☞ከበዙ ተአምራቱ አንዱን፡-
=>ጻድቁ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት::
+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::
+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::
+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::
+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ::
=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
<<< በበዓሉም (ግንቦት 19 ቀን) ጐንደር በሚገኘው ቤተ መቅደሳቸው ተገኝተን እናክብራቸው ! >>>
<<< ከጻድቁ በረከት አይለየን !! >>>
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞