1. የፕሮጀክቱ ር ዕስ - የደብረ ገነት
አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እድሳትና ጥገና ፕሮጀክት
2. የፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ -
01/03/2008 ዓ.ም - 30/02/2010ዓ.ም
3. ፕሮጀክቱ የሚጠይቀው ወጪ -
8,932,731.72 ብር
4. የፕሮጀክቱ ባለቤት - የደብረ ገነት
አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴና የደብሩ ሰበካ ጉባኤ
5. ፕሮጀክቱን በሃላፊነት የሚመራው የሥራ
ሂደት - ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ፤ የደብሩ ሰበካ ጉባኤና የአብከመ ባ/ቱ/ፓ/ል/ቢሮ
6. ለድጋፍ ፕሮጀክቱ የቀረበው - ከተለያዩ
በጎ አድራጊ ድርጅቶች፤ ግለሰቦችና የአካባቢው ም ዕመናን፤ ከፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ፤ ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ከሚመለከታቸው
የመንግስት አካላት
7. የፕሮጀክቱ ዓላማ - የቅርስ ሃብቱን
ከጉዳት መከላከል፤ ማልማትና በመንከባከብ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ
8. የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሥልት
v ለጥገናና እንክብካቤ ፕሮጀክት ዝግጅት
ከሳይቱ መረጃ መሰብሰብ
v የጥገናና የ እንክብካቤ ፕሮጀክት በማዘጋጀት
የበጀት ድጋፍ ማፈላለግ
v አስፈላጊ የጥገናና እንክብካቤ ቁሳቁሶችን
በድጋፍና በግዥ በማሰባሰብ
v አስፈላጊ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሠራተኞችን
በቅጥር (በኮንትራት) በማሰራት
v በሳይት ለሥራው አጋዥ የሆነ አነስተኛ
ወርክ ሾፕ በማዘጋጀት
v ሥራው በቢሮ የዘርፉ ባለሙያዎች እየተመራና
ክትትል በማከናወን
v ለሚመለከታቸው አካላት በየወቅቱ የፋይናንስና
የፊዚካል ሥራ ክንውን ሪፖርት እንዲቀርብ በማድረግ
v አግባብነት ባላቸው አካላት በየወቅቱ
በመስክ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ
v ስለ ጥገናና የእንክብካቤ ሥራ የጽሑፍና
የምስል ሙሉ መረጃ በመሰብሰብና በሰነድ መልክ በማዘጋጀት ለቢሮና ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ
v የጥገናና የ እንክብካቤ ሥራን በማጠናቀቅ
የቅርሱ ባለይዞታ በማስረከብ
ይቆየን...........................