ሃይማኖተ አበው አንድምታ ንባቡና ትርጓሜ (በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር ) ክፍል አንድ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Monday, November 9, 2015

ሃይማኖተ አበው አንድምታ ንባቡና ትርጓሜ (በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር ) ክፍል አንድ

(አትሮንስ ጥቅምት  27 ቀን 2007 ዓ.ም) ሰበር ዜና፦ የሃይማኖተ አበው አንድምታ ትርጓሜ መጽሐፍ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ታተመ።
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ
ሃይማኖተ አበው አንድምታ
(በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር )
ክፍል አንድ
መቅድመ ኩሉ ንሰብክ ስላሴ ዕሩየ ዘውእቶሙ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ----(ሃይማኖተ አበው 60፤2)
ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ የመጣው አንድምታ ንባቡና ትርጓሜ

  አዘጋጅ፤  ሊቀ ሊቃውንት መንክር መኮነን የአራቱ ጉባኤ ምስክርና መምህር
አሳታሚ፡ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክርና መምህር የጎንደር መንበረ መንግስት መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
ዋጋ፤ 600 ብር
የገጽ ብዛት፤ 1044
ክብደት፤ 2.6 ግራም

ቅዳሜ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ ሃይማኖተ አበው አንድምታ የተሰኘውን መጽሐፍ ምርቃት እንዲታደሙ ጥሪ የተደረገላቸው በመንበረ መንግስት መድሃኔዓለም አዳራሽ መሰብሰብ የጀመሩት እንግዶች ማለትም ከአዲስ አበባ የመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፤ የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት አለቆች፤ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እንደየ ማዕረጋቸው፤ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረ፤ የቤተክርስቲያን  ምዕመናን እናቶች፤ አባቶች እና የቆሎ ተማሪዎች፤ ወጣቶች ከትንሽ እስከ ትልቅ ቦታ እስኪጠብ ድረስ ሞልቶ ነበር።  ከአዳራሹ ውጭም በበሩና በመስኮቶቹ አካባቢ በታዳሚ ተጨናንቆ ውሏል።
የመጽሐፉ ምርቃት ፕሮግራም በጸሎት ከጀመረ በኋላ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በሊቀሊቃውንት ዕዝራ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር ተደርጓል።

 የዕለቱ ፕሮግራም መሪም መኖሪያውን አዲስ አበባ ያደረገ ነገር ግን ዕድገቱ በመንበረ መንግስት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በዲቁና እና በሰንበት ትምህርት ቤት ሲያገለግል የነበረ ዲያቆን አበራ ነበር።

                                               ዲያቆን አበራ የመርሐ ግብሩ መሪ
በዕለቱ ስለ ሃይማኖት አበው መጽሐፍ ምንነት ያቀረቡልን መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ እና ስለ መጽሐፉ ይዘት ትንታኔያቸውን  ያቀረቡልን መጋቤ ሐዲስ አብርሃም አድማሴ በተጨማሪም ስለ መጽሐፉ ሪፖርት ያቀረቡልን አባታችን ቀሲስ ፍቅረ ማርያም ናቸው።  ከአዲስ አበባ በመጡ እና ከጉባኤ ቤቱ የተማሩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቅኔ አቅርበዋል። የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረም ስለ መጽሐፉ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ 50 መጽሐፍ በመግዛት በጎንደር ከተማ ለሚገኘው ላይብራሪ እንደሚሰጡ እና መጽሐፉን ገዝተው ማንበብ ለማይችሉ ነገር ግን ላይብራሪ ሄደው እንዲያነቡ እና ስለ ሃይማኖታቸው የጠለቀ እውቀት እንዲይዙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የሃገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅም እንዲሁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።መጽሐፉ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድምታ ቢዘጋጅም አድንቆ ዝም ማለት ሳይሆን ብዙ ድካም የፈሰሰበት መሆኑን ገልጸው መጽሐፉን ገዝተን ብናነብ እና እውቀት ብንሸምትበት የአዘጋጁ ታላቅ ደስታ ይሆናል እንዲሁም ሌሎች መጻሕፍትንም እንዲያዘጋጁ ያበረታታቸዋል።  ከዚህ በፊትም ትንቢተ ኢሳይያስ አንድምታ መጽሐፍ ያዘጋጁ ሲሆን አሁንም ሌሎች መጽሐፍትን በአንድምታ አዘጋጅተው እንድንጠቀምበት ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስም በርቱልን አደራ አላለሁ ብለዋል።
የመጽሐፉ ደራሲ ሊቀ ሊቃውንት መንክር መኮንን የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር ሲሆኑ እኒህ  አባት ብዙ መጽሐፍትን ጽፈው ለሕዝብ ማቅረብ ፍላጎታቸው የነበረ ሲሆን  የጻፉትን መጽሐፍት ለሕትመት ሳይበቃላቸው እና ፍላጎታቸው ሳይሟላ እግዚአብሔር ጠርቷቸው ሄደዋል። ነገር ግን የመንፈስ ልጃቸው ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለሕትመት እንዲበቃ የተቻላቸውን ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው አሁን መጽሐፉን አሳትመው ለንባብ አብቅተውታል።
በመጽሐፉ ምርቃት በታደሙ ሊቃውንት የቀረቡ መርሐ ግብሮችሪፖርት፦  ከዚህ ጉባኤ ቤት ተምረው በወጡት በመምህር ፍቅረ ማርያም ቀርቧል
v  ቅኔ፤-   መጋቤ ሐዲስ ምስጢሩ ዘለቀ (ከአዲስ አበባ የመጡ)
          መጋቤ ብሉይ አእምሮ ብሩ (አዲስ አበባ አዲሱ ሚካኤል የመጽሐፍ መምህር)
          መምህር ትህትና ተስፋየ (በመንበረ መንግስት መድሃኔዓለም የጉባኤ ቤት ተማሪ)
          ሊቀ ኅሩያን ነቅዓ ጥበብ እሸቴ (የአቡን ቤት ቅዱስ ገብር ኤል ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህር)
v  የመጽሐፉን ይዘት (መጽሐፉን በተመለከተ) አቅራቢ፤ መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ
v  የመጽሐፉን ታሪክ አመጣጥ አቅራቢ፤ መጋቤ ሐዲስ አብርሃም አድማሴ፤

ከላይ የቀረቡ መርሐ ግብሮች ዝርዝር በክፍል ሁለት የሚቀርቡ ይሆናል።

ስለ ሃይማኖተ አበው አንድምታ ትርጓሜ መጽሐፍት የተሰጡ አስተያየቶች

                                              የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረ

·         ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ታላቅ ከመሆኗ የተነሳ ለኢትዮጵያ ያደረገችው አስተዋጽኦ በጣም ሰፊ ነው፤ ባለውለታም ናት
·         ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ለኢትዮጵያ አንድነቷን፤ ክብሯን፤ ልዕልናዋን ትውፊቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረገችው አስተዋጽኦ ታላቅና የማይረሳ ጉዳይ ነው። ባለውለታ ለመሆኗ ታሪክን ወደ ኋላ ማንበብ ተገቢ ነው።
·         ለኢትዮጵያ መሰረት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማንቶታችን ናት ልንጠብቃት ይገባል ይህንን የመሰለ መጽሐፍት ገዝቶ አንብቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የእኛ ሃላፊነት ነው
·         መጽሐፉን ገዝተን ማንበብ ቀላል ነው ከባዱ ነገር ግን ለትውልድ የምናስተላልፈው ነው ስለዚህ እኔ በበኩሌ ለሕዝብ ላይብራሪ የሚውል 50 መጽሐፍቶችን ገዝቼ እሰጣለሁ ምክንያቱም ይህን መጽሐፍ መግዛት የማይችሉ ብዙ አሉ ነገር ግን ሄደው ላይብራሪ እንዲጠቀሙ እና ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የአባቶቻቸውን ሃይማኖት ምን እንደሚመስል የተጻፈ መጽሐፍ በመሆኑ ላይብራሪ ሄደው እንዲያነቡ ሃላፊነቴን እወጣለሁ እናንተም እንዲሁ ብታደርጉ ሃይማኖታችን ጠበቅን ማለት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
·          የግብጽ ፓትርያርክ ጎንደር መጥተው በነበረበት ወቅት ጎንደር ማለት የክርስቶስ ከተማ ማለት ናት ብለው የተናገሩትን ምሳሌ በማድረግ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። በተጨማሪም እኛ እዚሁ ተወልደን፤ እዚሁ አድገን የማናውቀውን ታሪክ እኒህ ፓትርያርክ በመጡ ወቅት የተማርኩት ብዙ ነገር አለ እና ክርስትናችን እንጠቀምበት ብለዋል
·         የግዕዝ ቋንቋ ለመማር በርትተን እንሥራ ወጣቱን እንዲያስተምሩ አባቶች ተግተው እንዲሰሩ እስተያየቴን እገልጻለሁ
·         የተመረቀው መጽሐፍ ለየት የሚያደርገው
1)     ምስጢርን ማወቅ ለፈለገ
2)    አንድምታ መጽሐፍትን ማንበብ ልምድ እንዲኖረው
3)    በአጠቃላይ ሥለ እምነታችን አባቶቻችን የጻፉትን በአንድምታ ተተርጉሞ መቅረቡ
4)    እንዲሁም ሌሎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ከአባታችን ከሊቀሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክርና መምህር ተምረው ሌሎች መጻሕፍትን በአንድምታ እየተረጎሙ እንዲያዘጋጁ እና ድርሻቸውን እንዲወጡ ስል እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ አደራየን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አ ዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ

·         ግኖቲስቲክስ የተሳሳተ መጽሐፍ በመጻፍ በቅዱሳን ሥም እያስመሰሉ ቤተክርስቲያንን ለመበረዝ ጥረት ቢያደርጉም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ትክክለኛውን ትምህርት በጽሑፍ ለማስተላለፍ 300 ዓመት ፈጅቶባቸዋል
·         ሊቀ ሊቃውንት ዶ/ር አየለ ዓለሙ ከዋክብት አድርገው ያፈሯቸው እንደ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ አይነቱን በማፍራት ለትውልድ መጽሐፍ እንዲተላለፍ ማድረግ ምንኛ መታደል ነው።
·         በእነዚህ አይነት ታላላቅ አባቶች ታላቅ ነገር ተደረገልን እኛስ እነዚህን አባቶቻችንን እና ጉባኤ ቤቶቻችንን እንዴት መርዳት አለብን ብለን ማሰብ አለብን።  ማሰብ ብቻ አይበቃም በድርጊት መፈጸም የአንድ ክርስቲያን ግዴታ ነው።እኛም እነዚህን አባቶቻችንን እና ጉባኤ ቤቱን በረዳን ቁጥር ሃይማኖታችን እያደገች ትመጣለሽ ስለዚህ በርትተን እንስራ።
እልፍኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሕይወት
·         እግዚአብሔር የሚገለጽበት ጊዜ አለ ስለዚህ ይህ ሃሳብ በሊቀ ሊቃውንት መንክር ተጸንሶ በልጃቸው በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ተወልዷል።እኔም ባለሁበት ቤተ ክርስቲያን እንድንጠቀምበት እገዛለሁ።  ለሊቀሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስም  እግዚአብሔር ሰፊ እድሜ እንዲያድላቸው እንጸልይላቸው፤ የማቱሳላን እድሜ ያድልልኝ ብለዋል።
የመንበረ መንግስት መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ
·         ብዙ ምዕመናን ገዝተው ለገዳማት እና ለአብያተ ክርስቲያናት የሰጡ ብዙዎች እንደሆኑ እናውቃለን።
·         እኛም ሰበካ ጉባኤው በእኒህ ታላቅ አባት የተዘጋጀውን 10 መጽሐፍት ገዝተን ለገዳማት እናበረክታለን ብለዋል።

አጠቃላይ የታዳሚው አስተያየት
v  እንደዚህ አይነት ላሉ አባቶች እድሜ እና ጤን እየተመኘን፤ በገንዘብም፤ በጸሎትም ጉባኤ ቤቱን ለመርዳት ቃል እንገባለን።
v  ሪውን ዘመን ደግሞ በሌሎች ስራዎቻቸው እንደምናገኛቸው ተስፋ እናደርጋለን።
v  ዚህ የታደሙት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህርን ፈለግ በመከተል ለተተኪው ትውልድ መልካም ሥራ ሰርተው እንዲያልፍ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
v  እኛም ገዝተን መሄድ ብቻ ሳይሆን እንብበን እንጠቀምበት ዘንድ አምላክ ይርዳን ብለዋል


ይቆየን............................... ክፍል ሁለትን ይጠብቁ

Post Bottom Ad