አዳም አትብላ የተባለውንየእግዚአብሔርን ትዕዛዝበመሻሩና በመብላቱ ምክንያትከገነት ከተባረረ በኋላየነበረው ጊዜ የስቃይ የመከራየኩነኔ ዘመን በመሆኑ እስከክርስቶስ ልደት ድረስ ዘመነኩነኔ ወይም ዘመነ ፍዳበመባል ይታወቃል::እግዚአብሔርም ለአዳምከልጅ ልጅህ ተወልጄአድንሃለሁ ብሎ በገባለት ቃልኪዳን መሠረት፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል የምሥራች አማካኝነት ከንጽሕት ቅድስትድንግል ማርያም ተወልዶ፤ ተገርፎ፤ ተሰቅሎ፤ ሞቶ፤ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎከተነሳ በኋላ አርጓል፤ እኛንም ልጆቹን ከእርሱ ጋር አስታረቀን፤ ለፍርድም እንደሚመጣእናምናለን፤ እስከ እዚህ ድረስ ያለው ዘመን ደግሞ ዘመነ ምሕረት ወይም ዓመተ ምሕረት(የምሕረት ዘመን) በመባል ይታወቃል:: የሁለቱ ድምር ደግሞ ዓመተ ዓለም በመባልይታወቃል:: በዚህ መሠረት
ዘንድሮ 7506 ዓመተ ዓለም ሲሆን የ 2006 ዓመተ ምሕረትና የ5500 ዓመተ ፍዳ ወይምዓመተ ኩነኔ ድምር ነው::
አዳም ከገነት ያችን ዕፀ በለስ በልቶ ከተባረረ ወዲህ እግዚአብሔር አምላካችን ለአዳምተስፋ ሰጠው:: ተስፋውም ከአምስት ቀን ትኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁብሎ የገባለትን ቃል ኪዳን ከሰማ ወዲህ ቀን መቁጥር ወይም ማስላት ተጀመረ::
በናምሩድ ዘመን በሰናዖር የሰው ልጅ ቋንቋ ከተደበላለቀ በኋላ 5500 ዘመን መቁጠሩተዘነጋ:: ስለዚህ አንዳንዶች በጨረቃ እኩሎቹ በከዋክብት ሌሎቹ ደግሞ በፀሐይ ሲቆጥሩለዘመናት ያህል ኖረዋል::
እግዚአብሔር ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳንና ተስፋውን የሚጠባበቁ ካልሆነ በስተቀርየ 5500 ዘመን ማለትም የቀጠሮዋን ቀን የሚቆጥር፤ የሚያስብና የነብያትን ሱባኤየሚመረምር የሚያስተውል ሕዝብ ጠፋ:: ስለዚህ ፀሐይን የሚያመልክ በፀሐይሲቆጥር፤በጨረቃ የሚያመልክ ደግሞ በጨረቃ ሲቆጥር እንዲሁም በከዋክብት የሚያመልክደግሞ በከዋክብት ይቆጥሩ ጀመር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን ፀሐይን፤ጨረቃን፤ከዋክብትን ለዘመን መቁጠሪያ አድርጎ ነበር ለሰው ልጅ የሰጠው ነገር ግን የሰውልጅ አማልክት አደረጉአቸው::
የዘመንን አቆጣጠር ማን ቀመረው?
* 12ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲሜጥሮስ የዘመን አቆጣጠርን ቀመረው
* ቅዱስ ዲሜጥሮስ የአጽዋማትንና የበዓላትን የሚወስን የቁጥር ሕግ ለማግኘት ተመኘበመልአኩም አሳሳቢነት ሱባኤ ገብቶ ያሰበውንና የተመኘውን እግዚአብሔር አምላክገለጸለት እነሱም
* ሁልጊዜ ጾም ከሰኞ እንዲጀምር ወይም እንዳይወጣ ሥርዓትን ሰራላቸው
በበዓላት ጊዜ
* ደብረዘይት፤ ሆሳዕና፤ ትንሳኤ፤ ጰራቅሊጦስ ከዕሁድ እንዳይወጣ
* ስቅለት ከአርብ እንዳይወጣ
* ጾመ ድህነት ከረቡዕ እና አርብ እንዳይወጣ
* ርክበ ካህናት ከረቡዕ እንዳይወጣ
* ዕርገት ከሐሙስ እንዳይወጣ አደረገ
* ከጾመ አርባ ጋር አያይዘው እንዲያከብሩ የሕማማትን ሳምንትና የትንሳኤን በዓል ሥርዓትሠራላቸው
* የቀመር ሕግ አውጥቶ በዓመት ውስጥ ከወሰነላቸው ጊዜ ወደታች ወይም ወደላይእንዳይወጡ ባስቀመጠላቸው ቀመር እንዲጠቀሙ አደረገ
የተለያዩ የዘመን አቆጣጠር
* የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር
* አይሁዳውያን አመታቸውን የሚጀምሩት ከክርስቶስ ልደስ በፊት ከ3761ዓመት ነው:: ምክንያቱም አይሁድ የክርስቶስን መወለድ ስላልተቀበሉና ገና ይወለዳል ብለው ስለሚያምኑ ብቻ ነው::
* የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር
* እስክንድርያ የፈራክና ኮከብ ቆጠራ ማእከል ነበረች
* ዓመታቸውን በጨረቃ ሲቆጥሩ ከቆዩ በሁዋላ በፀሐይ ቆጥራለች
* በአንድ ወር ውስጥ ሠላሳ ቀናት ያላቸውን 12ቱን ወራት አምስት ቀን በመጨመር 365 ቀናት አንድ ዓመት መሆኑን ይናገራሉ
* በ239 ቢሲ 1/4ኛ ቀን ጨመሩ ይህም እኛ አሁን የምንጠቀምበትነው
* የዮልዮስ ቄሳር ዘመን አቆጣጠር
* ዓመት ብለው የሚጠሩት አስሩን ወራት ነበር ወራቶቹም 304ቀናትን የያዙ ነበር
* የሮምን ከተማ ከመሰረተው ንጉስ ቀጥሎ የነገሰው ንጉስ 304የነበሩትን ቀናት ጨምሮ 355 አድርጎታል
* በ46 ቢሲ ዲሊየስ ቄሳር በነገሰ ወቅት የአሌክሳንደራውያን ዘመንአቆጣጠር ዓመት ቀናት አብነት በማድረግ 365 ቀናት አደረገው ነገርግን የጳጉሜን ቀናቶች በየወራቱ በትኖ አከፋፍሎ አስቀመጣቸው::
* ዲዮናስዮስ ኤክሲጅየስ የተባለው የሮም ሊቅ መነኩሴ በ532 ዓ.ምእንዲህ በማለት ስለ ቀናትና ዓመታት ተናገረ:: ክርስቶስ ተወልዶበታልየተባለውን ዘመን ወደ ሁዋላ ስምንት ዓመት ወስዶታል:: የዚህ ዘመንጭማሪም 256 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጎአል:: ይህምዘመን የዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ መነሻ ሲሆን በሌላ በኩልም የዘመነሰማዕታት መጀመሪያ ነበር:: በዚህም 532 ዓ.ም ላይ ሆኖ ሳለ 276ይል የነበረውን አቆጣጠር 284 ብለው እንዲቆጥሩ አድርጎአልምአውጆአልም:: ከዚህ ዘመን ወዲህ የሰባትና ስምንት ዓመት ልዩነትእንዲፈጠር ዋና ምክንያት ሆኖአል ማለት ነው::
* ግሪጎሪ የሚባል የ13ኛው የሮም ፓፓ ከ46 ዓመተ ዓለም ጀምሮየነበረውን የዘመን አቆጣጠር 10 ቀናቶችን ጨምሮ ለውጥ በማድረጉምክንያት ግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር ተባለ:: የግሪጎሪያን አቆጣጠርመነሻውም የዓመቱ ቀናት 365 ከ6 ሰዓት የነበረውን 365 ቀናት ከአምስት ሰዓት ከ 48 ደቂቃና 46 ሰከንድ አደረገው:: በዚህምያልተኖረባቸውን 10 ቀናት እ.ኤ.አ ከ325 ዓ.ም ጀምሮ በማስላትእንዲወገዱ አውጁአል:: በዚህም መሠረት መስከረም ላይ የአስር ቀናትልዩነት ተፈጠረ:: ለምሳሌ ግሪጎሪ ጥቅምት 5 ቀን 1575 ዓ.ም /በኢትዮጵያ አቆጣጠር የነበረውን/ ጥቅምት 15 ቀን 1575 ዓ.ምእንዲሆን አዋጅ አድርጎአል::
* መሰግላን/መጥዓውያን/ (ጠንቁአዮች ኮከብ ቆጣሪዎች)
* በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ምድርግን ባዶ ነበረች አትታይምም ነበር የተዘጋጀችም አልነበረችምጨለማም በዉኃው ላይ ነበረ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይይፈስ ነበር:: እግዚአብሔርም "ብርሃን ይሁን አለ" ብርሃንም ሆነ::እግዚአብሔር አምላክም ብርሃኑን ቀን ጨለማውን ሌሊት ብሎጠራው:; እግዚአብሔርም አለ "በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በቀንናበሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ:: ለምልክቶች; ለዘመናት: ለእለታት; ለዓመታትም ይሁኑ:: በምድርላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ለማብራት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ:: እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ: ትልቁ ብርሃን(ፀሐይ) ቀንን እንዲመግብ ትንሹ ብርሃንም (ጨረቃ) ከከዋክብት ጋርሌሊትን እንዲመግብ አደረገ በመዓልትም በሌሊትም እንዲለዩ ሆነ(ዘፍ 1- 1-14):: እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ያደረገው ለእኛበምድር ለምንኖር ፍጥረቱ ሆኖ ሳለ በከዋክብት በጨረቃና በፀሐይዘመናትን; ዕለታትንና ዓመታትን በመቁጠር ፋንታ በከዋክብት;በጨረቃና በፀሐይ ዘመናትን ቆጥረው የፈጠራቸውን አምላክ ማምለክሲገባ እነዚህ መሰግላን ወይም መጥዓውያን ግን ያመልኩአቸዋል::
* ሰብአ ሰገልም ይህን የአቆጣጠር ዓይነት ተጠቅመውበታል
* ሠራዕያነ ህግ
* በዚህ ዓለም የምንኖር ፍጥረት የሰው ልጅንም ጨምሮ የሚኖረውለ7000 ዓመት ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው
* የሚገርመው ግን በነሱ ህግ መሠረት ይህች ዓለም መጥፋትየነበረባት የዛሬ 504 ዓመት ነበር ምክንያቱም 5500 + 2004 = 7504 ይሆናል ማለት ነው:: በዚህ አጋጣሚ በመነሳት ብዙ ሰዎችበተለይ በኛ ሕብረተሰብ ዘንድ 8ኛው ሺህ የሚባለው አባባል የዚህተጽሕኖ ሳይሆን አይቀርም ብየ አምናለሁ::
* ፍሌካውያን
* ከመሰግላን የተወሰነውን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ወስደውየጎደለውን በነገስታቱ አማካኝነት እያስወሰኑ የመጡ ናቸው
* የሃያ አራት ሰዓት መነሻን እኩለ ቀንን ያደረጉ ናቸው
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
* የፀሐይና የጨረቃ ጥምር አቆጣጠር ትጠቀማለች
* አንድ ዕለት የሚጀምረው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አስራ ሁለት ሰዓትነው:: የወሩ መጀመሪያ መስከረም እና የወሩ መጨረሻ ጳጉሜ ሲሆን የሳምንቱ መጀመሪያቀን ደግሞ እሁድ ነው::
* አንድ ዓመትም በውስጡ በ91 ቀናት የተከፋፈሉ አራት ክፍላተ ዘመናት አሉት እነሱምመፀው; ሐጋይ; ፀደይ እና ክረምት ናቸው::
*የሐሳበ ዘመኑ ትምህርት አቡሻህር ይባላል
* በአቡሻህር መጽሐፍ መግቢያ ላይ እንደገለጸው ይህትምህርት በዮሐንስ አቡሻህር ስም እንደተሰየመ ይነግረናል
* የአቡሻህር ስያሜዎችም
* ባህረ ሐሳብ - ስፋቱን ስለሚገልጽ
* ዘመነ ዓለም - የአዳምን ዘመን የሚቀምረውን ስለሚገልጽ
* መርሐ ዕውር - አዋቂውም አላዋቂውም ስለሚጠቀምበት
* የቁጥር ትምህርት - የዘመን አቆጣጠር ፈሊጥ ስለሚናገር
* በ81 መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ መጽሐፈ ሄኖክ እና የተወሰኑ መጽሐፍቶችደግነታቸው ቢታወቅም የዘመን አቆጣጠርን ስለሚናገሩ በዘመኑ ግሪካውያን ምንም ክርስትናን ቢቀበሉም የቀድሞው የአያቶቻቸው የኮከብ ቆጠራና ሥነ ፈለክልምዳቸውም ስለነበር መጽሐፍቱን አልተቀበሉትም:: በአንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አቡሻህር እና ሌሎች የቁጥር መጻሕፍት ከ 81 መጽሐፍቅዱስ ውስጥ ያልተካተቱበት ምክንያትም ለዚህ ነው::