ሰበር ዜና፤ ዋና የተሐድሶ አቀንቃኞች “መምህር” ፋሲካው፤ “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ፤ “ዘማሪ” ዳዊት በቀለ በደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል አውደ ምሕረት ጎንደር በቅሌት ተባረሩ። - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Sunday, January 3, 2016

ሰበር ዜና፤ ዋና የተሐድሶ አቀንቃኞች “መምህር” ፋሲካው፤ “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ፤ “ዘማሪ” ዳዊት በቀለ በደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል አውደ ምሕረት ጎንደር በቅሌት ተባረሩ።

አትሮንስ፤ (ታህሳስ 24 ቀን 2008 ዓ.ም)


ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ.ም ቀንደኛ የተሐድሶ አቀንቃኝ ”መምህር” ፋሲካው እና “ዘማሪ” ዳዊት  ጎንደር ደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብር ኤል ቤተ ክርስቲያን አወደ ምሕረትን  ለመቆጣጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው ተመልሰው በመጡበት አግራቸው ጠንካራ በሆኑት በደብሩ አለቃ፤ በአንጋፋው ሰንበት ትምህርት ቤት እና በጸጥታ ሃላፊዎች ጠንካራ ውሳኔ ተገደው ከአውደ ምሕረቱ እንዲወርዱ ተደርጓል።
  ü እነዚህ አጉራ ዘለል ሰባኪ እና ዘማሪ የመጡት በድብቅ ሲሆን  እስከ ሞት ድረስ ዋጋ እከፍላለሁ ያለላቸው የተሐድሶ አቀንቃኞች እንዲመጡ ጥረት ያደረገው ዘማሪ ታደለ ገድፉ ነው፤
  ü አምጪው ደግሞ በደብሩ የሚገኘው ማኅበር ማህበረ ደቅስዮስ ነው፤
  ü እኒዚህ ሰባኪ እና ዘማሪ ነን የሚሉት ደግሞ የደቅስዮስ ማኅበር አባል የሆኑት የዛሬ አመት ነው

ስለዚህ ማኅበሩን አንጋፋው ሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዲጠረጥረው ያደርገዋል።  በበዓሉ ዕለት እነዚህ የተሐድሶ አቀንቃኞች አጉራ ዘለል “ሰባኪ” ፋሲካውና  “ዘማሪ” ዳዊት በቀለ በማናለብኝነት አውደ ምህረቱ ላይ በመውጣት  ታቦቱ እስኪወጣ ድረስ በማለት እየዘመረ በነበረበት ወቅት
Ø የደብሩ አለቃ መልአከ ሃይል አባ ገብረ እግዚአብሔር “እነዚህ የተሐድሶ አቀንቃኞች ከአውደ ምሕረቱ ካልወረዱ ታቦቱን አላወጣም” በማለታቸው እና
Ø አንጋፋው የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ከጸጥታ ሃላፊዎች ጋር በመተባበር መምህርና  ዘማሪ ነን የሚሉትን  ፋሲካውንና ዳዊትን ከአውደ ምሕረቱ እንዲወርዱ አድርጓል።
Ø  “መምህር” ፋሲካውም............ አይ ማኅበረ ቅዱሳን እድሜህን ያሳጥረው እያለ ሲጮህና ሲራገም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ምዕመናን ሰምተው እንዳዘኑበት ምንጮቻችን ገልጸዋል። 
Ø በዕለቱ የነበሩ የቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና ምዕመናን እንዲሁም እማኝ የቤተክርስቲያን ልጆች እንደተናገሩት በስፍራው የነበሩ  ም ዕመናን ምስጋናቸውን ለጸጥታ ሃላፊዎች፤ ለደብሩ አለቃና ለሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
Ø በተጨማሪም እነዚህ የጸጥታ ሃላፊዎች........ በደብሩ ለሚገኙት ለደቅስዮስ ማኅበር ከአሁን በኋላ የዚህ አይነት ድርጊት ስትሰሩ ወይም ያለ ደብሩ ሰበካ ጉባኤ ፈቃድ በዚህ አውደ ምህረት ላይ አንዳች ነገር ቢደረግ ወይም ብንሰማ ወስደን እንዘጋችኋለን እንዳሏቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል።  ማህበሩም ረብሻ ሳያስነሱ እንደተለመደው ሳይደባደቡ  ፖሊስ እንደነገራቸው ያለምንም ረብሻ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል ብለዋል። 
ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።  ተዋሕዶ ትለምልም።  ተሐድሶ ከስር መሰረቱ ይጥፋ።

ምንጮቻችን እንደገለጹት የተሐድሶ ምንፍቅናን  ለማስፋፋት እቅድ ይዘው ለመንቀሳቀስ የተዘጋጁባት(የቅሰጣ) ቦታ በሆነችው ጎንደር በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የተሀድሶ አንቀሳቃሾች በአብነት ትምህርት ቤቶችና ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ በማኅበራትና በተለያዩ ወጣቶች ላይ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም አሁን ለአራተኛ ጊዜ የከሸፈባቸው መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በቀን 22/04/08 ለዓመታዊ የቅዱስ ደቅስዮስ ክበረ በዓል በማኅበረ ደቅስዮስ “ጠሪነት” “ መምህር” ፋሲካውና “ዘማሪ ዳዊት” ደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተሀድሶ ጉባኤ ለማከናወን አስበው ጎንደር ከተማ በድብቅ የገቡ ሲሆን ጉዳዩ በደብሩ የሚገኘው ሰንበት ትምህርት ቤት ከጠንካራው የደብር አስተዳዳሪና የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በመጡበት እግራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል።  

በተደጋጋሚ በደብሩ የሚገለገሉት ምዕመናን እንደገለጹት የእነዚህ የተሐድሶ መናፍቃን፤  ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ማኅበረ ደቅስዮስ ውስጥ ተሰግስገው በደብሩ በተደጋጋሚ የተሐድሶን ዓላማ የሚያስፈጽሙ አካላት እንዳሉ ማሳያ መሆኑን ገልጸው የጸጥታ አካላትም በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውና ማኅበሩን  እየተከታተሉት እንደሆነ......... ሰንበት ትምህርት ቤቱም የቀዳማዊ ደቅስዮስ ማኅበርን በትኩረት እንደሚከታተሉት ታውቋል ብለዋል።

ዓላማቸውም ጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን አዲስ አበባ እንደሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን እናደርገዋለን። መልእክታችንን እንደፈለግን እናስተላልፋለን።  ከዚያም ቀስ በቀስ ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት እንይዛለን የሚል እንደነበር ምንጮቻች ገልጸዋል።  ይህን ሃሳባቸውን በአጭሩ የቀጩት አንጋፋው የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት እና የደብሩ አስተዳዳሪ፤ ሰበካ ጉባኤ ምስጋናችን የላቀ ነው።  በዚህ በተሐድሶ ጉዳይ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጎንደር ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ሰበካ ጉባኤ፤ ለሃገረ ስብከቱና ለመሳሰሉት በግልባጭ መግለጫ አውጥተዋል።  ደስ ይበላችሁ የተዋሕዶ ልጆች።  ድል ለተዋሕዶ።  ተሐድሶ ከስር መሰረቱ ይጥፋ። ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በጎንደር ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ጋር በመተባበር በተሐድሶ ማንነትና የምንፍቅና ሥራዎች ዙርያ ለአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት፤ ካህናት፤ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር፤ ወጣት የማኅበራት አመራር እንዲሁም ለምዕመናን በመ/ነገስት ግምጃ ቤት ማርያም፤ አባጃሌ ተክለሃይማኖት፤ ቀሃ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን፤  ቀዳሜ አድባራት ቅዱስ ጊዮርጊስና በመጨረሻም በመ/መ/መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከታኅሳስ 21 እስከ 24 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ይህንን የተሃድሶ የምንፍቅና ስበት ለማፈራረስ ሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት ለመስራት የጋራ ሥምምነት ላይ ደርሰዋል።  ይህንንም መርሐ ግብር በማቅረብ ዲያቆን  ዶ/ር ያረጋል አበጋዝ፤ ዲያቆን ሄኖክ፤ ወ/ሮ ዘውዴ እና መዘምራን ከአዲስ አበባ ተሳታፊዎች ሆነዋል በማለት ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ከሶስት ሳምንት በፊት ጀምሮ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ጥረት አያደረገ የነበረው አንጋፋው የደብራችን ሰንበት ትምህርት ቤት፤        “አርማጭሆ የሚገኘው ሰበካ ጉባኤ አባላት ለሴቶች ገዳማት መርጃ በሚል ሰበብ በጋሻውን፤ በሪሁንና ምርትነሽን ጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በሃገረ ስብከቱ አስፈቀደው እንደነበርና...... ያስፈቀዱበት ሁኔታ ሲጣራ የተጭበረበረ መሆኑ  ሲጣራ........ የታሰበው ጉባኤ እንዲታገድ ሲደረግ......... የነበረው ውዝግብ ቀላል አልነበረም”።   ሰንበት ትምህርት ቤቱም ይህን ጀሮ ጭው የሚያደርግ ዜናን በመስማታቸው ከደብሩ አለቃ፤ ሰበካ ጉባኤ፤ ሰርክ ጉባኤ ኮሚቴ አባላት እና የደቅስዮስ ማኅበር ጋር እንደተወያዩና ............የደቅስዮስ ማኅበር ለነበጋሻው ጠበቃ ቆመው ሲከራከሩ “ እነ በጋሻው የሚሰብኩበት ፈቃድ አላቸው አያሉ ወረቀት ያሳዩ  እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ምንጮቻችን እንደገለጹት ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤  የታደለ ገድፉ የበገና ተማሪዎች፤ ምዕመናንና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የቅድስት ቤተክርስቲያን መደበኛ መምህራንም ጭምር በበገና ደርዳሪው ላይ ያላቸውን አቤቱታ ደብሩ ለሚገኘው ሰንበት ትምህርት ቤት፤ ለደብሩ አስተዳዳሪ እና ለተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት አቤቱታቸውን አሰምተዋል፤ መረጃም አለን ብለዋል። አቤቱታቸውም.......................
ü በገና እደረድራለሁ
ü ሶስት ካሴቶችንም አዘጋጅቻለሁ፤ ለአራተኛው ካሴት ተራ እየጠበኩ ነው ጨርሻለሁ
ü  በነገረ መለኮት ከቅድስት ሥላሴ ተመርቄአለሁ
ü  ስለዚህ አሁን በጎንደር ከተማ የበገና ትምህርት ከፍቼ አስተምራለሁ፤
ü ልጆቻችሁን አስመዝግቡ
በማለት የገንዘብ ማግኛ ተማሪ ካፈራ በኋላ..... በገና ተምረን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በቅድስና እናገለግላለን ብለው ለተመዘገቡት የዋሀን የተዋሕዶ ልጆች የሚያስተምረው በገናን ሳይሆን የተሐድሶ ኑፋቄ እንደሆነ አብዛኛው ተማሪ  እሮሮውን አሰምቷል።  ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በማቆምና ለደብሩ አለቃ ለመልአከ ሃይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔርና  ለሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች ጥቆማ በማድረጋቸው ጉዳዩ ዕልባት በአስቸኳይ እንዲያገኝ አለበለዚያ
ü ቶች እህቶችችን በአካል ሆነ በሞራል ሌላ ጉዳት ሳይደርስባቸው፤
ü የእምነት መሸርሸር ከመምጣቱ በፊት  ጉዳዩን ትኩረት እንዲሰጥ።
ü  መረጃም አለን ይጠየቅልን የሚሉ ከወንሞችና ከእህቶችም  ጭምር በመገኘታቸው ጉዳዩ እስከ ቤተክህነት ድረስ እንዲሄድ ሆኗል።

 ታደለም ምሽግ አድርጎ ከተቀመጠበት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን እንኳን አስቀድሶ ተሳልሞ እንደማያውቅ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች አባቶች ስለመሰከሩ....... 
በጋሻውንና አሰግድ ሰሀሉን ጎንደር እንዲመጡ ዋና ተዋናይ ሆኖ በመገኘቱ......
የተሐድሶ እንቅስቃሴ ጎንደር ላይ እንዲስፋፋ ከሚያደርጉ አካላት ዋና ሆኖ መገኘቱ..........
ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚሰጠው አገልግሎት የሌለ በመሆኑ (ቅጥረኛ አለመሆኑ).........
በቅድስት ቤተክርስቲያን ያለው የእምነት ጉዳይ አናሳ ሆኖ በመገኘቱ.........
ከቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ እንዲለቅ እና እራሱን ችሎ እንዲኖር የተወሰነ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

የዘማሪ ታደለ ገድፉ የኑፋቄ ጉዳይም በቤተክህነት እንዲታይ ተደርጓል ፤ በሥፍራው የነበሩ የቅድስት ቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች እንደገለጹት፤
Ø በዕለቱ  የጸጥታ ሃላፊዎች፤
Ø የቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ፤
Ø የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤
Ø  የማኅበረ ቅዱሳን አባላት፤
Ø የወጣት ማህበራት፤
Ø “ ታደለ ገድፉን ያስመጣው ማኅበርም(ማኅበረ ደቅስዮስ) የማኅበሩ አመራር፤
Ø የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አመራር፤ ተገኝተው ነበር።

 ይህ ጉዳይ ከመቅረቡ በፊት ሰንበት ትምህርት ቤቱ  ለቤተክህነት ሃላፊዎች እና ለጸጥታ አስከባሪዎች የፖሊስ ሃላፊዎች  መሪው ታደለ እንደሆነና ድርጊቱን ፈጻሚ የደቅስዮስ ማህበር ምክትል ሊቀ መንበር እንደሆነ ለተሰበሰቡት አቤቱታቸውን አቅርበዋል። አቤቱታቸውም 
·        የሰንበት ተማሪዋ በደቅስዮስ ማኅበር ምክትል ሊቀ መንበር ተደብድባለች............
·        የተደበደበችበትም ምክንያት የተሐድሶ መምህራን አይመጡም ደግሞም እኛ ለበዓሉ ወረብ እየተዘጋጀን ስለሆነ ጥናት አለብን በማለቷ  ..........
·        ከዚህ በፊትም ይህ ግለሰብ አንጋፋው የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል  ሰንበት ትምህርት ቤት አመራር ክፍልን በመደብደቡ ታስሮ እንደነበርና ይህ ድርጊት በዚህ ግለሰብ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን አበክረው በዚህ ጉዳይ ላይ ለተሰበሰቡት ምሬታቸውን ገልጸዋል።
·        በዚህ ጉዳይ የተሰበሰቡት ሁሉም አካላት ጉዳዩን ሰምተው  ምክትል ሊቀ መንበሩ ልጅቱን ስለበደላትና ለፈጸመው ስህተህ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተደርጓል። 
·        የጸጥታ ሃላፊዎችም በማስጠንቀቂያ እንዲታለፍና ሌላ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ተገቢ እርምጃ እንደሚወስዱበትም ተናግረዋል ብለዋል።

ምንጮቻችን እንደገለጹት የዘማሪ ታደለ ገድፉ የተከሰሰበት የኑፋቄ ጉዳይ፤
ü ተሐድሶ ኑፋቄ ትምህርት ያሰራጫል፤  
ü እነ በጋሻው፤ ዘርፌ፤ ምርትነሽ የመሳሰሉት የክርስቶስ ምርጥ እቃ እንደሆኑና ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራን  የተዋሕዶ አባቶችን በኑፋቄ እጠራጠራለሁ በማለቱ
ü ቅዱሳንን ያቃልላል፤
ü ከአንድ መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌላ አያስፈልግም፤
ü  የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዋልድ መጽሐፍት በዙ....መጽሐፍቶቹም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ስለሚጋጩ አያስፈልጉም
ü የአብነት ተማሪዎችን እንዲበተኑ ያደርጋል፤
ü ሴቶችን ከነወር አበባቸው ይግቡ ችግር የለም አንዴ በደሙ ድነናል፤ የክርስቶስን ማዳን ያጎድለዋል
ü  ምንኩስና አያስፈልግም፤ ስራ ፈትነት ነው፤
ü ቅድመ ጋብቻ በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም ሃጢአት አይደለም፤...
ü እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት አለ አንጂ መንኩሳችሁ ኑሩ አላለም........ ደግሞም አባ እንጦንስ ስልብ ስለሆነ እንጂ መመንኮስ ፈልጎ አልነበረም...... እርሱም ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ ነበር.......  ተከታዮቹ ግብጻውያን መጽሐፍ ጽፈው ኢትዮጵያ ላኩት.....  የእኛ አባቶች ደግሞ የእምነት መሰረት ስላልነበራቸው......የበሰለ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድ ብስለት የጎደላቸው ስለነበር........ ይህን ተረት ተረት ተቀብለውት ይኸው መላውን ኢትዮጵያ ጥቁር ለብሰው ክርስትናውን ጥቁር አለበሱት የሚሉ እና የመሳሰሉ የምንፍቅና ትምህርቶችን ለሕጻናት እና ለወጣቱ በማስተማሩ ምክንያት ቤተ ክህነት ቀርቦ እንዲጠየቅ ቢደረገም ታደለ ገድፉ  ሊቃውንት ባሉበት እንድንነጋገር ይፈቀድልኝ ከዚህ ያሉት አይመጥኑኝም በማለቱ ጉዳዩ እንዲራዘም ሆኗል ብለዋል ምንጮቻችን። 
የቤተክህነቱም ውሳኔ
                 ማንኛውም ጥርጥር ያለበት ሰባኪ ሆነ ዘማሪ በአውደ ምህረት ላይ     እንዳይሰብክ .....እንዳይዘምር.... ማንኛውም ሰባኬ ወንጌል ያለ ቤተክህነቱ ፈቃድ እንዳይመጣ  የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።

·        ይህ ጉዳይ በእንጥልጥል እያለ” በዘማሪ”ታደለ ገድፉ መሪነት “ በደቅስዮስ ማኅበር”  ጠሪነት ማን ይነካናል በሚል ዛቻ ለተሐድሶ ድብቅ ስራ ሲሰራ የነበረው “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ በዛሬው ዕለት ከቅጥር ግቢው የተባረረ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ።
·        “ዘማሪ” ታደለ ገድፉ በተሐድሶ ተጠርጣሪ የሆኑትን አጉራ ዘለል ሰባኪ እና ዘማሪ በድብቅ (ማንም ሳያውቅ) ከአዲስ አበባ እንዲመጡና ደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ላይ እንዲፈነጩ ለማድረግ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ከዚህ በፊት በቤተ ክህነትና የጸጥታ ክፍል ሃላፊዎች በእነ በጋሻውና በግሩፖቹ ጉዳይ ከላይ እንደተገለጸው በስብሰባው ውሳኔ ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት እነዚህ ግለሰቦች ያለ ቤተክህነቱ ፈቃድ አንዳችም ሰባኪ ይሁን ዘማሪ እንዳይመጡ የተወሰነባቸውን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው......... በማን አለብኝነት ወደ ደብሩ አውደ ምህረት...... በዓሉን ለማክበር ለመጡት ምዕመናን...... ማንንም ሳያስፈቅዱ እንዲዘምር ማድረጋቸው.......... የድፍረታቸውና የጸብ መጫሪያ ምልክታቸው መሆኑን የተገነዘቡት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና የደብሩ ሃላፊ፤ የሰበካ ጉባኤ አባላትም ጭምር ከጸጥታ ሃላፊዎች ጋር በመተባበር ከመድረኩ እንዲወርዱ ተደርጓል። 
ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

  ምዕመኑም በዚህ ጉዳይ በመበሳጨት ቤተክርስቲያናችን እስከ መቼ በተሐድሶ ትተራመሳለች በማለት ያጉረመረሙ ሲሆን በጸጥታ ሃላፊዎች ውሳኔ ደግሞ የተደሰቱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል።         የአብዛኛው ምዕመናን አስተያየትም..............
·        የተሐድሶ አቀንቃኞች ቢመጡም ገንዘባቸውን ከሰሩ እንጂ ምንም ዓይነት ስራ ሳይሰሩ......... በአጭሩ መቀጨታቸውና ያሰቡት ሳይሳካላቸው መቅረቱ ቢያስደስታቸውም......የተሐድሶ ጉዳይ በጎንደር ከተማ ስር ሳይሰድ ብዙ መስራት እንዳለብን እንረዳለን ብለዋል።   
·         በተጨማሪም  በጸጥታ ሃላፊዎች፤ በደብሩ አለቃና በአንጋፋው ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶት ጠንካራ አቋም......እነዚህ ተሐድሶአዊያን ግለሰቦች  ወደ መጡበት ባስቸኳይ እንዲመለሱ በመደረጉ ምዕመኑ እጅግ ደስተኛ እንደሆነም ምንጮቻችን ገልጸዋል። 

በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ጉባኤ  በዲያቆን ሄኖክ.... አማላጅነት..... በሚል ርዕስ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ............ተሐድሶ ምንድን ነው በሚል ርዕስ ደግሞ.......... ዲ/ን ዶ/ር ያረጋል አበጋዝ .......ከመረጃ ጋር ለምዕመናኑ ግንዛቤን በማስጨበጥ እና ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን በትጋት እንዲጠብቁ አስተምረዋል።

ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።  ተዋሕዶ ለዘለዓለም ትኑር።  ተሐድሶ ከስር መሰረቱ ይጥፋ።

Post Bottom Ad