በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በግብረሰዶማውያን ግብኝት ተቃውሞ መግለጫ !!!! - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, June 5, 2019

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በግብረሰዶማውያን ግብኝት ተቃውሞ መግለጫ !!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ለሚደረገው የግብረሰዶማውያን ግብኝት ተቃውሞ መግለጫ !!!!

ግብረ ሰዶማዊነት በክርስትና፣ በእስልምናና በመንግሥት ዘንድ ያለውን አንድምታ እናያለን። በእኛ ሀገር ያለውን ሁኔታ ባላውቅም በምዕራቡ ዓለም ፕሮቴስታንቲዝምና ግብረሰዶማዊነት የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታዎች ናቸው! ግብረ ሰዶማውያኑ "...ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ ግን አንሰርዝም" እንዳሉ ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል። የኾነ የመንግስት አካል ድጋፍ ባይሰጣቸው ኖሮ በልበ ሙሉነት ይኽን አይናገሩም ነበር። የተማመኑበት ነገር ሳይኖር እንዲህ አይሉም። ስለዚህ ጥያቄያችንና ተቃውሟችን ስለግብረ ሰዶማውያኑ ወደ አገራችን መምጣት አለመምጣት ብቻ አይደለም። የመንግሥትንም አቋም መፈተሽ ግዴታ ይሆንብናል።
እንዴት የፌዴራል ፖሊስ "ግብረ ሰዶማውያኑን እኛ እናጅባቸው" ብሎ የአማራን ክልል ሊጠይቅ ቻለ???
ግብረ ሰዶማውያኑ ቅዱስ ላሊበላንና ሌሎችንም ቅዱሳት ቦታዎች ለመጎብኘት ፕሮግራም የያዙት ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር እንደሆነ የአማራ ክልል የደህንነት ቢሮ ሓላፊው ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በመግለጫቸው አሳውቀዋል። የፌዴራሉ መንግሥት የአማራን ክልል የደህንነት ቢሮ ለጎብኝዎቹ አስፈላጊ የሆነ የደህንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው የጠየቀ ሲሆን የቢሮው ሀላፊ ጀነራል አሳምነው ፅጌ በበኩላቸው የግረሰዶም አባላት በክልሉ ለሚያደርጉት ጉብኝት ጥበቃ እንደማይሰጥ እና የፌዴራል ፖሊስም ላቀረው እኛ እንጀባቸው ጥያቄ ክልሉ ለፌዴራል ፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እውቅና እንደማይሰጥ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ለፌዴራል ፖሊስ መልስ ሰጠዋል። በመግለጫውም እንዳሉት «የግረሰዶም አባላት በአማራ ክልል የቅዱስ ላልይበላ እጅግ የተከበሩ መንፈሳዊ ስፍራዎችን ለመጎብኘት ከፌደራሉ መንግስት ጋር በመነጋገር በያዙት ፕሮግራም የአማራ ክልል ጸጥታ ዘርፍ ጥበቃ እንደማንሰጥና የፌዴራል ፖሊስም ላቀረበው እኛ እንጀባቸው ጥያቄ ለፌዴራል ፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እውቅና እንደማንሰጥ በጥብቅ እናስታውቃለን።» ብለዋል።
ስለዚህ መንግሥት በግብረ ሶዶማውያኑ ጉብኝት ላይ ግልጽ የሆነ አቋሙን ሊያሳውቅ ይገባል!!!
ወደኃላም ሄደን መንግሥት ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ያደረገውን ነገር ለማስታወስ እንገደዳለን። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ሚኒስቴር በነበሩበት ጊዜ በሀገራችን በተዘጋጀና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትንሹ ቡሽ በተሳተፈበት የዓለም አቀፍ የጤና ጉባኤ በተካሄደ ጊዜ የሃይማኖት አባቶች ግብረሰዶማዊነትንና በሀገራችን የተካሄደውን የእነርሱን ስብሰባ ለማውገዝ እንዳይሰበሰቡ ለምን በፌዴራልና በደህንነት ሰዎች ተከለከሉ???
በዚያን ጊዜ (በ2003 ዓ.ም) ግብረ ሶዶማውያኑ ካሳንችስ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ የራሳቸውን ጉባኤ ሊያደርጉ አቅደው የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ጉባኤያቸውን በተባበሩት መንግሥታት ECA የስብሰባ አዳራሽ አድርገዋል።
ይህ እንዳይደረግ በወቅቱ የነበረው የሃይማኖቶች ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ውይይት በማድረግ ጠንከር ያለ የተቃውሞ የአቋም መግለጫ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም የሃይማኖት መሪዎቹ እዛው ሳይበተኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ በደህንነቶች ታጅቦ ፈጥኖ በመድረስ "....ሀገራችንን እርዳታ ያሳጣታል ከአሜሪካ ጋር ያጣላናል" በሚል ዛቻና ማስፈራራት ተጽእኖ መግለጫው ሳይተላለፍ እንደቀረ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው።
በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ማኅበራት የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይወጣ በደህንነት አካላት ከፍተኛ ወከባ ሲደረግ እንደነበር አንረሳውም። ለዚህ ነው አሁንም መንግሥት በግብረሶዶማውያን ጉብኝት ላይ ግልጽ አቋሙን ሊያሳውቅ ይገባል የምንለው።
ወደ መነሻ ሀሳቤ ልመለስና በእኛ ሀገር ያለውን ሁኔታ ባላውቅም በምዕራባውያን ፕሮቴስታንቲዝምና ግብረሰዶማዊነት የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታዎች መሆናቸውን በማስረጃ እንመልከት:-
ዓለምአቀፋዊውን እውነታና አሐዝ መሠረት አድርገን አንድ ነገር በእርግጠኝነት እንናገራለን-ግብረሰዶማዊነትን በዓለም ላይ ያስፋፋው ፕሮቴስታንቲዝም ነው።
አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ግብረሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ ስፔን፣ ጀርመን፣ ቼክ ሪፐብ ሊክ፣ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣ ኢጣሊያ፣ ግሪክ፣ ፖላንድ የመሳሰሉ አገራት ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ በሌላው ዓለም ስናይ አሜሪካ፣ አርጀን ቲና፣ ቺሊ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል፣ ቬንዙ ዌላ፣ አውስትራሊያ፣ ፊሊፒንስና ጃፓን ደጋፊ አገራት ናቸው፡፡
ግብረ ሰዶማ ዊነትን በሕግ ከፈቀዱ አገራት መካከል ደግሞ፡- አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላ ንድ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ካናዳ፣ ቤልጂ የም፣ አውስትራሊያና ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን በመቃወም ኢትዮጵያ ከናይጀሪያ ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡
በእነዚህ አገራት የሚገኙ እና ወንጌልን እንስበክላችሁ የሚሉን የካቶሊ ክና የፕሮቴስታንት ቸርቾች ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ የሚያጠፋ መሆኑን የሚናገረውን የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት እያስተማሩ ግብረ ሰዶ ማዊነትን በዐዋጅ ተቀብለዋል፡፡ በክርስትና ስም የሚጠሩ “አብያተ ክርስቲ ያናት” የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ኀጢአት ወይም የሥነ ምግባር ግድፈት አድርገው አያዩትም፡፡ እንዲያ ውም ግንኙነቱን በመባረክ እንደ ጋብቻ እየቆጠሩት ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን ፈቅደው በቸርቾቻቸው ወንድን ከወንድ፣ ሴትን ከሴት እያጋቡ ነው፡፡ ወንጌል ገልጠው እያስተማሩ፣ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን እያሉ ግብረ ሰዶማውያንን በመቅደሳቸው አቁመው የሚያጋቡ የእምነት ድርጅቶች ስለ መኖራቸው ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኙ የፕሮ ቴስታንት “አብያተ ክርስቲያናት” ጠቅላይ ሲኖዶስ ግብረ ሰዶማውያን ጋብ ቻቸውን “በቤተ ክርስቲያን” ውስጥ እንዲፈጽሙ 94 በመቶ በሆነ ድምፅ አሳልፏል፡፡
“የአብያተ ክርስቲያናቱ” መሪ ሲኖዶሳቸው ወደፊት እያንዳንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይህን የግብረ ሰዶማውያን ጋብቻ በማጽደቅ ፍላጎታቸው ከሆነ ባርኮ ለማጋባት መንገዱ ተከፍቷል ብለዋል፡፡ የስኮትላንድ ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን” ደግሞ ተመሳሳይ ጾታ ካላቸው ተጋቢዎች መካከል ዲያቆናትንና ካህናትን መሾም የሚቻልበትን ሕግ አጽድቃለች፡፡ በስዊድን የሚገኘው የፕሮቴስታንት “አብያተ ክርስቲ ያናት ሲኖዶስ” የግብረ ሰዶማውያንን ጋብቻ ለመባረክ በ2012 ውሳኔ ሲያስተላልፍ፣ የዴንማርክ “ሲኖዶስ” በበኩሉ እያንዳንዱ የፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” ይህን ጋብቻ መፈጸም ግዴታው እንደሆነ በመግለጽ ውሳኔውን በሥሩ ላሉ “አብያተ ክርስቲያናት” አስተላልፏል፡፡ የኖርዌይ ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያንም” ከዴንማርክ ቀጥሎ ተመሳሳይ ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
በአጠቃላይ የካናዳ የተባበሩት “ቤተ ክርስቲያን” (the United Church of Canada)፣ የክርስቶስ የተባበሩት “ቤተ ክርስቲያን” (The United Church of Christ)፣ የጀርመን ሉተራን “አብያተ ክርስቲያናት” (all German Lutheran)፣ የኢኬዲ ተሐድሶና የተባበሩት “አብያተ ክርስቲያናት” (refor med and united churches in EKD)፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ “አብያተ ክርስቲያናት” (all Swiss reform ed churches)፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Protestant Church in the Netherlands)፣ የቤልጂየም የተባበሩት ፕሮ ቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Uni ted Protestant Church in Belgium)፣ የፈረንሣይ የተባበሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Unit ed Protestant Church of France)፣ የዴንማርክ “ቤተ ክርስቲያን” (the Church of Denmark)፣ የስዊድን “ቤተ ክርስቲያን” (the Church of Sweden)፣ የአይስላንድ “ቤተ ክርስቲያን” (The Church of Iceland)፣ የኖርዌይ “ቤተ ክርስቲያን” (the Church of Norway)፣ የፊንላንድ ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን” (The Eva ngelical Lutheran Church of Finland)፣ የሜትሮፖሊታን ኅብረት “ቤተ ክር ስቲያን” (The Metropolitan Community Church)፣ የሐዋርያት ጴንጤ ቆስታል አጋዥ ዓለም አቀፋዊ ኅብ ረት (The Global Alliance of Affirming Apostolic Pentecostals (GAAAP)) ግብረ ሰዶማዊ ነትን ያጸደቁና ግብረ ሰዶማውያንን በጸሎት የሚያጋቡ “አብያተ ክርስቲ ያናት” ናቸው፡፡
በአሜሪካም “ዩናይትድ ቸርች ኦፍ ክራይስት” የተባለው ቡድን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 2005 ላይ ግብረ ሰዶማዊነትን በይፋ ተቀብለዋል፡፡ ለአንድ ሚልዮን ሦስት መቶ ሺሕ ለሚኾኑ ተከታዮቻቸውም “ጥንዶችን በጾታቸው ምክንያት አድልዎ አታድርጉባቸው” ሲሉ ግብረ ሰዶምን ባርከዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወንድም ለሴትም ግብረ ሰዶማውያን ክህነት የሰጡ “አብያተ ክርስቲያናት” ደግሞ፡- የስኮትላንድ፣ የእንግሊዝ፣ የዌልስ፣ የስዊድን፣ የኖርዌይ፣ የዴንማርክና የአይስላንድ “አብያተ ክርስቲያናት”፣ የፊንላንድ ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የጀርመን ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን”፣ የቤልጂየም የተባበሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን”፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ “ቤተ ክርስቲያን”፣ የፈረንሣይ የተባበሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲ ያን”፣ የካናዳ ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የካናዳ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ የጥንቷ ካቶሊክ “ቤተ ክርስቲያን” እና የጃፓን የተባበሩት የክርስቶስ “ቤተ ክርስቲያን” ናቸው፡፡
ግብረ ሰዶም በክርስትናው የሞት ቅጣት የሚያስከትል እጅግ
ከባድ ኃጢአት ነው። ግብረሰዶምን የጀመሩት የሰዶም እና የገሞራ ሕዝቦች ናቸው። እግዚአብሔር ሎጥን ከምድራቸው አስወጥቶ ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን በእሳት እንደቀጣቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፏል ዘፍ 19።
"ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።" ዘሌ 20፡13።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እነዚህን እርኩሶች "ሞት ይገባቸዋል" ብሏል። ሮሜ 1፡32
የከበሩ ሐዋርያትም በዲድስቅልያ አንቀጽ 32 ቁጥር 218-219 ላይ "ሞትን ይሙቱ" ብለዋል።
♦ ግብረ ሰዶም በእስልምናም ከባድ ኃጢአት ነው። ይኽንንም ቁርአኑና ሐዲሱ በግልጽ ይናገራሉ።
ሱረቱ አል-አዕራፍ 7:80-84 ግብረ ሰዶም በፈጸሙት በኖኅ ዘመን ሰዎች ላይ የእሳት ዝናብ እንደዘነበባቸው ይናገራል። እንዲሁም ቀጥሎ ባሉት የቁርአን ጥቅሶች ላይ በግብረ ሰዶም ምክንያት ሰዎች እንደተቀጡ ተጽፏል፡- ሱረቱ አል-ሹራ 26:165-166 ፣ ሱረቱ አል-ነምል 27:54-56፣ ሱረቱ አል-አንከቡት 29:28-29፣
በሐዲሱም በግልጽ ተጽፎ እንደሚገኘው በእነ መሐመድ ዘመን
ግብረ ሰዶም ይፈጽሙ የነበሩ ሰዎች በሞት እንዲቀጡ የሙስሊሞቹ ነቢይ መሐመድ አዘዋል። Sunan Abu Dawud 38:4447።
በሌላኛው የአቡ ዳውድ ሐዲስ ላይ እንደተዘገበው ግብረሰዶም ሲፈጽም የተያያዘ ሰው በድንጋይ ተወግሮ እንዲገድል ታዟል።
Narated By Abdullah ibn Abbas: "If a man who is not married is seized committing sodomy, he will be stoned to death." Sunan Abu Dawud 38:4448
ሌላው ቢቀር አንድ ወንድ የሌላኛውን ወንድ ልዩ አካሉን እንዲሁም አንዲት ሴት የሌላኛዋን ሴት ልዩ አካሏን በዓይናቸው እንኳን ማየት አይችሉም። Narrated AbuSa'id al-Khudri: The Prophet said "man should not look at the private parts of another man, and a woman should not look at the private parts of another woman." Sunan Abu Dawud 31:4007 and 4008።
በቡኻሪ ሐዲስም ላይ እንደተጻፈው ሴታሴት መሳይ ወንድን ከቤት አውጥተው እንዲያባርሩት ነቢያቸው መሐመድ አዘዋል። Sahih Bukhari 7:72:774 & 8:82:820።
♦ ♦ ♦
ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያውያን ዘንድ በሃይማኖታችን ከባድ ኃጢአት ነው፤ በባሕላችን እጅግ አፀያፊ ነገር ነው፤ በማኅበረሰባችን እጅግ አሳፋሪና ነውር ነው፤ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ 6/29 መሠረትም ግብረ ሰዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። ስለዚህ ምንም ዓይነት አግባብነት ከሌለው መንግሥት በግብረሰዶማውያን ላይ ከሕዝቡ የተለየ አቋም መያዝ በፍጹም አይችልም። እደግመዋለሁ አይችልም! ባለሥልጣናቱ በግላቸው መደገፍ መሳተፍም መብታቸው ነው-የሕዝቡን መንፈሳዊና ሞራላዊ እሴት ብሎም የሀገሪቱን የወንጀል ሕግ የማክበር ግዴታ ግን አለባቸው። ደግሞም በሀገራችን ሕግ መሠረት የሚያስቀጣ እስከሆነ ድረስ ወደ ሀገራችን መግባታቸው በራሱ ወንጀል ማለት ነውና ስለዚህ ለግብረ ሰዶማውያኑ ቪዛ የፈቀደው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሕግ ጥሰት ሊጠየቅ ይገባዋል።
እንደ CDC/ center for Disease control/ ያሉ ዓለም ዐቀፍ የበሽታ መቈጣጠሪያ ማዕከላት ግብረ ሰዶማዊነት እና ሌዝቢያንነት የሚያስከትላቸውን አስከፊ የጤና ጠንቆች በሳይንሳዊ ጥናቶቻቸው ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከእነዚኽ ውስጥ፡-
1. የፊንጢጣ ነቀርሳ (ካንሰር)
2. የአንጀት ነቀርሳ
3. ፊስቱላ
4. ኪንታሮት
5. የጡት ካንሰር
6. የጒረሮ ቂጥኝ
7. የፊንጢጣ ቂጥኝ
8. መካንነት
9. ኤች አይ ቪ ኤድስ
10. በሱስ ውስጥ ተጠምዶ ራስን ማጥፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ስለዚህ መንግሥት ሆዬ! እንደኢትዮጵያዊነት መንፈሳዊነቱ እንዲሁም የሕዝቡን ሞራላዊ እሴትና ስብዕና መጠበቁ እንኳን ቢቀር ቢያንስ ሕዝቡን ለከፋ በሽታና ለከባድ የጤና ችግር አሳልፎ የሚሰጠውን ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወም ግድ ይልሃል።
ማሳሰቢያ፡- በመጨረሻም ለወደፊቱም ቢሆን ኦርቶዶክሳውያንና ሙስሊሞች ሁላችን ኢትዮጵያውያን፣ አቋሙ ከታወቀ መንግሥትም እነዚህን ጥያቄዎች የግድ መመለስ ይኖርብናል:- ግብረሰዶማውያኑ አሁን ላይ ፕሮግራም ይዘው አዋጅ አውጀው "እንመጣለን" ስላሉን ሁላችንም በቁጣ እየተቃወምን ነው። ግብረሰዶማውያኑ ለወደፊቱ ድምፃቸውን እያጠፉ ወደ ቅድስት ሀገራችን ቢገቡስ እንዴት ማወቅና መከላከል እንችላለን?
ከውጭ ስለሚመጡት ብቻም ሳይሆን አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ግብረሰዶማውያን ምን እናድርግ?
ግብረ ሰዶማዊነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋትም ሆነ ለመከላከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት እንደትልቅ ተቋምነታቸው የራሳቸውን ሥራ መሥራት አለባቸው። ኦርቶዶክሳውያን እና ሙስሊሙ ምእመናንንና ማኅበራት በጋራ ይህንን ሰይጣናዊ ተግባር በይፋና በአዋጅ በነቂስ መቃወም አለብን። የፕሮቴስታንቱ ዓለም እንደሆነ ፍጻሜው ራሱ ግብረሰዶማዊነት ነው። እስከዚያው ድረስ በአምልኮት ሰበብ በእርኩሰታቸው ምድሪቷን እያረከሱ ይቆያሉ እንጂ ፍጻሜያቸው ግብረሰዶማዊነትና አምልኮተ ሰይጣን ነው።
የኢትዮጵያ አምላክ ያጥፋችሁ አቦ።
የቅዱሳን አባቶችንና የቅዱሳት እናቶቻችን ጸሎት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሚገኘውን የዲዮቅልጥያኖስን መንፈስ ያጥፋልን።
ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት  ፌስ ቡክ የተጻፈ

Post Bottom Ad