(አትሮንስ፤ ኅዳር 29 ቀን 2008 ዓ.ም) ይህ ሰው እንደሚታወቀው
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዞ የተለየ መናፍቅ ነው። ቤተክርስቲያንን
እናድሳለን ብለው ከተነሱት መናፍቃን መካከል አሸናፊ መኮነን በዋነኛነት
ይጠቀሳል። ብዙም መረጃ ስለተገኘበት ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞታል። በአሁኑ ሰዓት ለብቻው ቤት ለቤት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑትን ምዕመናን
እያሰናከለ የሚገኝ ሲሆን በጋሻው እና አሰግድ ሳህሉን ወደ ጎንደር እንዲሄዱ እና በእርዳታ ሰበብ አስመስሎ የአብነት ትምህርት ቤቶችን እና ጉባኤ ቤቶችን ለመበከል
ጥረት እንዳደረጉ የሚታወስ ነው። በመሆኑም በበጋሻው እና በአሰግድ
ሳህሉ መሪነት ታቅዶ የተዘጋጀው ሴራ ጎንደር በሚገኙ ጠንካራ ምዕመናን እና ማህበራት፤ ሰንበት ተማሪዎች እንደከሸፈ ይታወቃል። ይህ ዕቅድ እንዳልሰራ የተረዱት ተሐድሶዎች እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለመሞከር
ዝግጅታቸውን አጠናክረው በመናፍቁ አሸናፊ መኮንን መሪነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት መናፍቁ አሸናፊ መኮንን በጎንደር ቀሃ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን
አጥቢያ አካባቢ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እንደሚታወቀው የተሐድሶ ዓላማ
የአብነት ትምህርት ቤቶችንና የጉባኤ ቤቶችን ምንጭ ማድረቅ ስለሆነ የተዋሕዶ ልጆች አሁን ካለፈው የበለጠ ርብርብ ልናደርግ ይገባናል። ተሐድሶዎች በጎንድር ላይ ዘመቻቸውን እያፏፏሙ ይገኛሉ። ቤት ለቤት እየዞሩ እያሰናከሉም ናቸው። ደጋፊዎችም .......... “ጎንደር ላይ ስራ ከሰራን ሌላው ቀላል ነው” እንሰራለን እያሉ እያስወሩ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት በየቤተክርስቲያኑ ደጋፊዎችን እያፈሩ ስለሆነ ምዕመናን፤ መንፈሳዊ
ማኅበራት እና ሰንበት ተማሪዎች በአንድ ላይ ሆነን የመጣብንን የቤተክርስቲያን ፈተና በጋራ እንወጣ። በመላው ጎንደር የሚገኙ አቢያተ
ክርስቲያናት አለቆች እና ስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች በሙሉ፤ ከቅድስት ቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ስለ ተሐድሶ መናፍቃን ማንነት
እንዲነገርና ም ዕመናን በቂ ግንዛቤ አግኝተው ተግተው ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንዲጠብቁ ማድረግ አለብን። ይህ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው። እኛም ዝም ብለን አንመለከትም ስለዚህ
መናፍቃንን ከቤተክርስቲያን ጠራርገን ለማስወጣት ተገተን እንስራ።
የአትሮንስ መልዕክት
ይህ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ በዓለም ያላችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች፤ አባቶች ሁላችንም ተረባርበን ተሐድሶን ከቤተክርስቲያናችን ጠራርገን ማስወጣት አለብን ለዚህም
v
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን
መምህሮቻችን
v
በቲዎሎጂ የተመረቃችሁ መምህሮቻችን
v
በዝማሬ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እያገለገላችሁ
የምትገኙ ወንድሞቻችን እህቶቻችን
v
በማኅበር እያገለገላችሁ ያላችሁ መምህሮቻችን
v
ምዕመናን፤ ሁሉም መንፈሳዊ ማኅበራት፤
አጠቃላይ ሰንበት ትምህርት ቤቶች
አንድ በመሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ እልባት እንዲያገኝ
ጉዳዩን ማሳሰብ ብቻ ሳይሆን ውሳኔና መፍትሔ እንዲያገኝ መጠየቅ አለብን። ያለበለዚያ በተሐድሶ ምክንያት ብዙዎች ምዕመናንን እያጣን
እንደሆን ልናውቅ ይገባል።
በየጊዜው ከቅድስት ቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ስለ ተሐድሶ መናፍቃን
ማንነት እንዲነገር እና ምዕመናን ግንዛቤ እንዲያገኙ እና ቤተክርስቲያናቸውን ተግተው እንዲጠብቁ ማድረግ አለብን።
ጎንደር የመጡበት ምክንያት ዋና ዓላማቸው፤ ጎንደር የሚገኙትን
የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ጉባኤ ቤቶችን በእርዳታ ሰበብ ሰርጎ ለመግባት አቅደው ነው። ቢሆንም እኛ ልንነቃ ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይለናል ንቁ በሃይማኖት ቁሙ፤ ጎልምሱ፤ ጠንክሩ
1ኛ ቆሮ 16፤13
የቅዱሳን አምላክ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን።