ሰበር ዜና፦ ትንቅንቅ ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, November 21, 2015

ሰበር ዜና፦ ትንቅንቅ ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር



ይህን ሁለት ቀን በጎንደር ከተማ ተሐድሶ መናፍቃን መስመራቸውን ዘርግተው ባልታሰበ ጊዜ እና ወቅት ጠብቀው ኑፋቄአቸውን ለመዝራት ሲዘጋጁ ሰንብተዋል።

 አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንድንሰብክ ፈቃድ ሰጥቶናል የሚል የፎርጅድ ደብዳቤ ለተሐድሶ አራማጆች አካል ፋክስ በማድረግ አቶ መናፍቁ በጋሻው እና አሰግድ ሳህሉ ጎንደርን በወንጌል እንጎበኛታለን በሚል ድብቅ ሴራ ሲደክሙ ሰንብተው በአቡን ቤት ቅዱስ ገብር ኤል ቤተክርስቲያን፤ በግምጃ ቤት ማርያም ጉባኤ ቤቱን በገንዘብ እንረዳለን በሚል ሰበብ እና በዓሉን አስመልክቶ በአጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መረባቸውን ዘርግተው ተንቀሳቅሰዋል፤ በዚህን ጊዜ የጎንደር ወጣት፤ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፤ ማህበረ ቅዱሳን እና ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ የማህበራት አባላት አንድ በመሆን የእነዚህን መናፍቃንን ሴራ አክሽፈውባቸዋል።

የመጀመሪያው እቅድ የተሐድሶ እንቅስቃሴው ከበፊቱ ይልቅ አሁን ጠንከር ብሎ በመዘጋጀት እስከ ቤተ ክህነት ድረስ በፎርጅድ የፈቃድ ደብዳቤ በመያዝ እና ከአባቶች ላይ በመጮህ አቶ በጋሻው፤ አቶ በሪሁን እና ምርትነሽ በአርማጭሆ ለሚገኘው የክርስቶስ ሰምራ የ እናቶች ገዳም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በማለት ጉባኤያቸውን በአቡን ቤት ቅዱስ ገብር ኤል ቤተክርስቲያን ለማድረግ ፈቃድ ያገኙ ሲሆን ለአጥቢያ ሰበካ ጉባኤው የመራው ሲሆን ይህንን ጉዳይ የሰሙ አካላት ለ እያንዳንዱ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፤ ለማህበረ ቅዱሳን አባላት እና ጎንደር ላይ ለሚገኙ ማህበራት አባላት በመደዋወል ወጣቱን ይዘን ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤልሳን ጉዳዩን በማስረዳት የተፈቀደውን ጉባኤ እንዲታገድ አድርገናል።  ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

የመጀመሪያው እቅድ እንደከሸፈ በሁለተኛው ቀን የሁለተኛ ዕቅድ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን ላለችው ጉባኤ ቤት የገንዘብ እርዳታ እንሰጣለን በማለት ለጉባኤ ተማሪዎች በመንገር እና ጉባኤ አዘጋጅተው ገንዘብ ሰብስበው ለመስጠት የተዘጋጁበት ሁኔታ ነበር።  ይህ ጉዳይ በድብቅ የተደረገ ሲሆን፤ በወቅቱ አጠቃላይ የሰንበት ትምህርት ቤት የአንድነት ጉባኤ ግምጃ ቤት ነበር።  ስለ ጸረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ግንዛቤ እንዲሰጥ እና በ የአጥቢያቸው ጉዳዩን እንዲያስገነዝቡ እና ቤተክርስቲያናቸውን በትጋት እንዲጠብቁ በምስልም በድምጽም በጽሑፍም የቀረበ ዝግጅት ነበር።  ሆኖም አንድ ክስተት ተፈጠረ።  የአሰግድ ሳህሉ አጫፋሪዎች ዛሬ አውደ ምህረት ስለሚሰብክ እንዲፈቀድለት የሚል ጥያቄ፡ ይዘው አይናቸውን አፍጠው፡ መጡ።  እኛም ጉባኤአችንን አቋርጠን ከነዚህ መናፍቃን ጋር ንትርክ ገጠምን።  ደስ የሚለው ነገር ግን ሰበካ ጉባኤው እኛ የማናውቀው ጉባኤ ስለሆነ ይህ ሰው በፍጹም አይሰብክም አሉ በዚህ ደስ ብሎን ሳል በጉባኤ ተማሪዎች አነጋገር እጅግ አዝነን ነበር።  ምክንያቱም እነሱ የተገነዘቡት እኛ በገንዘብ እንዳይረዱ በምቀኝነት ተነሳስተን መስሎአቸው ነበር።  ነገር ግን እድሜ እና ጤና ይስጠው እና ዲያቆን ዳን ኤል ክብረት ስድሳ ሺህ ብር በመስጠጥ  ለጉባኤ ቤቱ የአመት ቀለብ ሰጥቶ ነበር።  ነገር ግን እኛን የሚረዳን የለም ብሎ ሌላ ነገር መናገራቸው ቢያሳዝነንም ነገሩን ግን ቀስ ብለው በስብሰባ ከተነገራቸው እና ከተረዱት በኋላ ብንራብ ይሻላል እንጂ ይህን መናፍቅ አንፈልግም ብለው በአንድ ድምጽ ወደ መጣበት እንዲመለስ አድርገዋል።  የጉባኤ ቤት ተማሪዎችም እኛ፡እንዲረዳን የምንፈልግ ከሃይማኖት ሕጸጽ የጸዳ መሆን አለበት እንጂ ማንንም መናፍቅ በሆድ ሊገዛን አይችልም በማለት አሰግድን አሳፍረው ሰደውታል።  ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

የሁለተኛው እቅድ አልሳካ ሲል ወደ ሦስተኛ እቅዳቸውን ለማሳካት ሲፍጨረጨሩ ቆይተዋል።   ይኸውም የቤተክርስቲያኑ ሕንጻ ኮሚቴ እና ሰንበት ትምህርት ቤቱ ያቀደውን የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር የቅዱስ ሚካኤልን በዓል አስመልክቶ ከተጋበዙት እውነተኛ መምህራን ጋር አብሮ በመደባለቅ ለማስተማር ሊመጣ ነው የተባለው አካል የስነ ምግባር ችግር አለበት ስለተባለ ሌላ መምህር ይቀየር እና ጉባኤው ይካሔድ የሚል አቋም ይዘን ነበር።    እኔም በሕንጻ ኮሚቴ ንዑስ አባል ሆኜ እያገለገልኩ መምህራንን ለማስመጣጥ ፈቃዱን አግኝቼ ስልክ እየተደዋወልኩ ነበር።  ከሕንጻ ኮሚቴ አባል ስልክ ተደዉሎልኝ በቃ አትልፋ መምህር ተገኝቷል አሉኝ እኔም እነማን ናቸው ብየ ጠየኩ። የአብነት መምህራን ጉባኤ ቤት ለመርዳት ይመጣሉ እናም እነሱን እናድርጋለን አለኝ እኔም ደስ ብሎኝ እሽ ብየ ነበር።  በኋላ ግን የሚመጣው አካል አሰግድ ሳህሉ መሆኑን ስንሰማ አይደለም አውደ ምህረት ወጥቶ ለማስተማር ቀርቶ ቤተክርስቲያኒቱ አጥር፡ግቢ እንዳይመጣ፡የሚል አቋም ይዘን እርሱን አገድን።  ይህን መርሐ፡ግብር፡ያስያዘ ማን ነው የሚል ጥያቄ፡አቅርበን ነበር ነገር ግን ባለማወቅ እና መረጃ የሌላቸው በመሆኑ እኛም፡ጉባኤ ሲዘጋጅ የሚመጡትን መምህራን ተወያይተን ለወደፊቱ እንደምናዘጋጅ ተነጋግረን በሰላም ጨርሰናል።  ለዚህም እግዚአብሔር፡ይመስገን። 

የአትሮንስ መልእክት
እነዚህ የተሐድጾ፡ፕሮቴስታንታዊ መናፍቃን ምዕመናኑን ማህበረ ቅዱሳን ነው ይህን የሚያደርግ እያሉ ያስወራሉ፤ ይፍጨረጨራሉ፤ ይወራጫሉ፤ ጸብ ለመፍጠር፡ይጥራሉ፡ነገር ግን ያላስተዋለው ሰው እነሱን ተከትሎ ባለማወቅ ቤተ ክርስቲያንን ሲያቆስል ይኖራል። ስለዚህ ይህ ጉዳይ የማህበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ይምለከተዋል። እንደኔ ማኅበረ ቅዱሳን የተዋሕዶ ልጆች ስለሆኑ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል ስለሚሉ መናፍቃን ይጠሏቸዋል። ማህበረ ቅዱሳን አባል ያልሆኑ ነገር ግን ተሐድሶን የሚያሳድድ አካል ሲገኝ፡ደግሞ፡ይሕን ሰው ጽንፈኛ፡ ነው፤ በአገልጋዮች ላይ ስም ማጥፋት ከማህበረ ቅዱሳን ኮርስ ወስዶ ነው በማለት ተሰሚነትን እንዳያገኝ፡ እና እነዚህ መናፍቃን ስራቸውን ለመስራት ይመቻቸው ዘንድ የሚያደርጉት ስልት እንደሆነ ልናውቅ ይገባል።

እሰከ መጨረሻው የተሐድሶ እንቅስቃሴን ልንበጣጥሰው ይገባል። በዚህ ሳምንት ጎንደር መጡ ነገስ» እንሰብበት ይህ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው።

Post Bottom Ad