ሰበር ዜና:- የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ጉዳይ እንዲያከትም ማኅበረ ደቅስዮስ ከአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር ውይይት አደረጉ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, February 13, 2016

ሰበር ዜና:- የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ጉዳይ እንዲያከትም ማኅበረ ደቅስዮስ ከአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር ውይይት አደረጉ


 • ማኅበረ ደቅስዮስ እና የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት በተሐድሶ ዙሪያ በዲ/ን ያረጋል እና ወ/ሮ ዘውዴ አማካኝነት ውይይት አደረጉ
 •  በኑፋቄ የተጠረጠረው “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ ኑፋቄው በሊቃውንት ሊቀርብ መሆኑን ሲሰማ ጎንደርን ለቆ ወደ አዲስ አበባ መሄዱን ምንጮቻችን ገልጸዋል


(አትሮንስ የካቲት 5 ቀን 2008 ዓ፣ም) በየዓመቱ ታህሳስ 19 ለሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክበረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክብር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ  “መምህር” ፋሲካውንና “ዘማሪ”ዳዊት በቀለ የሚባሉትን ግለሰቦች የተሐድሶ አቀንቃኞች እንደሆኑ ባለመረዳት ማህበረ ደቅስዮስ ጋብዘዋቸው እንደነበር እና ከፍተኛ ውዝግብ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ እና ከመንፈሳዊ ወጣቶች ጋር አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የሚታወስ ነው።  በመሆኑም ማኅበረ ደቅስዮስ ይህን የተሐድሶ ዓላማ ምን እንደሆነ በመረዳት ከማኅበረ ቅዱሳን መምህር ዲ/ን ያረጋል አበጋዝንና ወ/ሮ ዘውዴን በመጋበዝ በደብሩ ለሚገኙ ካህናትና ምዕመናን ስለ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ግንዛቤ እንዲያገኙ አድርገዋል። ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ቀጥሉበት እንላለን።   ማኅበረ ደቅስዮስም ስማችን በሚዲያ ጠፍቷል፤ ተሐድሶ ተብለናል የሚል ጥያቄ አንስተው እንደነበር እና ሰንበት ትምህርት ቤቱም ምላሽ ሲሰጡ ማኅበሩን ተሐድሶ ናችሁ ያላቸው እንደሌለና በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሐድሶ መጠቀሚያ እንደሆኑና የሚገፋፋቸው አካል እንዳለ በማስረጃ አቅርበውላቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለ “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ በኑፋቄ ተጠርጥሮ ከአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መባረር እና የኑፋቄው ጉዳይ በሊቃውንት እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ሳለ ጎንደርን ለቆ መሄዱ ያሳሰባቸው ወንድሞች እና እህቶችም እንዳሉ ምንጮቻችን ያመለክታሉ። ነገር ግን ማኅበረ ደቅስዮስ ስለ አጽራረ ቤተክርስቲያን፤ ተሐድሶ መናፍቃን ጉዳይ ለወደፊቱ ተግቶ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል።  በመጨረሻም ዲያቆን ያረጋል አበጋዝና ወ/ሮ ዘውዴ ለማኅበረ ደቅስዮስ እና ለአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት መገልገያ ይሆናቸው ዘንድ መጻሕፍትን አበርክተውላቸዋል።  ለወደፊቱ ማኅበረ ደቅስዮስ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጋር በመተባበር የተሐድሶን ገመድ ለመቁረጥ መልካም ሥራ እንደሚሰሩ ተስፋ አደርጋለሁ።  
   
የአትሮንስ መልእክት


 • ማንኛውም የተዋሕዶ ልጅ ከጓደኛ ይልቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልናስቀድም ይገባል፤ ከማኅበር ይልቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እናስቀድም ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን
 • ቤተ ክርስቲያን ለሚመጣባት ማንኛውም አደገኛ ፈተና ልናስቀድም ወይም ልንታደጋት የሚገባን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ብቻ ነው እንጂ........ ጓደኛየ ወይም ማኅበሬ ስለሆነ ብሎ ምክንያት እየደረደሩ ቤተ ክርስቲያንን ማስመታት ቢቀር መልካም ነው


 • ማንኛውም መንፈሳዊ ማኅበር የተመሰረተው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል እንደሆነ መርሳት የለብንም።  ቅድሚያ መስጠት ያለብን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብቻ ነው።
 • በታሕሳስ 24 ቀን 2008 ዓ.ም  በዘገብኩት ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተና የተበሳጩ ወንድሞች.......... እኔን ለመደብደብ ከቤቴ ድረስ በመምጣት..... ባለቤቴን በማስፈራራት በዛቻ የተመለሱ ግለሰቦችም ነበሩ፤  በእርግጥ ምንም እንደማያመጡ ባምንም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለተሐድሶ አጫፋሪ መሆን የለብንም ቅድስት ቤተ ክርቲያናችን ትበልጥብናለች። ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ስለሌለ አሁንም አትድከሙ ተሐድሶ ይጥፋ ተዋሕዶ ትለምልም። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን እንዳለ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 24፤15
 • ተሐድሶን እስከ መጨረሻው መዋጋት ቤተ ክርስቲያንን መታደግ ነው ስለዚህ ተግተን ለቤተ ክርስቲያን እንስራ
 • ማኅበሩ በተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የጀመረውን እንዳያቋርጥ 
 • ሰንበት ትምህርት ቤቱ በአንድነት እና በመግባባት ሥራዎችን እንዲሰራ
 • ይህን የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንዲገታ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት የደብሩ አለቃ መልአከ ሃይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ሊመሰገኑና ሊበረታቱ ይገባል
 • በደብሩ ላይ ስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ እና የተሐድሶ መናፍቃንን ሴራ የሚቆጣጠር ኮሚቴ ቢዋቀር የተሻለ ሥራ ይሰራል

Post Bottom Ad