አትሮንስ
ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ/ም
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ(ፍዳ)
= 2012 + 5500 =7512
❖ ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለምን ለአራት አካፍለን የዓመቱን ወንጌላዊ
እናገኛለን።
= 7512 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል
7512 - 4×1878 = 0
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 4 ' ወይም ' 0 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ
ይሆናል። ስለዚህ ቀሪው ' 0 ' ስለሆነ
የዘንድሮው ወንጌላዊ ዮሐንስ ስሆን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ
ይባላል።
❖ መባቻ= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት ÷7
= 7512 + 1878 ÷ 7 = 9390 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 3
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ ሰኞ
ቀሪው ' 1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው ' 4 ' ከሆነ ዓርብ
ቀሪው ' 5 ' ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው ' 6 ' ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም
ቀሪው ' 3 ' ስለሆነ ዘንድሮ መባቻ(ዘመን መለወጫ)
ሐሙስ ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ መደብ = ዓመተ ዓለምን በ19 በመግደፍ እናገኛለን።
= 7512 ÷ 19 = 395 ደርሶ 7 ይቀራል። ስለዚህ መደብ
7 ይሆናል
❖ ወንበር = ከመደብ አንድን ለዘመን በመተው ወንበርን
እናገኛለን። ስለዚህ ወንበር 6 ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ አበቅቴ ፦ አበቅቴን ወንበርን በጥንተ አበቅቴ አባዝተን
በ30 ገድፈን እናገኛለን።
አበቅቴ = 6 ×11= 66 ÷ 30, ' 2' ደርሶ ቀሪው '6'
ስሆን ዘንድሮ አበቅቴ ' 6 ' ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
❖ መጥቅዕ ፦ ወንበርን በጥንተ መጥቅዕ አባዝተን ለ 30
አካፍለን እናገኛለን።
መጥቅዕ = 6×19 = 114 ÷ 30 ቀሪው ' 24 ' ስለሆነ
መጥቅዕ ዘንድሮ ' 24 ' ይሆናል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
✿መጥቅዕ፦ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ፤ ከ14
በታች ከሆነ በጥቅምት ይውላል፡፡
❖ ፆሜ ነኔዌ = ፆሜ ነኔዌን መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ
በመደመር እናገኛለን፡፡
ዘንድሮ መጥቅዕ በመስከረም ሲውል መስከረም 24
በቅዳሜ ይውላል። የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው።
ስለሆነም ፆሜ ነኔዌ 8 + 24 = 32 ስሆን በ30 ገድፈን '
2' ይቀራል። ስለዚህ ዘንድሮ በየካቲት ' 2 ' ሰኞ ፆሜ
ነኔዌ ይገባል።
✿ ሌሎችን አጽዋማት ተውሳኩን ከነኔዌ(መባጃ ሐመር)
ጋር ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን እናገኛለን።
❖ ዓብይ ፆም = ተውሳኩ 14 ነው
= 14 + ነኔዌ = 16, ስሆን ዘንድሮ በዘመነ ዮሐንስ ዓብይ
ጾም በየካቲት 16 ሰኞ ይገባል፡፡
❖ ደብረ ዘይት = ተውሳኩ 11 ነው
= 11 + ነኔዌ = 13, ይሆናል፡፡ 13 ከ 30 ስለሚያንስና
በየካቲት ስላለፍን በመጋቢት 13 እሁድ ደብረዘይት
ይሆናል።
❖ ሆሣዕና = ተውሳኩ 2 ነው
= 2+ነኔዌ = 4, ስሆን ከ30 ስለሚያንስና በመጋቢት
ስላለፍን በሚያዝያ 4 እሁድ በዓለ ሆሣዕና ይውላል።
❖ ስቅለት = ተውሳኩ 7
=7 + ነኔዌ = 9, ስሆን በሚያዝያ 9 ዓርብ ስቅለት
ይሆናል፡፡
❖ ትንሣኤ = ተውሳኩ 9 ነው
= 9 + ነኔዌ = 11, ስሆን ሚያዝያ 11 እሁድ በዓለ
ትንሣኤ ይውላል።
❖ ርክበ ካህናት = ተውሳኩ 3 ነው
= 3 + ነኔዌ = 5 , ስሆን በግንቦት 5 ረቡዕ ርክበ ካህናት
ይሆናል።
❖ ዕርገት = ተውሳኩ 18 ነው
= 18 + ነኔዌ = 20, ስሆን ግንቦት 20 ሐሙስ በዓለ
ዕርገት ይሆናል።
❖ጰራቅሊጦስ = ተውሳኩ 28 ነው
= 28 + ነኔዌ = 30 ስለዚህ ግንቦት 30 እሁድ በዓለ
ጰራቅሊጦስ ይውላል።
❖ ፆመ ሐዋርያት = ተውሳኩ 29 ነው
= 29 + ነኔዌ = 31, በ30 ገድፍን ቀሪው 1 ስሆን ሰኔ 1
ሰኞ የሐዋርያት ፆም ይገባል።
❖ ፆመ ድህነት = ተውሳኩ 1 ነው
= 1 + ነኔዌ = 3, በመሆኑም ጾመ ድህነት(የረቡዕና
ዓርብ ፆም) ሰኔ 3 ረቡዕ ይገባል።
መልካም ዘመን ያድርግልን ።
Post Top Ad
Responsive Ads Here
Thursday, September 5, 2019
Post Bottom Ad
Author Details
Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized to deliver best result for your blog.