የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ አበውን፣ ሕገ ኦሪትንና ሕገ ወንጌልን..አስተባብራ በመያዝ የጥበብ ምንጭ፣ የሥርዓት መፍለቂያ፣ የዕውቀትባሕር ሆና ሁሉ የተሟላላት ስንድ እመቤት ናት። በማኅበራዊ..አገልግሎቷ ደግሞ የድኩማን መጠጊያ፣ ያዘኑና የተከፉ መጽናኛ፣የማንነትም አሻራ ነች። ለዚህም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በተለያዩ..ገዳማት፣ አድባራት፣ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶች
ተቀዳሚ ተጠቃሾች ናቸው። በተለያዩ ጊዜያት የተንኮልና የክህደት.ቋጠሮ ይዘው የመጡ መስሐቲያን (አሳሳቾች) አፍረው የተመለሱት..ከአብነት ት/ቤቶቹ በወጡ መምህራን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለሀገር
መሪ ለሕዝብ አስተማሪ በመሆን ሕዝብን ያገለገሉ ደጋጎች ከእነዚህ የአብነት ት/ቤቶች በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ናቸው።
መሪ ለሕዝብ አስተማሪ በመሆን ሕዝብን ያገለገሉ ደጋጎች ከእነዚህ የአብነት ት/ቤቶች በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ናቸው።
የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ሳይከለስና ሳይበረዝ ተጠብቆ እስከአሁን.እንዲዘልቅ ያደረጉት ገዳማት፣ አድባራት፣ አብያተ ክርስቲያናት እና.የአብነት ት/ቤቶች ናቸው። ስለሆነም እነዚህ የትምህርት ማዕከላት.በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንዳይዘጉ፤ መምህራኑና ተማሪዎቻቸው.እንዳይሰደዱ፣ ወንበር እንዳይታጠፍ በጋር እና በተናጠል ድጋፍ ሲደረግ.መቆየቱ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ.በመምጣቱ የእሳት ማጥፋቱ ሥራ በልማት ቢታገዝና ዘላቂ መፍትሔ.ማግኘት ቢቻል መልካም መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ነው።
ገዳማት አድባራትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ.ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ለኢትዮጵያ ተቆጥሮና ተሰፍሮ የማያልቅውለታ የዋሉ፤ እንደ ዓይናችን ብሌን ልንጠብቃቸው የሚያስፈልጉ.የተቀደሱ ሥፍራዎቻችን ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን አራት ጉባኤያት አሉ። እነዚህም መጽሐፈ ሐዲሳት፤ መጽሐፈ
ብሉያት፤ መጽሐፈ መነኮሳት፤ መጽሐፈ ሊቃውንት ያባላሉ። እኔም ከአሜሪካ
ተነስቸ ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩበት ዋና ዓላማየ መጽሐፍትን ለመማር ነበር።
ቲዮሎጅ ለመማር። የእኔ ነገር። እግዚአብሔር ግን ከልብ መሻቴን ያውቅ ነበርና ቲዮሎጂውን በሩቁ እንድማር
መጽሐፈ ትርጓሜን ደግሞ በቦታው ተገኝቼ እንድማር በወንድሞቼ አማካኝነት ከነገረኝ በኋላ ሃሳቤን ቀይሬ ወንድሞቼ እንዳሉት ቲዮሎጅን
በርቀት፤ መጽሐፍትን በአካል እንድማር ሆነ። በመጀመሪያ ከመምህሬ
ከየኔታ ዳንኤል የቁስቋም የቅኔ መምህር ጋር በመሄድ አንድ አመት ከ5 ወር ተማርኩ ከዚያም ወደ ግምጃ ቤት ማርያም መጽሐፈ ሐዲሳት
ትርጓሜ በአካል ከሰኞ እስከ አርብ ተማርኩ። ከሰዓት በኋላ መጽሐፈ
መነኮሳትን ተማርኩ። ስለዚህ መጽሐፈ ሐዲሳትንና መጽሐፈ መነኮሳትን በመማሬ እጅግ ደስተኛ ነኝ። ለዚህም የመጽሐፈ ሐዲሳት መምህሬ መምህር የኔታ ቃለ ሕይወትና የመጽሐፈ መነኮሳት
መምህሬን መምህር የኔታ ተሾመን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። ረጅም
እድሜና ጤና ያድልልኝ። ቅዳሜንና እሁድን ደግሞ የነርስ ዲግሪን ተምሬ
በመመረቄ እጅግ ደስተኛ ነኝ። ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፍኩት ስድስት
ዓመታት በትምህርትና በትምህርት ብቻ ነበር። እኔ የተረዳሁት ነገር
ቢኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷ ፈጽሞ አያልቅም። ከውቂያኖስ ላይ በጭልፋ መጨለፍ ያህል ነውና። ብቻ ደስታየ እጥፍ ነው።
Theology Graduation 2010 E.C
Bachlor of Nursing Graduation at Blue Nile College in Gondar