በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው ጥፋት - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Friday, August 31, 2018

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው ጥፋት



የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጭም በተነሡ ኃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ጥፋትና ዘረፋ ደርሶባታል፡፡ከውጭ ከመጡ ኃይሎችም ደግሞ የእንግሊዞች፣ደርቦሾችና ፈሽሽት ኢጣሊያን  ጥፋቶች ተወዳዳሪ አይገኝላቸውም፡፡
እንግሊዝ፤- እንግሊዞች ከአንድ ሺ ሦስተ መቶ በላይ የሚሆኑ የብራና መጻሕፍትን ከመቅደላ እንደወሰዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሆኖም ግን በተለያዩ ምክንያቶች ቅረሶቹ ተዘረክርከው በመቅረታቸው በአሁኑ ሰዓት 400 ያህል ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ክብረ ነገስት መጽሐፍ፣ታቦታት፣ቅዱሳት ሥዕላት፣የአጤ ቴዎድሮስ ከበሮ፣የአቡነ ሰላማ መስቀል፣ዋንጫ ፣ከወቅር የተሰሩ ሁለት ጽዋዎች ፣የወርቅ የእንገት መስቀሎች ወ.ዘ.ተ ተወስደዋል፡፡
ድርቦሾች፤- ድርቡሾች የእንግሊዝና የግብጽን የጋራ አገዛዝ በመቃወም ሱዳን ውስጥ ከተነሳው የማኀዲስቶች እንቅስቃሴ አካል ነው፡፡ድርቡሾች በወቅቱ ሱዳን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግብጻውያንን መካራ አጽንተውባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ በኩል አድርገው ግብጻውያን ወደ ሀገራቸው እንዲገቡና እንግሊዞች የያዟቸውን የኢትዮጵያ ግዛቶችን ለመመለስ በአጼ ዮሐንስ አማካንነት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ስምምነቱም የሕይወት ስምምነት ይባላል፡፡ ኢትዮጵ ስምምነቱን አክብራ ግብጻውንን ወደ ሀገራቸው ማሻገር ስትችል እንግሊዝ ስምምነቱን ሳታከበር እንደውም ምጽዋን በኢጣሊያ እንዲያዝ አድርጋለች፡፡ በዚህ ምክንያት ድርቡሾች በጣም ተናደው በተለይም 1879 እስከ 1880 ድረስ በጎጃምና ጎንደርን በመውረር አብያተ ክርስቲያናትን፣ገዳማትንና ካህናትን በውስጣቸው የሚገኙ በርካታ ቅርሶችን አቃጥለዋል፡፡አፄ ዮሐንስም በመተማ ጦርነት ከነዚህ ማህዲስሶች ጋር ሲዋጉ እንደሞቱ ይታወቃል፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ፤- ኢጣሊያን በአጤ ሚኒልክ በአድዋ ጦርነት ውርደት ከተከናነበ በኋላ በ1928 ዓ/ም ሌላ ጦርነት በኢትዮጵያውን ላይ አውጇል፡፡በዚህም ጊዜ የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያንና ሃይማኖቷን ለማጥፋት የነበራትን የልብ ፍላጎት አጋጣሚውን በመጠቀም በግልጽ መሳሪያ በማስታጠቅና ‹‹ በመባረክ›› የጥፋት ተልዕኮ ዋና አቀንቃኝ ነበረች፡፡
ኢጣሊያ በነበራት የአምስተ ዓመት የጥፋት ዘመቻ ቤተ ክርስቲያን ደምታለች፣ቆስላለች፣ተዘርፋለች፡፡ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ አድባራትና ገደማት ተቃጥለዋል፡፡ በዝቋላ፣በላሊበላ፣በጎንደር፣በአክሱም ፣በደብረ ሊባኖስ ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች በጣም በርካታ መነኮሳት ፣ካህናትና ምእመናን በግፍ ተጨፍጭፈዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ብቻ በአንድ ቀን ወደ አምስት መቶ የሚደርሱ መነኮሳት መረሸናቸው ተዘግቧል፡፡በምዕራብ ኢትዮጵያ የጎሬው ሊቀጳጳስ አቡነ ሚካኤልና የወሎው ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ተገድለዋል፡፡
አክሱም ሐውልትና የይሁዳ አንበሳ ምንም ቢመለሱም ለብዙ ዓመታት ከሀገራችን ተወስደው የነበሩ ቅረሶች ናቸው፡፡
አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ የኢትዮጵያ መሬት ለኢጣሊያ እንዳይገዙ በማለት በአደባባይ በማውገዛቸው ፋሽስቶቹ በመትረየስ መሐል አዲስ አበባ ላይ ገድለዋቸዋል፡፡
ፋሽስት በአገራችን ለአምስት አመታት በቆዩባው ጊዜያት ሴተኛ አዳሪነት፣ሌብነት፣ሱሰኝነት፣ቁማርተኝነትና የመሳሰሉት ማህበራዊ ቀውሶች እንዲስፋፉና በርካታ መንፈሳዊ ዕሴቶቻቸን እንዲዳካሙ ምክንያት ሆኗል፡፡
ሚስዮናውያን በኢትዮጵያ
ሚስዮናውያን የምነላቸው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሀገራቸን በመግባት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ሲተናኮሎ የነበሩ የካቶሊክ ፣ፕሮቴስታንትና የመሳሰሉት የእምነት ድርጅቶች መልዕክተኞች ናቸው፡፡እነዚህ ሚስዮናውያን በተለያየ ጊዜ  ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጡ ምክንያት የነበሩ ሦስት ጉዳዮች ናቸው፡፡
1.  በመጀምሪያው የመስቀል ጦርነት ጊዜ ተደጋጋሚ ሽንፈት የገጠማቸው ምዕራባውያን ካቶሊኮች ሙስሊሞች ለማሸነፍ በሐሳባቸው የፈጠሩትን የሕንዱን ቄስ ንጉስ ዮሐንስን ፍለጋ መጀመራቸውን ይህንንም ሐሳብ የፈጠሩት ሰው ከኢትዮጵያ ጋር በመዛመዳቸው
2.  ኢትዮጵያውያን ነገስታት በውስጥና በውጭ የሚያስቸግራቸውን የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመግታተት የዘመናዊ መሳሪያና ሌሎች ድጋፍ በመፈለጋቸው
3.  ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ የቴክኖሎጅ ስራዎችን የሚያሰተዋውቁ የጥበበኞችና የጥበብ እድ ባለሙያዎችን መፈለጋቸው ናቸው፡፡
ካቶሊክ ሚስዮናውያን ለረዥም ዘመናት የነበራቸው ምኞች ለጊዜው እውን የሆነው በአጼ ሱስንዮስ ዘመን ነበር፡፡በዚህ ጊዜ በትግራይ፣በላስታ፣በበጌ ምድር በጎጃምና በሽዋ ያሉ ሊቃውንት ደንቀዝ እየሄዱ ‹‹ሰማዕትነት አያምልጣችሁ›› እያሉ በሱስንዮስ አደባባይ ከስምንት ሺ በላይ ህዝብ ረግፏል፡፡ ከሚስዮናውየን አንዱ አልፎንዙ ሜንዴዝ ለሁለት ኢትዮጵውያን እንዳስተማራቸው የሚነገረው ቅባትና ፀጋ የተባሉ ሁለት እምነቶች ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ዓይነተኛ ምክንያት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡
      ንጉስ ሱስንዮስ በነገሱ በ28ዓመታቸው 1625ዓ/ም ሞቱ፡፡
      ልጃቸው አጼ ፋሲለደስም ‹‹ኦርቶዶክስ ትመለስ የካቶሊክ እምነት ትርከስ›› ብለው ሃይማኖትን መልሰው ፣ካቶሊኮችን አባረዋል፡፡
      ቢሆንም ካቶሊክ ሚስዮናውያን ግን በሊቃውንቱ ላይ ቀላል የማይባል የሃይማኖት ጥርጣሬ ፈጥረዋል፡፡
በአጠቃላይ ሚስዮናውያን በተለያዩ ጊዜ የነገስታቱን ደካማ ጎን በማጥናት ኢትዮጵያን ለማበጣበጥና በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበርም፡፡ዓላማቸው ግን በኢትዮጵያውያን ሀገር ወዳድነትና ለሃይማኖት ተጋዳይነት ሊሳካ አልቻለም፡፡
ራስን የመቻል ትግል እና ስኬት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በግብፅ/እስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ለ1600ዓመታት ያህል በሞግዚትነት አስተዳደር ሥር እንደነበረች ይታወቃል፡፡
የሁለቱ  አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት የተጀመረው አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን /ፍሬምናጦስ/ በ20ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ አትናቴዎስ ተሹሞ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆኖ ከመጣ ወዲህ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ዘመናት ከግብፅ ጳጳሳትን ለማምጣት የተገደደችበት ምክንያት በ7ኛው መ/ክ/ዘ በሠለስቱ ምእት ስም በኒቅያ ቁባዔ 42ኛው ቀኖና ላይ የተጨመረው የሐሰት ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ እርሱም‹‹ ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሾም ›› የሚል ነው፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ጊዜያት ክግብጽ ጥገኝነት ስር ሁና ከእስክንድርያ ጳጳሳት ስታስመጣ መኖሯ በርካታ ችግሮች አስከትሏል፡፡ጳጳሳቱ፤-
ÿ የኢትዮጵያን ቋንቋና ባህል አለማወቃቸው
ÿ ጳጳሳቱ አንድ ብቻ ስለሆኑ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ተዘዋውረው ማስተማር አለመቻላቸው፤ዲቁናና ቅስና መስጠት አለመቻላቸው፡፡
ከግብጻውያን ጳጳሳት ጋር በተያያዥነት ባላቸው ችግሮች ምክንያት በተፈጠረው አስተዳደራዊ ክፍተት ለመሙላት በመካከለኛው ዘመን የደብረ ሊባኖስ ዕጨጌ ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና አስተዳዳራዊ አገልግሎት ከጳጰሳት ቀጥሎ ሁለተኛው ሰው ነበሩ፡፡
ከአቡነ ተ/ሃይማኖት እስከ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ /አቡነ ባስልዮስ/ ድረስ 59 ያላነሱ እጨጌዎች እንደ ነበሩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የመጨረሻው እጨጌ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊው ፓትርያርክ አቡነ ባስሊዮስ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያውያን ነገስታት በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሾሙ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ጥረቱ ግን የተሳካው በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግስትበ1921ዓ.ም ሲሆን አምስት ኢትዮጵውያን መነኮሳት ጵጵስና ተሸመዋል ፡፡እነርሱም
1.  አቡነ ፊልጶስ
2.  አቡነ ጎርጎሪዮስ
3.  አቡነ ማትያስ
4.  አቡነ አትናትዮስ
5.  አቡነ ሳዊሮስ ናቸው፡፡
1951ዓ/ም አቡነ ባስሊዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ሁነው በ116ኛው የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ተሹመው ለዘመናት የነበረው ራስን የመቻል ትግል በታላቅ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ከብፁእ አቡነ ባስልዮስ በኋላ የተሾሙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮች ሢመት የተፈጸመው አዲስ አበባ ሲሆን እነርሱም ፤-
ÿ አቡነ ቴዎፍሎስ/1963-1967ዓ/ም /
ÿ አቡነ ተክለ ሃይማኖት/1968-1980ዓ/ም /
ÿ አቡነ መርቆሪዎስ/ 1980-1983ዓ/ም/
ÿ አቡነ ጳውሎስ/ 1984-200
ÿ አቡነ ማትያስ/     ጀምሮ/ ናቸው፡፡
6.  በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በድኅረ አብዮት/1966-1983ዓ/ም/
በኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የታሪክ ሂደት መገንዘብ የሚቻለው መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የችግሮች ሁሉ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ መሆኗን ነው፡፡
ፈተናዎች/ችግሮች
ÿ የአቡነ ቴዎፍሎስ በግፍ መገደል
ÿ በመሬት ላራሹ ዐዋጅ ‹‹ የገዳማትና አድባራት መሬት መነጠቋ
ÿ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ ሹመት በመንግስት መሆኑ
ÿ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤቶች መወረሳቸው
ÿ በ1977ዓ/ም በተከሰተው ርሃብ የፕሮቴስታንትና ሌሎች የሃይማኖት ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ፡፡
7.  የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ/ከ1983ዓ/ም ጀመሮ/
አበይት ችግሮች
ÿ የአክራሪ እስላሞች ጥቃትና የመስጊዶች መስፋፋት
ÿ የመናፍቃን ተጽእኖ
ÿ የተሃድሶ መናፍቃን መነሳት
ÿ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች መበተን
ÿ የቅርስ ስርቆትና ቃጠሎ መባባስ
ÿ በአብያተ ክርስቲያናት በሮች ላይ የሚስተዋል ከፍተኛ ልመና እንቅስቃሴ
         በጎ ተጽእኖ
ÿ የማኅበ አገልግሎት
ÿ የሰንበት ት/ቤቶች እድገት
ÿ ስብከተ ወንጌልና በጎ አድራጎት ተግባራት መጠናከር ወ.ዘ.ተ

Post Bottom Ad