪት ስርአት እንዲፈጸም አድርጓል፡፡ለብዙ ዘመናት እስከ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ድረስ የኢተዮጵያ ነገሥታት መንግስታቸውን ከእስራኤል ‹‹ከሶሎሞን ሥርወ መንግስት›› ጋር ለማገናኘት የሞከሩት በቀዳማዊ ምኒልክ መነሻነት ነው፡፡
ቀዳመዊ ምኒልክ ‹‹ለሶሎሞናዊው››ሥርወ መንግስት በትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ቢባልም ለአክሱም ለአክሱም መንግስት ግን የመጀመሪያ ነውንጉሥ ሊባል አይችልም፡፡ምንያቱም ቀዳማዊ ምኒልክ በኢትዮጵያ እንደነገሰ የሚነገረው ከጌታ ልደት በፊት በአስረኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ ሲሆን አክሱም ለኢትዮጵያ መንግስት ማዕከል መሆን የጀመረች ው ከጌታ ልደት በፊት አጋማሽ መኆኑን መረጃች ይጠቁማሉ፡፡አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸውም የኢትዮጵያ  መንግስትና ቤተክርስቲያን ታሪክ በአክሱም ዘመነ መንግስት የተጀመረ ሳይሆን ከዛ በፊት አያሌ ዘመናት  ያስቆጠረ መሆኑን እገነዘባለን፡፡ አገራችን ከ3000 ዓመታት በላይ ታሪክ እንዳላት የሚነገረውም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ነው፡፡እርግጥ ኢትዮጵያ በማናቸውም ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰችበት ጊዜና በቂ የሆነ የታሪክ መረጃዎችን ጥሎ ያለፈ ዘመን በመሆኑ የአክሱም መንግስትና ሥልጣኔ በአገራችን ታሪክ ጎልቶ የሚነገር ነው፡፡
የታቦተ ጽዮኝ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እንደሚወዳት በመጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ክፍሎች የጠገለጠ ቢሆንም ከሁሉም በላይ በልዩ ጥበቡ የታቦተ ጽዮን ባለቤት ሲያደርጋትበተግባር ተረጋግጧል፡፡ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት እንደሆነ ተደጋግሞ በቅዱስ መጽሐፍ ተገልጧል፡፡ዘጸ25፡22 የዚሁ ሀብት ባለቤት በመሆናችን መቸም ቢሆን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እነደሆነ ኢትዮጵያውያን እናውቃለን፡፡ታቦተ ጽዮን በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእስራኤል ዘሥጋ ብዙ ገቢረ ታምራትን አድርጋለች፡፡1ኛ ሳሙ 4፡6
ስለ ታቦተ ጽዮን በብሉ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ እስከ ንጉሥ ሶሎሞን ዘመነ መንግስት ድረስ ከ 200 ጊዜ በላይ የተጠቀሰ ሲሆን ከንጉሥ ሶሎመን በኋላ ግን የታቦተ ጽዮን ታሪክ አንድ ጊዜም አልተወሳም፡፡እስራኤላውያ ከባቢሎን ምረኮ በኋላም ወደ አገራቸው ሲመለሱ ዘሩባቤል ባሳነጸው ቤተ መቅደስ ታቦት አልነበረም፡፡ስለሆነም አንዳንድ ጸሓፊዎች ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ሲያፈርስ ተቦተ ጽዮን ያን ጊዜ እንደ ጠፋች ይገለጣሉ፡፡በዚህ ምክንያት የታቦተ ጽዮኝ የመሰወር ጉዳይ ለሌላው ዓከም እንቆቅልሽ ሆኖ ለዘመናት ኖሯል፡፡ታቦተ ጽዮን ግን ከእስራኤል ከተሰወረች ጀምሮ የነበረችው በኢትዮጵያውን ቤተ መቅደስ ነው፡፡ታቦተ ጽዮኝ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችውም እስቀድሞ እንደተገለጠው ከንግሥተ ሳባ የኢየሩሳለም ጉብኝት በኋላ በቀዳ ማ ምኒልክ አማካኝነት መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህች ታቦተ ጽዮን አሁን የምትገኘውም በአክሱም በራሷ በተለየ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ዙሪያዋም በአጥር  የተከለለ ሲሆን የሚጠብቃትም በድንግልና የመነኮሰ መላ እድሜውን ለዚህ አገልግሎት የሚያውል አባት ነው፡፡ጽላቷ የምትገኝበት የተለየ ቦታ ባለ አንድ ፎቅ ሲሆን ምድር ቤቱም ብርቅና ድንቅ የሆነ ልዩ ልዩ ቅረሶች የተቀመጡበት ነው፡፡
የብሉይ ኪዳን እምነት እና ሥርዓት በኢትዮጵያ
ከክርስቶስ ልደት በፊት በብሉይ ኪዳን እምነት ከእስራል ቀጥሎ ሕገ ኦሪትን በመቀበል ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሀገር ነች፡፡በንጉሥ ሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ አማካይነት ከታቦተ ጽዮኝ ጋር ብዙ እስራኤላውያን፣የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት፣ሌዋውያን ካህናት ----ወዘተ ወደ እንደመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
 ሀ)የብሉይ ኪዳንና የኦሪት ሕግ በኢትዮጵያ እንደነበር የሚገልጹ መረጃዎች
1ኛ የጣቦተ ጽዮን መኖርና አከባበሩ
ታቦት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለምህረት በሚገለጥበት ጊዜ ዙፋኑ ነው ዘፍ 13፤21፡፡የታቦት መኖርና የአከባበር ሥርዓቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ትልቁ የእምነቷና የሥርአቷ ምንጭ ነው፡፡የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን የታቦት ባለቤት መሆኗ ብቻ ሳይሆን በጥምቀት በሌሎች በዓላት ንግሥ ጊዜ የሚታየው ታቦታትን ተሸክሞ በሆታ፣በመዝሙር፣በዕልልታወዘተ መጓዝና አጠቃላይ አከባበሩ የብሉይ ኪዳን እምነት ባለቤት እንደነበረች የሚገለጥ ነው፡፡
2ኛ ቀደሚት ሰንበትን ማክበር
ቀዳሚት ሰንበትን ማክበር በሕገ ኦሪት የተሰጠ አምላካዊ ትእዛዝ ነው ዘጸ20፤8፡፡የቀዳሚት ሰንበት መከበር ከአስርቱ ቃላተ ኦሪት ጋር አንድ ሆኖ የታዘዘ የብሉይ ኪዳን ትእዛዝ ነው፡፡የቀዳሚት ሰንበት መከበር የብሉይ ኪዳን እምነት በኢትዮጵያ ስለመኖሩ አንዱ ማስረጃ ነው፡፡
3ኛ ልብሰ ተክሕኖ(የካህናት)
የኢትዮጵያ ካህናት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ሲፈጽሙ የሚለብሱት ልብስ በአሰራሩም ሆነ በሚቀመጥበት ቦታ የተለየ የመንፈሳዊ አገልግሎት ልብስ ነው፡፡ሕዝ 44፤17-19፣ዘጸ 18፡፡መሰረቱም የኦሪት ሌዋውያን ስለሆነና መላ ሥርዓቱም ከጥንቱ ጋር ስለሚመሳሰል ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን ባለቤት የሚገልጥ ማስረጃ ነው፡፡
4ኛ እንግዳ መቀበል
እንግዳ መቀበል እስራኤላውያን ያዘወትሩት የነበረ መንፈሳዊ ተግባር ነው፡፡ኢትዮጵያም ከዓለም ካሳወቋት ዐበይት ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡አብርሃም ሦሥቱን እነግዶች ሲቀበል ሎጥ ሁለቱን መላይክትን ሲያስተናግድ የጠጠቀሙባቸው ቃላት ሳይቀር እስከዛሬ ድረስ በአገራችን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
አብርሃም ‹‹ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁ፣እግራችሁን ታጠቡ፣ቁራሽእንጀራ ላምጣለችሁ---››ሎጥም ‹‹ጌቶች ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፣ከዚያም እደሩ፣እግራችሁንም ተጠቡ፣ነገ ማልዳቸሁ ንገችሁን ትሔዳላችሁ ዘፍ 19
በእብራውያን ሲዘወተር የነበረው እንግዳ መቀበልነኢትዮጵያም የተለመደ ተግባር መሆኑኢትዮጵያ በብሉይ ኪዳን እምነት ሥርዓት የነበራትን ሱታፌ የሚገልጽ ነው፡፡
5ኛ ግዝረት
ግዝረት ለአብርሃም የጠሰጠው የቃል ኪዳን ምልክት ነው ዘፍ 17፤9ኢትዮጵያም የብሉይ ኪዳን ባለቤት ስለነበረች ልጆቿን በስምንተኛው ቀን ማስገረዝ የተለመደ ተግባሯ አድርጋዋለች፡፡ይህም ኢትዮጵያ በቅድመ ክርስትና የነበራትን ሥርዓተ እምነት የሚያመለክት ነው፡፡
6ኛ የሚበሉና የማይበሉ እንስሳትን መለየት
በኦሪት ዘዳግም 14፤3-21 እና ዘሌዋውያን 11፤47 በተጠቀሰው መሰርት ኢትዮጵያውያን ሰኮናው የጠሰነጠቀና ያልተሰነጠቀ፣የሚያመሰኳና የማያመሰኳ ወዘተ እያሉ የሚበሉትና የማይበሉትን መለየታቸው በቅዱስ መጽሐፍ በተገለጠው የዕብራውያን ልማድ መሰረት ነው፡
ለ) የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን አስመልክተው የተገለጡት በርካታ ጥቅሶች ኢትዮጵያ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበራትን ጠንካራ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚያረዱ ናቸው፡፡ለምሳሌ
አሞጽ 9፤7 ‹‹እናንተ እስራኤላውያን ለኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁም››
መዝ 87፤34፣‹‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች››
 ስኢሳ 48፤14 ‹‹ግብጽን ላንተ ቤዛ አድረጌ ኢትዮጵያን ላንተ ፋታ ሰጥቸሃለሁ››
የሐዋሥ 8፤27
ሐ) መሥዋተ ኦሪት በአገራችን ይሰዋ እንደነበር የሚያሳዩ ምልክቶች በአንዳንድ ቅዱሳት መካናት መገኘታቸው ነው፡፡እነዚህም መርጡለ ማርያም፣አክሱም ጽዮን፣ተድባበ ማርያም፣ጆመዳ ማርያም፣ብርብር ማርያም፣ኢየላ ሚካኤል እና ጣና ቂርቆስ ናቸው፡፡
መ)በግዕዝና በአማርኛ ቋንቋ ቀጥታ ከእብራይስጥ የተወረሱ በርካታ ቃላት መገኘታቸው፤ለምሳሌ ጣኦት፣ገሃነም፣መሥዋት፣ቤት ወዘተ የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ምዕራፍ ሦስት
ክርስትና በጥንታዊት ኢትዮጵያ
የክርስትና ሃይማኖት ወደ  ኢትዮጵያ መግባት
ኢትዮጵያ ለክርስትና ሀይማኖት ዜና ለአፍሪካ የመጀመሪያዋ ናት፡፡የክርስትና ሀይማኖት በፍጥነት ወደ ሀገራችን እንዲገባ አስተዋጽኦ ያደረጉ በርካታ ያደረጉ ነገሮች ሲኖሩ ዋናዋነዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1)የብሉይ ኪዳን እምነት፣ሥርዓትና ትንቢት ቀድሞ በሀገራችን መፈጸሙ
ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን እምነትና ሥርዓት ባለቤት ስለነበረች የክርስትና ሀይማኖት ለመቀበል አልተቸገረችም፡፡የዓለም መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወለድ በትንቢት ታውቀውና ትጠብቀው ስለነበር ክርስናውን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደባትም፡፡የመወለዱን ዜማ በሰማች ጊዜ ወርቅ፣ዕጣንና ከርቤ ጊዜ ከሰብዓ ሰገል ጋር በኮከብ መሪነት ቤተልሔም ተጉዛ ከስግደት ጋር እጅ መናሻ ማቅረን ይነገራል፡፡በብሉይ ኪዳን ትምህርት የለሰለሰውና የተዘጋጀው የኢትዮጵያውያን ልብ የሐዲስ ኪዳን ዘር በአጭር ጊዜ ውስጥ አብቅሎ አመርቂ የክርስትና ፍሬ ተገኝቶበታል፡፡
2)ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የነበራት የጠበቀ ግንኙነት
ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የነበራት ግንኙነት ክርስትና በምድረ እስራኤል ሲብት በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት የክርስትናው ዜና በሀገራችን በቶሎ እንዲዳረስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ክርስትና ወደ አትዮጵያ የገባው በንግሥት ህንደኬ ጃንደረባ አማካኝነት በ34 ዓመት ዐም ነው ብንልም ከዚያ በፊት ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር በነበራት የጠበቀ ግንኙነት ጌታችን በተወለደ ሰሞን ከዛ አካባቢ በሚመጡ ሰዎች ምክንያት የክርስትናው ወሬ በአገራችን ተዳርሶ ነበር፡፡ጌታችን በተወለደ ዘመን የነበረው ነጉሥ ባዚን በመባል ይታወቃል፡፡
3)የንግሥት ህንደኬ ጃንደረባ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም
ጃንደረባው የፋሲካ በዓልን አክብሮ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ የነብዩ ኢሳይያስን የትንቢት መጽሐፍ ሲያነብ(ኢሳ53) እግዚአብሔር ቅዱስ ፊልጶስን ልኮለት የክርስትናን ትምሕርት ከተረዳና ከተጠመቀ በኋላወደ አገሩ ተመልሷል፡፡ይህ የኝግስት ህንደኬ ባለሟል ያደረገው አስተዋጽኦ ታላቅ ስለነበር የክርስትና ሀይማኖት ወደ አገራችን የገባው ከጌታ ልደት በኋላ በ34 ዓም ቅዱስ ፊሊጶስ ባጠመቀው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ መሆኑን እንረዳለን፡፡
3)የንግሥት ህንደኬ ጃንደረባ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም
ጃንደረባው የፋሲካ በዓልን አክብሮ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ የነብዩ ኢሳይያስን የትንቢት መጽሐፍ ሲያነብ(ኢሳ53) እግዚአብሔር ቅዱስ ፊልጶስን ልኮለት የክርስትናን ትምሕርት ከተረዳና ከተጠመቀ በኋላወደ አገሩ ተመልሷል፡፡ይህ የኝግስት ህንደኬ ባለሟል ያደረገው አስተዋጽኦ ታላቅ ስለነበር የክርስትና ሀይማኖት ወደ አገራችን የገባው ከጌታ ልደት በኋላ በ34 ዓም ቅዱስ ፊሊጶስ ባጠመቀው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ መሆኑን እንረዳለን፡፡
4)ኢየሩሰሌም ተገኝተው በዓለ ኀምሳን ያከበሩ ኢትዮጵያውያን
በዓለ ኀምሳን ለማክበር ከተለያየአካባቢ ተሰብስበው በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ያመኑ ሦስት ሺህ ምዕመናን፡፡(የሐዋ 2)ከነዚህም መካከልኢትዮጵያውያን ስለነበሩከበዓሉ በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰው የክርስትና እምነት እንዲታወቅ በማድረግ በኩል የበኩላቸው አስተዋጽኦ እንደነበር ይታመናል፡፡ኢትዮጵያውን በባዓሉ እንደነበሩም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በባዓለ ኀምሳ ድርሳኑ‹‹ቅዱሳነ  ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በተቀበሉበት ወቅት ኢትዮጵያውያንምተገኝተው ነበርብሏል፡፡
5)የሐዋወያት አስተዋጽኦ 
የታወቁት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ሩፊኖስና ሶቅራጥስ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌል እንደሰበከ ጽፈዋል፡፡አባ ጀሮም ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ    እንዳስተማረ ሲገልጽ የሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ቅዱስ ቶማስ እንዳስተማረ ጽፏል፡፡
6)ክርስተና አስቀድሞ በነገሥታቱ አካባቢ ተቀባይነት ማግኘቱ                                                                                                                                                                                                                                                                                 







Post Bottom Ad