ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ/የጥያቄ ቀን/ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Thursday, May 16, 2019

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ/የጥያቄ ቀን/




                   
          ለምን የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል
  
ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ-መቅደስ ምክንያት፣ በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ; ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ; የሚል ነበር፡፡ (ማቴ.21፤23-27፣ ማር.11፤27-30፤ ሉቃ.20፤1-8)





 እርሱም መልሶ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ከሰማይን; ወይስ ከሰው; አላቸው፤ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምሕርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡ ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባ ነው፡፡
            በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፤ የትምህርት ቀንም ይባላል፤ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፤ መክሮ መመለስእንደሚገባንሲገልጽልንነው፡፡(በማቴ.21፤23-27፣ማር.12፤2-13፤37፣ ሉቃ. 20፤9፣ 21፤38) የሚገኘው ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሙን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበት ይገባዋል፡፡

Post Bottom Ad