ርዕሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ በአዲስ ዓመት
መግቢያና በወሮች መጀመሪያ በሆነው መስከረም አንድ ቀን በልዩ ልዩ የአከባበር ሥነ ሥርዓት የሚከበር ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአከባበር ሥር ዓት ከሚከበሩ ሃይማኖታውያንና ብሔራውያን በዓላት አንዱ ነው።
የመስከረም 1 ቀን ትርጉም
ü
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የርዕሰ ዓውደ
ዓመት ቅዱስ ዮሐንስን በዓል ምክንያት በማድረግ ዘመናትን ከዘመናት፤ ወሮችን ከወሮች፤ ሳምንታትን ከሳምንታት፤ ዕለታትን ከዕለታት
ለይታና ወስና በዓመት ውስጥ የሚውሉ አጽዋማትንና በዓላትን በምን ቀንና በመቼ ወቅት እንደሚውሉ የምታውጅበት
ü
አሮጌው ዘመን አልፎ አዱሱ
ዘመን የሚተካበት
ü
ዘመነ ማቴዎስ፤ ዘመነ ማርቆስ፤
ዘመነ ሉቃስና ዘመነ ዮሐንስ በየአራት አመታቸው በተራ የሚቀያየሩበት
ü
አሮጌው ዓመት ሊያልፍ ክረምት
ሲመጣ፤ ዝናብና ማዕበል፤ መብረቅና ጎርፍ፤ ጭቃና ጉሙ፤ በተለይ ደግሞ በረዶው ተወግዶ ግንዱ ወደ ልምላሜ፤ ልምላሜው ወደ አበባ
ተለውጦ የሚታይበት
ü
ጨለማው ወደ ብርሃን ተለውጦ
የሚታይበት
ü
የጨለማ ዘመን አልፎ የብርሃን
ዘመን የሚተካበት፤ አዲስ ሕይወት የምንጀምርበት
ü
ስለ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም ‹‹ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› ብሎ አምላክ ወልደ አምላክነቱን የመሰከረ፤ አምላኩን ያጠመቀ፤ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የሚከበርበት የሚታሰብበት::
ዮሐ 1፡29-34
ü
በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን
ሁሉ አዲሱን ዘመን ምክንያት በማድረግ ልብሳችንን በውሃ ኃጢአታችንን በንስሐ አጥበን አዲስ ሕይወት የምንመሰርትበትና አዲስ የጽድቅ
ሥራ የምንጀምርበት
ü
ከአሮጌው ዓመት ወደ ዓዲሱ
ዓመት የተሸጋገርንበት
ü
ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ
መጸው የተሸጋገርንበት
ü
በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ አዳኝነት ከዓመተ ፍዳ ወደ ዓመተ ኩነኔ፤ ከኦሪት ወደ ወንጌል፤ ከሲዖል ወደ ገነት የተሻገርንበት መሆኑን የምናስብበት
ü
የጥፋት ውሃ መታሰቢያ የሆነውን
ዘመነ ክረምትን አልፈን አዲስ ዘመንንና አዲስ ወርን መጀመራችንን የምንሰብክበት
ü
አሮጌው ዘመን አልፎ አዲስ
ዘመን እንደሚተካው ሁሉ ይህ ዓለም አልፎ ዘለዓለማዊ የሆነ ሌላ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ተስፋ የምንይዝበት ታላቅ የምስጢር ዕለት
ነው።
የአውደ ዓመት መጠሪያ ስሞችና ትርጉም
1.
ርዕሰ ዓውደ ዓመት፤
ü
ር ዕስ፤ ዓውደ፤ ዓመት የሚሉት
የሦስቱ ቃላት ጥምር ነው።
ü
ር ዕስ ማለት ዋና፤ መጀመሪያ፤
መነሻ ማለት ነው
ü
ዓውድ ማለት ዙሪያ፤ መስከርከሪያ፤
መመለሻ ማለት ነው
ü
ዓመት ማለት ከመስከረም ወር
ጀመሮ እስከ ጳጉሜ ድረስ ያለው የ365 ቀናት መጠሪያ ስም ነው
ü
የአማርኛ መዝገበ ቃላት የዘመን
መለወጫ በዓል፤ እንቁጣጣሽ መስከረም አንድ ቀን የአዲስ ዓመት መጀመሪያ በሚል ይገልጸዋል።
2.
ርዕሰ አውራኅ፤
ü
እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
የወሮች ራስና የወሮች መጀመሪያ የሆነው መስከረም ሲሆን ር ዕሰ አውራኅ የተባለበትም ምክንያት የ12 ወሮች ሁሉ መጀመሪያና ራስ
ስለሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስም አዲስ ወር ሲል ይገልጸዋል፤ ዘጸ 23፤14 ይህም የአዲሱ ዘመን ወር የሚለወጥበት ስለሆነ ከዚያ ጋር
ተያይዞ የተሰጥጠ ስያሜ መሆኑን ያመለክታል።
3.
በዓለ መጥቅዕ፤
ü
ጠቅዐ መታ ከሚለው የግዕዝ
ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደወል ወይም መለከት ማለት ነው። የባሕረ ሐሳብ ቀመር ስም በመሆንም ያገለግላል
ü
በዓለ መጥቅዕ ብሎ ሲናበብ
(ሲጣመር) የአዋጅ መንገሪያ ቀን የመጥቅዕ (የደወል) መታሰቢያ በዓል ማለት ነው
ü
ይህ በዓለ መጥቅዕ ከኖህ ጀመሮ
የመጣ ሲሆን በብሉይ ኪዳን ጀመሮ የተሰሩ በዓላትና አጽዋማት በምን ቀንና ወቅት እንደሚውሉ ይታወጅበት ነበር ዘሌ 23፤25
4.
ጥቢ
ü
“ጸብሐ” ጠባ (ነጋ) ከሚለው
የግ ዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ንጋት፤ ጎሕ መቅደድ ማለት ነው። በዘመን የአከፋፈል ይትበሃል ጎሕ ጽባሕ የሚባለው የመስከረም
ዋዜማ የጳጉሜን ሳምንት ነው። የመስከረም ወር መጀመሪያም ክረምቱ
የሚነጋገርበትና የዘመን መሸጋገሪያ ጊዜ ስለሆነ በተልምዶ ጥቢ እየተባለ ይጠራል። እንዲሁ ከመስቀል በዓል ቀጥሎ ያለውም ሰሞን በተለምዶ ጥቢ መስቀል ይባላል
ትርጉሙም የመስቀል ብርሃን የታየበት ጊዜ ማለት ነው።
5.
በዓል
ü
በዓል ማለት የአከባበር ደረጃ
ያለው ሲሆን የአምላክንና የቅዱሳን በዓላት የወል ስም ነው። ይህም
በዓለ አከበረ ከፍ ከፍ አደረገ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን የከበረ የገነነ ከፍ ከፍ ያለ የተቀደሰና የተለየ በዓል ማለት
ነው።