ምዕራፍ ሁለት
2. ኢትዮጵያ እና እምነቷ በቅድመ ክርስትና
2.1. የዛሬዋ ኢትዮጵያ በጥንቱ ዘመን አጠራር
፩. ኢትዮጵያ በጥንት ግብጻውያን አጠራር
Ø የጥንት ግብጻውያን በአፍሪካ የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ ሕዝቦች ናቸው፡፡
Ø ለሥልጣኔያቸው የዓባይን ወንዝ መሰረት የደረጉት እነዚህ ሕዝቦች ፈርዖኖች በመባል በሚታወቁ ገዠዎቻቸው፣በፒራሚዶቻቸውና ሄሮግላፊክስ በሚባለው የአጻጻፍ ስልታቸው በዓለማችን የጥንት ታሪክ በሚገባ ይታወቃሉ፡፡
Ø የጥንቶቹ ግብጻውያን ‹‹ኢትዮጵያ››የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በተለያየ መጠሪያ ያውቋት እንደነበር ይታመናል፡፡እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡፡
Ø ፩.፩. ጱንጥ፤- ይህን ስያሜ አስመልክቶ ሁለት አይነት አስተያየቶች አሉ፡፡የመጀመሪያው ጱንጥ የተባለው ስም ከአራቱ የካም ልጆች አንዱ ከሆነው ከ‹‹ፉጥ›.ጋር ይመሰሰላል የሚለው ነው፡፡
Ø የካም ወንዶች ልጆች ስም ተጠቅሷል፡፡ እነዚህም ሚዝራይም፣ኩሽ፣ ከነዓን እና ፉጥ ናቸው፡፡
Ø ዘፍ 16 እዚህ ላይ ኢትዮጵያን ያቀኗት የካም ልጆች /ዘሮች /ናቸው፡፡ የሚለው ትውፊታዊ ምስክርነት ስላለ ምን አልባትም በዚሁ ምንያት አገሪቱ ጱንጥ የሚለውን ስያሜ ከካም ልጆች አንዱ በሆነው ፉጥ በሚለው አግኝታ ሊሆን ይችላል የሚል ነው ፡፡
Ø በሌላ አነጋገር የጥንት ግብጻውያን የታሪክ መረጃዎች በአፍሪካ ቀንድ ‹‹ፑንት››የሚባል ጥንታዊ መንግስት ትክክለኛው የግዛት ወሰን የታወቀ ባይሆንም የዛሬዋ ኢትዮጵያ በኢያ ስር እንደምትጠቃለል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Ø በጥንታውያኑ ግብጾች አጻጻፍ በፒራሚዶች ላይ መረጃዎችም ግብጻውያን ፈርዖኖች ውድና ብርቅ የሆኑ ዕቃዎችን ከ‹‹ፑንት››ያገኙ እንደነበር ያመለክታሉ ፡፡
Ø በተለይም ዕጣን፣ የዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ ከርቤና የዐይን ኩል ዋና ዋነዎቹ ናቸው፡፡እነዚህ ነገሮችም በተለይ ከሌሎች በተሸለ የሚገኙት ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ነው፡፡
v ከሚታወቁት ታሪካዊ ማስረጃዎች ሌላ በሁለቱም አገሮች በጋራ የሚታወቁት አንዳንድ ቁሶች ይህንንሃሳብ ሚየጠናክሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን እንውሰድ
ü የኢትዮጵያና የግብጽቆነጀጅቶችየሚጠቀሙበት
የዐይን ቅባት በሁለቱም አገር ሰዎች እስከዛሬ ድረስ በተመሳሳይ መጠሪያ ‹‹ኩል›› በመባል ይታወቃል
ü በአገራችን የምንጠቀማቸው አንዳንድ ጌጣጌጦች /ለምሳሌ አምባር፣ጨሌ‹‹‹ የግብጻውያን ተፅዕኖ አለባቸው፡፡
ü ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ዕጣን ጥንታውያን ግብጾች ለአምልኮአቸው ይጠቀሙበት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በሁለቱ አካባቢዎች በተመሳሳይ መጠሪያ ዕጣን ተብሎ ይታወቃል፡፤
ü ጸናጽል፣ዋሽንትየመሳሰሉት የመዝሙር መሳሪያዎች ጥንት መሰረታቸው ግብጽ እንደነበረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ü አሁን በዝዋይና በጣና ሐይቆች አካባቢ የሚያገለግሉ ጀልባዎች ከጥንት ግብጻውያን ጀልባዎች ጋር በጣም ይመሳሰላሉ፡፡
ü እንግዲህ ይህ ሁሉ በአጋጣሚ የሆነ ነው ለማለት ያዳግታል፡፡
ü ይልቅስ ሁለቱ አገሮች በጥንታዊ ታሪክ የባህልና የንግድ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁምና ‹‹ጱንጥ››የሚለው ስያሜያቸው የሚያመለክተው በበርካታ ነገር የሚያውቁት የሚያውቁት የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ü ፩∙፪. ቶ-ኔቶር፤- ይህ ስያሜ የጥንት ግብጻውያን ለኢትዮጵያ ምድር የሰጡት ስያሜ እንደነበር ሲታወቅ ትርጉሙም ‹‹የአምላክ ሀገር›› ማለት ነው፡፡
ü ግብጻውያን የዛሬዋን ኢትዮጵያ አካባቢ ‹‹የአምላክ ሀገር ››ብለው መጥራታቸው ሁለት ዓበይት ምክንያቶች ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡
ü የመጀመሪያው ለግብጻውያን የሥልጣኔ መስረትና የኑሮ ዋስትና የሆነው የናይል (ዓባይ) ወንዝ መነሻ ስለሆነች ሲሆን
ü ሁለተኛው ደግሞ ጥንታውያን ግብጻውያን ለአማልክቶቻቸው የሚያቀርቡት ዕጣንና ሌሎች ውድ የሆኑ ሽቶዎች የሚያገኑት ኢትዮጵያ ስለነበር ነው፡፡
ü ፩∙፫.የኩሽ ምድር፤- ይህ ስያሜ ግብጾች ከሃገራቸው በስተደቡብ ያለውን ሰፊ ቦታ የሚያውቁበት ሌላኛው መጠሪያ ነው፡፡
ü ሊቀ ነቢያት ሙሴም ብሉይ ኪዳንን ሲጽፍ ኢትዮጵያን የኩሽ ምድር እያለ መጥራቱ በግብጽ ምድር ተወልዶ ማደጉንና የግብጻውያንን ባህልና ቋንቋ ያውቅ ስለነበር ነው፡፡
ü የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ደግሞ ኢትዮጵያ የኩሽ ምድር ተብላ ስትጠራ የነበረችበት ምክንያት የካም የመጀመሪያ ልጅ የኩሽ ዘሮች ስለሰፈሩባት እንደሆን ይገልጻሉ፡፡ዘፍ 16 ፡፡
ü ከጌታ ልደት በፊት በ284 ዓመት ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክኛ (ጽርዕ) የተረጎሙት ሰባው ሊቃውንትም ሙሴ ‹‹ኩሽ››እያለ የጻፈውን ‹‹ኢትዮጵያ›› በሚል የተኩትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ይቀጥላል………………