ግዕዝ ቋንቋን እንማር (ክፍል አንድ) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Tuesday, October 22, 2019

ግዕዝ ቋንቋን እንማር (ክፍል አንድ)


የልሣነ ግዕዝ ተማሪዎች ለሌሎችም #Share አድርጋችሁ አድርሱልኝ አሁን በመጀመሪያው ቀለል ያሉ ቃላትን እንማርና ከዛ ከበድ ወደ ሚለው ልሣነ ግዕዝ አርዕስት እንገባለን ስለዚህ ዛሬ የ"ሀ"ን ነጠላ ግስ ዘርና ነባር/Dictionary የሚያሳየውን የ"ሀ"ነጠላ ግስ እንመለከታለን!!!
መልካም ጥናት!!!
ግዕዝ - ትርጉም
ሎሀ - ጻፈ
መርሐ - መራ
ሰርሐ - አቀና፡አከናወነ
ሰብሐ - አመሠገነ
ሰብሐ - ሰባ
በዝሐ - በዛ
ጸንሐ - ቆየ፡ አበደ
ጼሐ - ጠረገ
ፈልሐ - ፈላ
ፈርሐ - ፈራ
ፈትሐ - ፈረደ
በጽሐ - ደረሰ
ተግሀ - ተጋ
ተፈስሀ - ደስ አለው
ነስሀ - ተመለሰ
ነቅሐ - ነቃ ፡ ነዳ
ነብሐ/ከልሐ - ጮኸ
ነግሀ/ጎሀ - ነጋ
ነጽሐ - ንጹሕ ሆነ
ኖኀ - ረዘመ
ለብሐ/ጠብሐ - አረደ
ጸርኸ - ጮኸ
ናሁ - አሁን
በሊህ - ስለት
አምኀ - እጅ ነሳ
ብዙሕ - ብዙ
ወርሀ - ጨረቃ/ብርሃን
አንቆቅኆ - እንቁላል
ኦሆ - እሽ/በጀ

Post Bottom Ad