ትንቢተ ሐጌ ፩፤፰ ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
ክፍል አንድ
የቤተክርስቲያኑ አሰራርና ነባራዊ ሁኔታ
የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ንጉስ አድባር ሰገድ ዳዊት ተሰርቶ ተጠናቀቀ። ንጉሰ ነገሥቱ በዘመኑ ከግብጽ አሌክሳንደርያ በመጡት የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ክርስቶደሉ ባላባቱና ም ዕመናኑ በተገኙበት ሰኔ 1 ቀን 1709 ተመረቀ።
በአራት ማዕዘን ቅርጽ የተሰራው ይህ ቤተክርስቲያን ግድግዳው በጥቁር ድንጋይና ተቃትሎ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት በውሃ ተዘፍዝፎ በተብላላ ኖራ ተገብቷል። በሮቹ ከቁስቋም ተጠርቦ በመጣ ቀይ ልዝብ ድንጋይ በቅስት ተጌጡ። ጣራው በባኅላዊ
በተጠረበ እንጨት ወራጅ ተሰክተው ጠፍጣፋ ድንጋይ ከለበሰ በኋላ ውሃ እንዳይሰርግ በኖራ ተለብጦ በግድግዳው ላይ ወራጅ አሸንዳዎች ተደረጉበት። ከም ዕራብ ወደ ምስራቅ የተገነባው ቤተክርስቲያ ከደጀሰላሙ እና ከቤተ መንግስት ጋር ትይዩ ነበር። በደጀ ሰላሙ የቤተክርስቲያን ም ዕራብ ግድግዳ ላይ በሰሜንና ደቡብ የ እንቁላል ቅርጽ ያላቸው ሞላላ የግንብ ማማዎች ተገንብተዋል።
በተጠረበ እንጨት ወራጅ ተሰክተው ጠፍጣፋ ድንጋይ ከለበሰ በኋላ ውሃ እንዳይሰርግ በኖራ ተለብጦ በግድግዳው ላይ ወራጅ አሸንዳዎች ተደረጉበት። ከም ዕራብ ወደ ምስራቅ የተገነባው ቤተክርስቲያ ከደጀሰላሙ እና ከቤተ መንግስት ጋር ትይዩ ነበር። በደጀ ሰላሙ የቤተክርስቲያን ም ዕራብ ግድግዳ ላይ በሰሜንና ደቡብ የ እንቁላል ቅርጽ ያላቸው ሞላላ የግንብ ማማዎች ተገንብተዋል።
ከቤተ መንግስቱ ጋር አስቄት በር በተባለችና ከአስራ ሁለቱ የአፄ ፋሲል ግቢ በሮች በማይጠቀሰው በር በኩል ጉሰ ነገሥቱና ባለሟሎቻቸው ይገቡ እንደነበር የታሪክ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
የቤተክርስቲያኑ የም ዕራብ በኩል የቤተልሔም ሕንጻ ይገኛል። ቤተክርስቲያኑ የንጉሥ ቤተ ክርስቲያን እንደ መሆኑ እጅግ ድንቅ የሆኑ ንዋየ ቅድሳት ባለቤት ስለነበር ለዕቃው ማስቀመጫ ባለ አንድ የእንቁላል ቅርጽ ያለው ሕንጻ ተገንብቶለት ነበር።
የቅርሱ ጥገና አስፈላጊነት
- ቅርሱ ከ300 ዓመት ያህል እድሜ ያለውና በሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ጉዳቶች የደረሰበት በመህኑ ወደ ነበረበት ጥንታዊ አሰራሩ መመለስ አስፈላጊነቱ የጎላ ነው
- ቅርሱ አሁንም ድረስ የመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ካለው የጉዳት ደረጃ አንጻር በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ቀድሞ መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ
- ቅርሱን ወደ እበረበት ጥንታዊ አሰራሩና ውበቱ በመመለስ እየሰጠ ያለው ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳ ከፍ ማድረግ በማስፈለጉ
- ቅርሶች መጠበቅ፤ ማልማትና፤ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የባህልና ቱሪዝም ተግባርና ሃላፊነት በመሆኑ
- ቅርሱ መጠበቅና መልማቱ የሚሰጠው፡ጣሪኻዊ፡ፋይዳ፡ኸፍጠኛ በመሆኑ
ደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል፤ ቱሪዝም እና ፓርኮች ልማት ቢሮ ባሕር ዳር ፤ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ይህን የቅርስ ጥገና ጥናት እና አስተያየት እንዲሰጥ የጠየቀበት ደብዳቤ እነሆ።