ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (few pictures) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, June 11, 2014

ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (few pictures)

 there is more picture...coming soon

 (የገዳሙን ሕልውና ስለመታደግ)

  • ጻድቁ አባታችን አባ ምዕመነ ድንግል ሲያገለግሏትና ሲቀድሱባት የነበረችው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ታቦት ያለችበት ገዳም በአሁኑ ሰዓት በጎርፍ አደጋ ላይ ስለምትገኝ።
  • በኒህ ጻድቅ አባት በአባ ምዕመነ ድንግል ስም በስማቸው የሚጠራው ተራራ ላይ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማሰራት ታስቦ የአቅም ማነስ ስላጋጠመ ከበረከቱ እንድትሳተፉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን።
  • ይህ ታላቅ ጥንታዊ ገዳምና የበረከት ቦታ በአሁኑ ወቅት የሚገኝበት ሁኔታም ከዚህ የሚከተለውን ይመስላል  1. በገዳሙ ብዙ መነኮሳት የሚገኙ ቢሆንም በቂ መተዳደሪያ የላቸውም።  ይኸውም በቂ የእርሻ መሬት እና የገቢ ምንጭ በማጣት ምክንያት ከዚህ ቀደም የነበረው የገዳሙ መሬት ምንም ሰፊ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በገዳሙ ይዞታነት አይገኝም።  እርዳታም ማንም አይሰጣቸውም።
  2. ይህ ጥንታዊ ገዳም በምዕመናን መታወቅ የጀመረውም በአሁኑ ወቅት ነው። በቅርቡ የገዳሙን ሁኔታ አይተውና ተገንዝበው የሄዱ ምዕመናን የአቅማቸውን ያህል እየረዱ ይገኛሉ።  ቢሆንም ማህበሩ እየሰፋ እና እየተጠናከረ ስለሆነ እገዛው በቂ እና አርኪ አይደለም።  ሆኖም ለአገልግሎት የሚሆን ነዳጅ፤ ጧፍ፤ እጣን፤ ሻማ፤ የግብር ስንዴ እና ሌሎች መገልገያዎች ችግር ያለባቸው ሲሆን፤ አሁን አሁን ስለ ገዳሙ ታሪክ የሚሰሙ ምዕመናን ሁሉ አልፎ አልፎ የእርዳታ እጃቸውን እየዘረጉ ለአንድም፤ ለሁለትም ሰንበት መቀደሻ እየተገኘ ነው።  ለዚህም እግዚአብሔር ይስጥልን።
  3. የቤተ ክርስቲያኑም ሕንጻ በምዕመናን እገዛ ቢሠራም በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ካለው ታላቅ ወንዝ መሙላት በሚያስከትለው የአፈር መሸርሸር ምክንያት በአደጋ ላይ ይገኛል። ለመጭውም ክረምት እንደቆመ የሚከርም አይደለም።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተችና በቅዱሳን አባቶቻችን ተጋድሎ የጸናች ስትሆን በውስጧም ለሚፈጸመው መንፈሳዊ አገልግሎት በእርግጥ ቁሳዊ ድጋፍ ያስፈልጋታል።
“የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለች በታላላቆቹም ፊት ታቆመዋለች” (ምሳ 18፤16)
“በበረከት የሚዘራ በበረከት ያጭዳል” (2ኛ ቆሮ 9፤6)


ይህንን ታላቅ ገዳም ለመርዳት የምትፈልጉ፦
ስልክ፦ 0912 17 45 60
         0918 29 74 05
         0918  18 26 02
         0911 38 41 60
በባንክ ለመርዳት የምትፈልጉ፦

Post Bottom Ad