ጥቅምት 4 - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Sunday, October 13, 2019

ጥቅምት 4

በረከታቸው ይደርብን

  • ቅዱስ ባኮስ በሰማዕትነት ዐረፈ
  • ከሰባሁለቱ አርድ እት ሐናንያ በሰማዕትነት ዐረፈ
  • ለአባ ጰንጠሌዎን ዘጸማዕት ዕረፍቱ
  • ሮማውያን ጻድቃን የጃንደረባው ዮሐንስና ገብረ ክርስቶስ መታሰቢያ
  • የኢትዮጵያ ነገሥታት አብርሐና አጽብሐ የዕረፍታቸው መታሰቢያ

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ ጠላቴ ሰይጣንን እክደዋለሁ ለዚህም ምሥክሬ ድንግል ማርያም ናት!!!
☞ሀገራቸው ሮም፤ትውልዳቸው ከቤተ መንግሥት ነው፡፡ቁጥራቸው ከተሰዓቱ ቅዱሳን ነው፡፡
☞ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አልሜልዳ በነገሠ በ፭ ዓመት ነው፡፡እንደመጡም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በአክሱም ፲፪ ዓመት ኖረዋል፡፡አንድነቱ ለጽሙና ለብሕትውና የማይመቻቸው ቢሆን ተለያይተው የራሳቸውን በዓት ሠርተው ገዳም አቅንተው የሚኖሩ ሆነዋል፡፡በዚህ ጊዜ አባ ጰንጠሌዎን ከነበሩበት ፪ ምዕራፍ ያህል ርቀው በልካቸው በዓት ሠርተው እሕል ውኃ ሳይቀምሱ ፵፭ ዓመት ኖረዋል፡፡
☞ብዙ ልዪ ልዪ ድንቅ ድነቅ ተአምራትን አድርገዋል፡፡ከብዙውም አንዱ ይህ ነው አጼ ካሌብ የሰማዕታት ናግራንን ደም ለመበቀል ወደ ሳባ ሲዘምቱ አባቴ መርቀህ አሰናብተኝ አሏቸው መርቀው አሰናብተዋቸዋል፡፡ሳባውያንን እንደ ጎመን ቀርድደው ፈጅተዋቸው የዘረፉትን ነዋያተ ቅድሳት መልሰው በተደረገላቸው ረድኤት እየተደነቁ ሲመለሱ ብላቴኖቻቸው አባ ጰንጠሌዎን ሐፀ እሳት ይዞ በመካከላቸው እየተመላለሰ ሲፈጃቸው አይተናል አሏቸው በዚህ ምክንያት ንጉሡ መንግሥታቸውን ትተው ከሳቸው መዓረገ ምንኩስናን ተቀብለው በጽሙና የሚኖሩ ሆነዋል፡፡
☞ጌታ እረፍታቸውም ሲደርስ ጌታ በኪዳንህ የተማጸነውን ከሞተ ነፍስ አድንልሀለሁ ብሎ ተስፋውን ነግሯቸው በዚህ ዕለት በክብር ዐርፈዋል፡፡(በ480 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ታላቅ ወቅት ነው)
✔✔✔በረከቱ ይደርብን!!!

Post Bottom Ad