አትሮንስ ነሐሴ 28 ቀን
2011 ዓ/ም
አጠቃላይ የስብሰባው ድባብዛሬ ሐሙስ አስቸኳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከ50ሚልዮን በላይ የኦርቶዶክስ አማኝ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረ ጉባኤ ነበር። ጉባኤው ወደፊት የቤተክርስቲያናችንን የጉዞ ምዕራፍ የሚያሳምር ወሳኝ ጉባኤ ነበር። ጉባኤው ወደ ሰባት አጀንዳዎች ቀርጾ ነበር ወደ ስብሰባ የጀመረው።
ከወትሮው በተለየ ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት እና የታረዱ ካህናት የፈሰሰው ደምና እንባ በሕሊናቸው እያቃጨለ በቁጭትና በመንፈሳዊ ወኔ ተሞልተው ነበር ስብሰባውን የጀመሩት።
በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጸሎት አድርሰው ውዳሴ ማርያምና ጸሎተ ማርያም ተደርሶ3:00 ላይ ስብሰባው ተጀመረ።
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ( ዳግማዊ እለስክንድሮስ) የእንኳን ደህና መጣችሁና አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤው መጠራት ለምን እንዳስፈለገው አጭር ንግግር አደረጉ።
በመቀጠልም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍ በሚያምር አንደበታቸው ስለሚወያዩባቸው አጀንዳዎችና ስለ አጀንዳዎች ማብራሪያ ሰጡ።
ቤተክርስቲያን ስለደረሰባት መከራና መራር
ዘግናኝ ታሪክ የማይረሳው ሰቆቃ ውይይት ተጀመረ
የቅዱስ ሲኖዶሱ ድባብ አትጠይቁኝ መንፈስ ቅዱስ የወረደ እስኪመስል ድረስ ይናገራሉ ተብሎ የማይጠባበቁ አባቶች ሳይቀር ያወርዱት ጀመር
ማን ምን አለ በከፊል ነው ወዳጆቼ?
ከንግግራቸው ቀንጨብ አድርጌ
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
" እኔ አባቶቼ ቤተክርስቲያን ብቻ አይደለችም የተቃጠለችው የ3000 ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ እንጂ ታዲያ ታሪክ ሲቃጠል ዝም የሚል መንግስት ምን ይሉታል ተሸውደናል ተንቀናል የፈራ ይመለስ እኔ መቃብር እስክገባ እፋለማለሁ "
አቡነ ሩፋኤል
" አባቶቼ የደረሰብንን ዘግናኝ ግፍ አንረሳውም አሁን ማንንም የምንጠብቅበት ዘመን ላይ አደለንም ሁላችን ወደ ፊት እኔን የሚያስተዳድረኝ ሰማያዊ መንግስት ነው "
አቡነ ጎርጎርዮስ
" ኦርቶዶክስ ሃገር ናት ብሎ የነገረን መንግስት ቤተክርስቲያን ስትቃጠል ሃገር መቃጠሏን ረስቷል ቅድሚያ ሰላም ማምጣት ነበር ተቀዳሚ ተግባሩ "
ከዚህ ውይይት በኋላ
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የጠቅላይ ሚንስተሩ ተወካይ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገቡ
ሁሉም አበው ጋር የሚነበበው እንደ ቀድሞው ባለስልጣን ሲመጣ እንደሚያስተናግዱት ሳይሆነ በሃዘኔታ ገፅታ ተቀበሏቸው።
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቤተክርስቲያን ስለደረሰባት ችግር አብራርተው
ጥያቄዎችን ማዝነብ ጀመሩ
ከበርካታ ንግግራቸው ና ጥያቄያቸው በጥቂቱ
" መንግስት ሥራውን እየሰራ ነው ብለን ባናምንም ትመልሱልናላችሁ ብለን ተስፋ ባናደርግም ለመሆኑ በኦሮሚያ ክልል ከክልል ዞንና እስከ ቀበሌ ድረስ የምትሾሙት ፕሮቴስታንትን ብቻ ለምን ሆነ ? " ኦሮሚያ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚመሩት አካላት ማን ነው እድል የሰጣቸው የልብ ልብ ማን ሰጣቸው?
ምዕላተ ጉባኤው የቅዱስነታቸውን ብርታት እያየ ፊታቸው በደስታ ተሞላ
አቶ ሽመልስ ባፋጣኝ እናስተካክላለን ከእናንተ ከአባቶቻችን ጋር መስራት እንፈልጋለን ከማለት የዘለለ የሚያወራው ሁሉ በፍርሐት ነበር
ስለኦሮሚያ ቤተክህነት ስለተባለው ነገር
እንደ ኦሮሚያ ክልል ተቀባይነት የለውም
ብሏል ከሲኖዶስ ያፈነገጠ መንግስታችን
አይቀበልም
በየተራ እየተነሱ አወረዱት ስንቱን አውርቼና ጽፌ ስንቱን ልተወው ምንስ ያልተናገረ አባት አለ ሁሉም እረ ጉድ ነው። መላ የሲኖዶስ አባላት ተናገሩት አይገልጸውም
የችግሮችን ምንጭ ለይተን እንወቃቸው ተልካሻ አሰራሮችን እናስወግድ ተዋሕዶን እናስቀድም የውይይቱ አካል ነበር።
ጸልዩ
ኒቅያ በሉት
ጉባኤው አሁን ይቀጥላል ውሳኔዎች ይጠበቃሉ።