መስቀል ማለት
- · በብሉይ ኪዳን ዘመን፤ በእስራኤል ዘንድ ሰው በድሎ ወይም ጥፋት አጥፍቶ ከተገኘ፤ የሞት ፍርድም ከተፈጸመበት በኋላ፤ አስከሬኑን በእንጨት መስቀል ወይም ዛፍ ላይ በማንጠልጠል ለህዝብ ለማስጠንቀቂያ ወይም ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ ይጠቀሙበት ነበር። ነገር ግን እስራኤላዊያን ሰውን በስቅላት አይገድሉም ነበር ። (ዘዳ 21፤21-23 ኢያ 10፤26)
- · ሮማዊያን በብዙ ስቃይ እንዲሞት የተፈረደበትን ሰው በተለይም ደግሞ አመጸኞችን ይሰቅሉ ነበር። በተለይ እንደ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አገላለጽ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ400 ዓመት በፊት ብዙ ሺ ህዝብ በስቅላት እንደጨረሱ የተለያየ አይነት የስቅላት ምልክቶችም አንዳሉ ይነገራል።
- · ለእኛ ክርስቲያኖች የመዳን ምልክት ነው። ክርስቶስ የሞተው ስለ እኛ ኃጢአት ነውና የመስቀሉ ቃል የወንጌል ምልክት ሆኖልናል (1ኛ ቆሮ 1፡17-25
- · መስቀል የማስታረቅ ቃል ነው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶልናልና (ኤፌ 2፤14
- · መስቀል የቅድስና ቃል ነው። ምዕመናን ከክርስቶስ ጋር በመስቀሉ ተባብረዋልና በመስቀሉ ኃጢአታቸውን ክደዋል፤ ከዓለም ተለይተዋል፤ በመስቀልም ትምህርት አድርገው በአዲስ ህይወት ይኖራሉ (ሮሜ 6፤4 ገላ 2፤20
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7 ቃላት አሉ 7ቱ " አጽርሐ መስቀል " በመባል ይታወቃሉ። እነሱም፦
1) አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" ማቴ 17፦46
2) አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ሉቃ 23፦34
3) ዛሬ በገነት ከኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሀለሁ" ሉቃ 23፦4
4)አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" ሉቃ 23፦ 46
5) እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ" ዮሐ 19፦26
6) ተጠማሁ" ዮሐ 19፦28
7) ሁሉ ተፈጸመ " ዮሐ 19፦ 30
ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤
በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/
1. ፀሐይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም ሆነች
3. ከዋክብት ረገፉ
በምድር፤/ማቴ 27፦51_53/
1. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ
2. ምድር ተናወጠች
3. መቃብሮች ተከፈቱ
4. ሙታን ተነሱ
1) አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" ማቴ 17፦46
2) አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ሉቃ 23፦34
3) ዛሬ በገነት ከኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሀለሁ" ሉቃ 23፦4
4)አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" ሉቃ 23፦ 46
5) እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ" ዮሐ 19፦26
6) ተጠማሁ" ዮሐ 19፦28
7) ሁሉ ተፈጸመ " ዮሐ 19፦ 30
ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤
በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/
1. ፀሐይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም ሆነች
3. ከዋክብት ረገፉ
በምድር፤/ማቴ 27፦51_53/
1. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ
2. ምድር ተናወጠች
3. መቃብሮች ተከፈቱ
4. ሙታን ተነሱ
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በስቅላት በሞት ከፈረዱበት በኋላ
ብዙ ጊዜ የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸሙበት ነበር
1)
ከመሰቀሉ በፊት ይገረፋል (ማቴ 27፤26
2) መስቀሉን ወይም የመስቀሉን ግንድ ተሸክሞ ከከተማ ወደ ውጭ ወዳለው መስቀያ ቦታ ይወሰዳል (ዮሐ
19፤17
3) በምሳሌ 31፤6 የተጻፈውን በማሰብ በኢየሩሳሌም የነበረ የሴቶች ማህበር የስቃይ ማደንዘዣ መጠጥ
ለሚሰቀሉት ይሰጣል (ማቴ 27፤34
4) በመስቀል ላይ ይቸነከራል ወይም በገመድ ይታሰራል (ዮሐ 20፤25
5) ከበደለኛው ራስ በላይ የሟቹ ወንጀል ተጽፎ ይለጠፋል (ዮሐ 19፤19
6) የተሰቀለውን ሰው ልብስ ወታደሮች እንዲካፈሉት ያደርጋል (ዮሐ 19፤23
7) የተሰቀለው ሰው የሚሞተው ደሙን በማፍሰስ ሳይሆን በልቡ ድካም ነው። የሚሰቀለው ሰው ብዙ ጊዜ በሁለተኛው ወይም ሦስተኛው ቀን ይሞታል (ማር
15፤44) ወዳጆች እንዳያወርዱት መስቀሉ በወታደሮች ይጠበቃል ተሎ እንዲሞት ሲፈልጉ እግሮቹን ይሰብሩ ነበር። ጌታችን
መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግን ጎኑን ወጉት (ዮሐ 19፤31