ጠቃሚ ባህላዊ መድሃኒቶች (ክፍል አንድ) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Thursday, May 16, 2019

ጠቃሚ ባህላዊ መድሃኒቶች (ክፍል አንድ)1. #ጤና አዳም፡-ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ መታወክ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ህመሞች መድሃኒትነው፡፡
2. #ዳማከሴ፦ ለጉንፋን፣ ለመተንፈሻ ቧንቧ ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
3. #ሬት( Aloe vera )ሲሆን ቅርፊቱ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ የማር ወለላ የመሰለው ነገር ከሌላ ምግብ ጋር አዋህዶ በመምታት መመገብ የከሱ ሰዎችን ውፍረት ይጨምራል ፡፡ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው፡፡ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደሻይ አፍልተው ቢጠጡት የመፈወስ አቅም አለው።
4. # አርማ ፦ጉሳ አረንጓዴው ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው ደግሞ ቅጠሉ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ሀይልና የምግብ አፒታይት የመክፈት ሀይል አለው ፡፡
5.#ነጭ-ሽንኩርት/ Garlic ፡-ለደም ዝውውር፣ለጨጓራ ፣ለውስጥ ካንሰር፣ለመተንፈሻ አካል ፣ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ አባቶች አብነት በመጥቀስ ይናገራሉ፡፡
6. #የኮክ ዛፍ ቅጠል/peach tree ፡- የጋማና የቀንድ ከብቶች በድንገት ሲታመሙም ሆነ ሰዎች በድንገተኛ በሽታ ሲያዙ ከጤና አዳም ጋር ተወቅጦና ተጨምቆ ሲጠጡት ከህመማቸው ይፈወሳሉ፡፡
7. # ግራዋ/-Vernonia amygdalina ቀን ተመርጦ 7 ቅጠሉ ተቀንጥሶ በሰው እጅ መድሃኒት ለበላ ሰው ቢያጠጡት የመፈወስ ሀይል አለው፡፡
8.#ጨለስ/አባርየ/ሁረታ/፡- የሚባል እንጨት በእርሻ፣ በአጥርና በቤት በር ቢያኖሩት አራሺ/ሰላቢ/ በንብረት ላይ ጥፋት የማድረስ አቅም ያሳጣዋል፡፡
9. #የነጭ ባህርዛፍ ቅጠሉ/ Eculaptus tree ፡- ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነት ፈውስ ያገኛል፡፡
10. #ቀይ ሽንኩርት/ Onion ፡- ለአጠቃላይ ጤንነትና ለደም ዝውውር ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር የዘር ፈሳሽ እጥረት ላጋጠማቸው ሰዎች በብዛት ለማመንጨት እንደሚያገለግል አባቶች ይናገራሉ፡፡
11.#ዞጓራጋጅ፡- የሚባል ቅጠል በእንጨት የሚጠመጠም ሆኖ እንደ አሚቾ ስር የሚያኮርት ሲሆን ይኸው ስሩ ትክትክ ለያዘቸው ህፃናትና ወባ ለያዛቸው ሰዎች አገልግሎት እንደሚውል አባቶች ይናገራሉ፡፡
12. #የጣይበተረ/ኦምሮ፡- ሴቶች በወሊድ ወቅት የፈሰሳቸውን ደም ለመተካትና በወር አበባ ጊዜ ተቀቅሎ እንዲጠጡት ይደረጋል፡፡ ይህ መድሃኒት የቅጠላቅጠል ዝርያ ሲሆን ለወለደች ሴትና የወር አበባ ያየች ሴት ከአንድ ሣምንት ላላነሰ ጊዜ እየተቀቀለ እንዲጠጡት ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም ቁርጠትን ይከላከላል፣ሆድ ያጥባል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡
13. #እንስላል /Dill :- ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል፡፡
14. #የፉር ጌተረ፡- ህፃናት ግግ ሲወጣባቸው ታሽቶ ሲቀባ ያጠፋዋል፡፡
15. #የምድር እምቧይ ስሩ /አሚቾው/፡- ተወቅጦ የታመሙ ከብቶች እንዲጠጡት ሲደረግ ከብቶቹ ይድናሉ፡፡
16. #መቅመቆ/ Rumex abyssinicus ፦ የተባለ ተክል ስሩ ተወቅጦ እንዲደርቅ በማድረግ ዱቄቱ 2 ወይም 3 በሻይ ማንኪያ በውሃ በማፍላት እንዳሻይ ቢጠጣ የደም ግፊት ይቀንሳል፡፡
17. #የእንጆሪ ቅጠል/ berry leaf :- በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል፡፡
18# ፌጦ፦ ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል፡፡
19.#ቀበርቾ /ቾሳ/ Echinops kebericho :- ከስራ ስር ክፍል የሚመደብ ሲሆን አገልግሎቱም ለድንገተኛ ህመም ፣ውጋት ወዘተ በማኘክ የሚወሰድ ፈዋሽ መድሃኒት ነው፡፡
20. ጋሳይ ካሳይ በባአል የሃገራችን ሰዎች ስጋ ሲያስገቡ መጀመረያ በቀትርጫቱ ካሳይ ያንጥፉንና ስጋው እዛ ላይ ከሆነ ስጋው የበላው ሰው ብስንና ብስንና አይለውም ግሳቱ የስጋ ህመም አይሰማውም ሆድም አይነካውም ግሳቱ የስጋ ህመም የነካው የካሳይ እንጨት ያኝክንና ከምራቁጋ ይዋጥ ወዳው ሆዱ ሲደርስ በ1 ከቂቃ ይተወዋል ።
እንናተም ከእነዚህ ውጭ ሌሎችን ያሉ ባህላዊ ግን ጠቃሚ መድሃኒቶች አካፍሉን።

Post Bottom Ad