አንተ ኢየሱስ ክርስቶስን ማን ትለዋለህ? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Tuesday, December 29, 2015

አንተ ኢየሱስ ክርስቶስን ማን ትለዋለህ?

 
 
- አምላኬ ትለዋለህ፤ ነገር ግን ፈቃዱን ለማድረግ ራስህን ሰጥተሃልን?
- ጌታየ ትለዋለህ፤ ነገር ግን በህይወትህ ሁሉ ትገዛለታለህን?
- ንጉሴ ትለዋለህ፤ ነገር ግን ለቅዱስ ቃሉ ትገዛለታለህን?
- አባቴ ትለዋለህ፤ ነገር ግን እንደ ልጁ ትቀርበዋለህን?
- እረኛየ ትለዋለህ፤ ነገር ግን ከበጎች ጋር በበረት አለህን?
- መመኪያየ ትለዋለህ፤ ነገር ግን በመከራ ጊዜ በእርሱ ታምነሃልን?
- መድሃኒቴ ትለዋለህ፤ ነገር ግን በፍጹም ንስሐ ነፅተህ ወደ ስጋ ወደሙ ቀርበሃልን?
- አለኝታየ ትለዋለህ፤ ነገር ግን በ እርሱ አለኝታነት ታምነህ ተገኝተሃልን?
                                              ተው ተመለስ !!!
 
 
በአንድ ወቅት ሌቦች ወደ አንድ ባህታዊ መጡና እኛ የመጣነው ያለህን ሃብት በሙሉ ልንወስድብህ ነው አሉት:: እሳቸውም " ልጆቼ የፈለጋችሁትን ያህል ውሰዱ" አላቸው:: በበዓቱ ያለውን ሁሉ ይዘው ከሄዱ በኋላ አረጋዊው መነኩሴ ባህታዊ አንዲት ነገር ቀርታ ስላየ ያችን እቃ ይዞ በፍጥነት ተሎ ተሎ በመራመድ ከደረሰባቸው በኋላ ጠርቶ ይህችንን እቃ እረስታችሁት ነበርና ውሰዷት ለአንድ ጉዳይም ትሆናችኋለች ብሎ እቃዋን ሰጣቸው:: በዚህን ጊዜ ሌቦቹ በባህታዊው ትዕግስትን ጽናት ተደንቀው የወሰዱትን ሁሉ መልሰው በነበረበት ካስቀመጡ በኋላ በ እውነት ይህ ሰው የ እግዚአብሔር ሰው ነው ተባብለው ተጸጽተው ንስሐ ገቡ:: ማቴ 5:38-42 ሮሜ 12: 16 እና 21
 
ከቅዱሳን ጸሎት ያሳትፈን በረከታቸውም ይደርብን አሜን::

Post Bottom Ad