🔥ክቡር ከንቲባው ሰላማዊ ሰልፍ ከጠሩ አካላት ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡🔥 - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Thursday, September 5, 2019

🔥ክቡር ከንቲባው ሰላማዊ ሰልፍ ከጠሩ አካላት ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡🔥

አትሮንስ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲያስቆም መንግሥትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ የፈቃድ ደብዳቤ ካስገቡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራት ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡
በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በመሻሻል ፈንታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱና ቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያኖች ተለይተው የጥፋት ዒላማ በመሆናቸው ችግሩን እንዲያስቆም መንግሥትን ለመጠየቅ ደብዳቤ ያስገቡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራት ከዚህ በፊትም በግንቦትና ሰኔ ወር ላይ በኢትየጵያ ሆቴል እና በዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ እየደረሰ ያለውን ችግር አስመልክቶ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
ከክቡር ምክትል ከንቲባው ጋር በመወያየት ላይ የሚገኙት እና ሰላማዊ ሰልፉን የሚያስተባብሩት ማኅበራትም-
1. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
2. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት
3. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት
4. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
5. በኢ/ኦ/ተ/ቤ./ክ በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን
6. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት
7. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሠለስቱ ምዕት ማኅበራት ኅብረት
8. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ተናሥኦት ኅብረት ናቸው፡፡

Post Bottom Ad