ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Thursday, May 9, 2019

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

By Memhir Cherinet Yigrem
===========================

የመከራ ጨለማ ያጠላበትን የሰው ልጅ ሕይወት ፍጹም ብርሃን የሆነውን የአለም ብርሃንን የምትወልደው እርሷ የምትጎበኝ የጎህ/ የነግህ ብርሃን ሆና በሊባኖስ ተራራ ተወለደች
ዓለምን የሸፈነውን ጨለማ በዘላለም ብርሃን የሚያበራውን ፀሐይን ትወልድ ዘንድ እንደ ፀሐይ እያበራች እንደ ከዋክብት ደምቃ ጨረቃ ተወለደች።
በሊባኖስ ተራራ በ፭ሺህ ፭መቶ ፹፭ ዓመተ ዓለም የመወለዳዷን ዜና ሲሰሙ የጨለማ አበጋዞች ዲያብሎስና ሠራዊቱ ደነገጡ አለቅነታቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶ ምርኮን የሚማርከውን ኃይልን ንጉሥ የምትወልደው በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለችና፣
ጠቢቡ ሰሎሞንም የመወለዷን ዜና በትንቢት መነጽር አይቶ መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎህ ሰናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሐይ ፣ ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ እንደ ጨረቃ ውብ እንደ ከዋክብት ብሩህ እንደ ፀሐይም የደመቀች ማን ናት? አለ
የአዳምና የልጆቹን በመርገም ኃጢአት የጠፋ ውበት የምትመልስ ውብና ንጽሕት በቅድስናዋ በንጽሕናዋ የደመቀች ምትክ ተወልዳለችና አዳም ከደይን ሲኦል ሆኖ ሐሴት አደረገ፣
ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ይፈስ የነበረው ደስታ ከሰው ልጆች በመርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ምክንያት ጠፍቶ ነበርና ፣ ይህን ደስታ ዳግም የምታሰጥ ሙሐዘ ፍስሐ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለችና መላእክት በሰማይ ተደሰቱ፣
ሰዶምን እንዳንሆን ገሞራን እንዳንመስል ዘር ያስቀርልናል ፣ እግዚአብሔርን በመተማመንም ፣ከእሴይ ግንድ ቁጥቋጥ ይወጣል ፣ ብለው ትንቢት የተናገሩ ነቢያት የቆጠሩት ሱባኤያቸው ደርሷልና ከሊባኖስ ተራራ ድንግል ስትወለድ አበው ነቢያት ከአርያም ሐሴት አደረጉ፣

Post Bottom Ad