ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Tuesday, September 3, 2019

ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

አትሮንስ ነሐሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም

ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ጠርቷል።  በየአህጉረ ስብከቱ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት ለነሐሴ 28 ቀን ለሚደረገው አስቸኳይ ስብሰባ እንዲገኙ መልእክት ተላልፎላቸዋል።  ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የማንነትም ጭምር በመሆኑ ጉዳዩን አስረግጠው ማስፈጸም አለባቸው ባይ ነኝ።  ምክንያቱም በአሁኑ ሰዓት ስልጣን ላይ ያሉት የእስልምና እና የፕሮቴስታንት ተከታይ በመሆናቸው ይህን ሥልጣን ተጠቅመው ቤተክርስቲያኒቷን ለመከፋፈልና የማፈራረስ ዕቅድ ይዘው የተነሱትን የዘመኑ አርዮሳውያንን በአንድ መንፈስ ሆነን ልንቃወም ይገባል።  ይህ የሕይወት ጉዳይ ነው።  የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ።  አባቶቻችን ውሳኔ እስኪሰጡን ድረስ ባለንበት በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ ይኖርብናል።  
አባቶቻችንም የሚነግሩንን ለመስማትና በፍጥነት የታዘዝነውን ለመፈጸም በንቃት ተዘጋጅተን መቆም አለብን።  ሁልጊዜ መቻቻል እየተባለ መጥፋት የለብንም።  የሚታረዱት ካህናትና ምዕመናን ደማቸው ይጮሃል።  ከአሁን በኋላ ግን መከባበር ግድ ይላል አለበለዚያ ግን የሚመጣውን ድብን አድርገው አካሪዎቹም ያውቁታል።  አድዋ፤ ዮዲት ጉዲት፤ ግራኝ መሀመድ፤ ጣልያን፤ እንግሊዝ ሞክረው በሽንፈትና በውርደት ተከናንበው አልፈዋል። ስለዚህ መከባበሩ መልካም ይመስለኛል።  ካልሆነ ግን የምትፈልጉትን ማድረግ ቀላል ነው ባይ ነኝ።  አንዳንድ የእስልምና ተከታይ የሆኑ ወገኖቻችን ሲቃወሙ አይቻለሁ ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ ከመቃጠል ግን አልዳነችም ስለዚህ ተባብረን እረፉ ልንላቸው ይገባል ባይ ነኝ።

Post Bottom Ad