የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ አጭር ደሰሳ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Sunday, September 2, 2018

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ አጭር ደሰሳ



1.  ከአገር አንድነት፣ነጻናትና ክብር
ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት ጎን ተሰልፋ በየዘመኑ የተነሱ እንደ ቱርክ ፣ግብጽና ኢጣሊያን የመሳሰሉት የሃገር ወራሪዎችን ድል አድርጎ በማባረር ፣ታቦት ይዛ ከህዝብ ጋር በመዝመት ፣በጸሎት፣በሞራልና በመሳሰሉት ነገሮች ጭምር ከፍተኛ ድጋፍ ማድረግ ለድሉ መገኘት ጉልህ ድርሻ ነበራት፡፡ምሳሌ፤- የአድዋ ድል እና የአቡነ ጴጥሮስ ንግግር እንዲሁም አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ባንደራችን ምንጫ ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
2.  በአስተዳዳር ሕግና ውጭ ግንኙነት
ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ታሪክ ድረስ በኢትዮጵያ የነገሱ ልየ ልዩ ነስታታት መንፈሳዊ ትምህርትና በጎ ሥነ ምግባርን ከቤተ ክርስቲያን ስለተማሩ አገር መሪዎችን ከማፍራት አኳያ ትልቅ አስተዋጸኦ አበርክታለች፡፡
ዘመናዊ ህግ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት 1923 ዓ/ም ከመርቀቁ በፊት ሀገርን ይመራ የነበረው የቤተ ክርስቲያኒቱ መጽሐፍ በሆነው ፍትሐ ነገሥት ነበር፡፡
በየዘመናቱ የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው ወደ ውጭ የሚላኩ መልዕክተኞች በአብዛኛው የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ስለነበሩ፡፡በኢየሩሳሌም ያሏት ቅዱሳት መካናት ውጭ ግንኙነት ውጤቶች ናቸው፡፡ለዚህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡
3.  በትምህርትና በጤናው ዘርፍ
    ዘመናዊ ትምህርት በሀገራችን ከመስፋፈቱ በፊት ሥርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት ለቤተ ክህነቱም ሆነ ለቤተ መንግስቱ የሚሰማሩ ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን በማፍራት እንደ ዩኒቨርስቲ ያገለገለች ይህች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ምሳሌ፤ - አጼ ላሊበላ ፣አጼ ቴዎደሮስ፣አለቃ ገብረ ሐና፣አራት አይና ሊቀ ሊቃውንት መንክር ፣ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ወ.ዘ.ተ
     በጤናውም ዘርፍ በእምነቱ፣በጸበሉ ፣በምስጢረ ቀንዲሉ ለህሙማን ፈውስን ሰጥታለች እየሰጠችም ትገኛለች፡፡
4.  በባህልና ማኅበራዊ ኑሮ
የብዙ ኢትዮጵያውያኖች  የአመጋገብ ፣አለባባስ፣የጨዋታ እና የመሳሰሉት ባህላዊ እሴቶች በእንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት፣ሥርዓትና ትውፊት ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ምሳሌ፤- እንግዳ መቀበል፣አብሮ መብላት፣በሐዘንና ደስታ ጊዜ መጠያቅ፣መረዳዳት ወ.ዘ.ተ
5.  በኪነ ጥበብ ዘርፍ
5.1.          በሥነ ጽሁፍ ዘርፍ
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፊደል ቀርጻ፣ቀለም በጥብጣ፣ብራና ዳምጣ፣ብዕር ቀርጻ  የጽሁፍ ጥበብን እና የሥነ ጽሁፍ ውጤቶችን ለትውልድ ያበረከተች ከፍተኛ የአገር ባለውለታ ናት፡፡
ምሳሌ፤-
Ø አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ለግዕዝ ፊደላት አናባቢ በመፍጠር፣መንፈሳዊ መጽሀፍትን ከግሪክ ወደ ግዕዝ መተርጎማቸው
Ø ከዓለም የሌለ የመጽሐፈ ሄኖክ መጽሀፍ ባለቤት መሆኗ
Ø የቅዱስ ያሬድ አምስቱ ጸዋትዎ የዜማ መጻሕፍት
Ø የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልዩ ልዩ መጻሕፍት
Ø ልዩ ልዩ ብራና መጻሕፍት
በዚህም ረገድ እንደ ብላቴ ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ፣አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣መንግስቱ ለማ፣ሀዲስ አለማየሁ ወ.ዘ.ተ ቤተ ክርስቲያን ያፈራቻቸው እውቅ የሥነ ጽሁፍ ምሁራን ናቸው፡፡

5.2.           በሥነ ሥዕል
አገራችን በሚገኙ ልዩ ልዩ ገዳማትና አድባራት  የአብያተ ክርስቲያናቱ  ግድግዳዎች እና ጥንታዊ የብራና መጽሐፍት ገጾች ላይ በድንቅ ሁኔታ ተስለው የሚገኙ ሥዕሎች በኢትዮጵያ የሥዕል ጥበብ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑን ያመለክታሉ፡፤
ከሥዕል ጥበብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀላማትን በተለያየ ነገር ቀምማ በማዘጋጀት ፣ለመቀቢያና ለመሳያ የሚገለግሉ የተለያዩ ነገሮች በመሥራት ለትውልድ ያቆያቸው መሰረታዊ ዕውቀትም ሊታወስ የሚገባው ነው፡፡
5.3.          በሥነ ህንጻ
የምህንድስና ትምህርት ባልነበረበትና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልዳበረበት በጥንታውያኑ  የአክሱም ፣የዛጉዌ እና የጎንደር መንግስታት ዘመን አገራችን የተሰሩ ህንጻዎች ዓለምን ያስደነቁና ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ናቸው፡፡ ምሳሴ፤- ላሊበላ፣ፋሲል ግንብ ወ.ዘ.ተ
ከሥነ ሥዕልና ከሥነ ሕንጻ ጥበባት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን  ከብረታ ብረት ፣ከሸክላ እና ከእንጨት የተሰሩ እንደ መስቀል፣ጌጣጌጦች እና ልዩ ልዩ የመገልገያ ዕቃዎቸን ከእነ አሰራርና ጥበባቸው ለትውልድ ማቆየቷ ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ዐቢይ ጉዳይ ነው፡፡
6.  በቅርስና ቱሪዝም
      የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን አቅፋ የያዘች መንፈሳዊት ተቋም ናት፡፡ከሚዳሰሱ የቤተ ክርስቲያኗ ቅርሶች መካከል የውቅርና የዋሻ ውስጥ አብያተ ክርስቲያናት፣የመቃብር ቦታዎች የመታሰቢያ ሀውልች፣አብያተ መንግስታት፣የብራና መጻሕፍት፣መስቀሎች፣ስዕሎች፣አልባሳት፣ዘውዶች፣ጥንታዊ መገልገያ ዕቃዎች፣መዝሙር መሳሪዎች/ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያ/ እና ሌሎች ንዋያተ ቅዱሳት ይገኙበታል፡፡
    ከማይዳሰሱ የቤተ ክርስቲያኗ ቅርሶች የሚመደቡ ደግሞ ያሬዳዊ ዜማ፣ማህሌትና የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ፣የመንፈሳዊ በዓላት አከባበር፣ገዳማዊ ህይወት፣የአብነት ትምህርት ቤቶች ፣ሥርዓተ ትምህርትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
   ከላይ የተጠቀሱት ቅርሶች የቱሪዝም መስህቦች በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ይዞታ ስር ስለሚገኙ ቤተ ክርስቲያኗ በቱሪዝም ሀብት ክምችት በሀገራችን የቀዳሚነት ስፍራ እንዲኖራት አድርጓል፡፡
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ማዕከል ብቻ ሳትሆን ምጣኔ ሀብት፣ማህበራዊ፤ .ታሪካዊ፣ ስነ ጥበባዊ እና መሳሰሉት ጠቀሜታ ያላቸው የበርካታ ቅርሶች ባለቤት በመሆኗ በቱሪዝም ዘርፍ ለሀገራችን ያላት አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑ በሚገባ እንገነዘባለን፡፡

Post Bottom Ad