የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, October 12, 2019

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ


        የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ማለት ምን ማለት ነው?
        የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ማለት፤-
  1. 1. የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የክርስትና ሃይማኖት ታሪክ ነው፡፡

        በመሆኑም በዋናነት የሰው ልጅ ከአምላኩ ጋር ለዘመናት የነበረውን ግንኙነት ማዕከል ያደረገ የመንፈሳዊ ትምህርት ዘርፍ ነው፡፡
        የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ዕለት ጀምሮ እስካለንበት ጊዜ ድረስ ያሳለፈችውንና የኖረችበትን የረዥም ዘመን እንቅስቃሴ ለመዳሰስ መንፈሳዊና ቁሳዊ ክንዋኔዎችን የሚያትት ሃይማታዊ ጉዞ ነው፡፡
የኢትዮጵያ   ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጥናት አከፋፈል
        በጊዜ ቅደም ተከተል መሰረት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአራት አበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
        . የኢትዮጵያ እምነት በክርስትና በፊት - ይህ ክፍል በሕገ ልቡን እና በሕገ ኦሪት ዘመን በአገራችን ስለነበረው አጠቃላይ የእምነት ሁኔታ እና በዚሁ ዘመን ተያያዥነት ያላቸውን ታሪካዊ ክስተቶች የምንመለከትበት ነው፡፡
        . ክርስትና በጥናታዊት ኢትዮጵያ፤- ይህ ክፍል በአክሱምባ ዛጉዌ ሥርወ መንግሥት ዘመን የተከናወኑ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ነክ ጉዳዮች የምናጠናት ነው፡፡
        . የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በመካከለኛው የታሪክ ዘመን፤- ይዞ ክፍል እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 1270/ ጀምሮ እስከ 1855 / ድረስ የነበረውን የቤተ ክርስቲያን ጉዞ የምንዳስሰብት ነው፡፡
        . የኢትዮጵያ ቤተ ክርስስቲያን በዘመናዊ ታሪክ - ይህ ዘመን ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ጀምሮ /1847-1860// እስካለንበት ጊዜ ድረስ ያለውን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ሒደት የምንረዳበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ   ቤተ ክርስቲያን  ሥያሜ
  • ጥንታዊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋህዶ›› በመባል ትታወቃለች፡፡
  •  ኦርቶዶክስ የሚለው ‹‹ኦርቶ›› እና ‹‹ ዶክስ›› ከሚሉት ሁለት የግሪክ ቃላት የተወሰደ ነው፡፡‹‹ኦርቶ›› ማለት ቀጥተኛ የተስተካካለ ማለት ሲሆን ‹‹ ዶክስ›› ደግሞ እምነት አመለካካት ማለት ነው፡፡
  • ስለሆነም በአንድ ላይ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ/ርቱዕ/ የሆነ ማለት እምነት /ሃይማኖት/ማለት ነው፡፡
  •  ኦርቶደክስ የሚለው ሥያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 325/ በኒቅያ /በታናሻ እስያ/ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን ናቸው፡፡በዚህ ጉባዔ አርዮስ ተወግዟል፡፡
  •   ኦርቶዶክስ የሚለው ሥያሜ ከኢትዮጵያና ኦሪየንታል ከሚባሉ አኀት አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ ግሪክና ራሽያን የመሳሰሉ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናትም ይጠቀሙበታል፡፡
  • ይህን ሥያሜ ከክርስትና ውጭ የሚገኙ ሌሎች የእምነት ድርጅቶችም የሚገለገሉበት ሲሆን ለአብነት ያህልም እምነታቸውን የሚጠበቁ አይሁዶች እና የሱኒ ሙስሊሞች ኦርቶዶክሶች ተብለው ይጠራሉ፡:
  • ስለሆነም ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ ይልቅ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ማንነት ይበልጥ የሚገልጸው ‹‹ ተዋህዶ›› የሚለው ቃል ነው፡፡
  • በኒቂያ እና ኤፎሶን ጉባዔ መካካል እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 381/ 150 የሚሆኑ ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተነሳውን የመቅዶንዮስን ትምህርት  አውግዘዋል፡፡
  •  ‹‹ተዋህዶ›› የሚለው ስያሜ መሰረታዊ መነሻው እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 431/ የተካሄደው የኤፎሶን ጉባዔ ነው፡፡
  •   በዚህም ጉባዔ 200 ሊቃውንት የተገኙ ሲሆን በእስክንድሪው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ መናፍቁ ንስጥሮስን ተከራክሮ መልስ በማሳጣት ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ኩራት አጎናጽፏል፡፡
  • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስቀድሞ የተጠቀሱትን የኒቅያና/325//   የቁስጥንጥንያ /381// እና ኤፎሶን /431// የሃይማኖት ጉባኤያትን እና ውሳኔዎቻቸውን ትቀበላለች ስለሆነም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትጠራለች፡፡
  • ኦሮንታል ተብለው የሚቃወቁት የግብፅ፣ሶርያ፣ሕንድና የአርመን አብያ ክርስቲያናት  ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር የትምህርት ሃይማኖት እና የታሪክ አንድነት ያላቸውና የተዋህዶ እምነት የሚከተሉ ናቸው፡፡

  እነዚህ አምስቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባህርይ ነው›› ብለው ስለሚያምኑ የኬልቄዶንን ጉባኤ/451//ውሳኔና የሁለት ባህርይ ትምህርት የማይቀበሉና የሚያወግዙ ናቸው፡፡
ይቀጥላል….…


Post Bottom Ad