ቅዱስ እንድራኒቆስ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, May 29, 2019

ቅዱስ እንድራኒቆስ

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+
Image may contain: 2 people, people standing =>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ
ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ
ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር
ደምሮ አስተምሮታል::
+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት
ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር::
ይሕ የተፈጸመ ገና
መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)
+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10
ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ
ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን
ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት
አምላኩን
አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ
መልዕክቱ
16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::
+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ
ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል
አብርተዋል:: እጅግ ብዙ
መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው
ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት
ቤቶችን አፍርሰው
አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::
+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን
ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን
አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር
ገንዞ ቀብሮታል::
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+
=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ
የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር
የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ
ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ
ገስጾታል:: በዚህም
ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል::
እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት
ቀስፎታል::
❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ
ክብራቸውን ያድለን::
❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ
++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ:
ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Post Bottom Ad