ደብረዘይት ምን እየሆነ ነው?

Saturday, September 28, 20190 comments
ትናንት በደብረ ዘይት ከተማ የመስቀል በዓልን ለማክበር ሰንበት ተማሪዎች በለበሱት ልብስ ምክንያት
ፖሊስ "መልበስ አትችሉም" በማለቱ በተፈጠረው ችግር ደመራ ሳይለኮስ ቀርቶ ነበር:: ይሁን እንጂ
ማንነታችው የማይታወቁ ጎረምሶች ሌሊት 5:00 አካባቢ ካህናት እና ምእመናን በሌሉበት ደመራውን
ለኩሰው አንድደውት አድረዋል::
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ጎርጎርዮስ በችግሩ መንስኤ ላይ እና
በተፈጠረው ሥርዓት አልበኝነት ላይ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ዛሬ ቀን ከ 7:00 ጀምሮ
ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እንደገቡ ሳይወጡ በመዋላቸው "አባታችንን ልቀቁልን" ከሚሉ ምእመናን ጋር
ፖሊስ በድጋሚ መጋጨቱን አረጋግጬአለሁ::
ማንነታቸው በውል ያልታወቁ "ቄሮ ነን" የሚሉ ወጣቶች የሊቀጳጳሱን መፈታት ለመጠባበቅ በከንቲባ
ጽህፈት ቤት ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር ምሽት ላይ ግብግብ በመፍጠራቸው የክልሉ ፖሊስ አስልቃሽ
ጭስ በመተኮስ ምእመናንን የበተነ ሲሆን "ቄሮ ነን" ባዮቹን ጽህፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ ሰብስቦ
እንደዘጋባችውም ሰምቻለሁ:
ሊቀጳጳሱ ለውይይት ወደ ከንቲባዋ የመስተዳድር ቢሮ ሃያ ከሚሆኑ አገልጋዮች ጋር እንደገቡ እስከምሽቱ
1:00 ምክንያቱ በውል በማይታወቅ ሁኔታ ቆይተው የነበረ ሲሆን አሁን በስልክ እንደሰማሁት ግን
ተለቀው ወደሀገረ ስብከታቸው ገብተዋል::
source በኃይሉ ደምሴ
Share this article :

Advertisement / ሰለስቱ ምዕት ቤተ ክርስቲያንና ጉባኤ ቤት ጎንደር

 
Support : Creating Website | | መ/ር ንጋቱ አበበ
Copyright © 2011. አትሮንስ ዘተዋሕዶ - All Rights Reserved
Template Created by Published by መ/ር ንጋቱ አበበ
Proudly powered by Blogger