ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (ክፍል ሦስት) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, June 7, 2014

ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (ክፍል ሦስት)

                      ጻድቁ አባ ምዕመነ ድንግል
“የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለች በታላላቆቹም ፊት ታቆመዋለች” (ምሳ 18፤16)


  1. በዚያን ጊዜ ያች ደገኛ አገልጋይ ጎንደር የአፄ ግንብ እንደሚሰራ ትንቢት ለአፄ ፋሲል ተናግራለች። ይህ ቦታ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረና ዛሬም ድረስ ድንቅ ተአምራት እያደረገ ይገኛል።  ከእነዚህም ውስጥ ለግንዛቤ ያህል የሚከተሉት ይገኙበታል።ንጉሱ አፄ ፋሲልም የጻድቁን ቦታ ሳይረሱ መንግስታቸው ከጸናላቸው በኋላ ለገዳሙ ርስት ጉልት ሊሰጡ በተጓዙ ጊዜ ከአፋፍ ቆመው “የት ላይ ነው የጻድቁ በዓት?” ሲሉ ጠየቁ “ይህ ወይራና ጽድ የበዛበት በፊታችን የምናየው ነው” ሲሏቸው “ይህ ጭው ያለው ዱር ነው?” ቢሏቸው አዎ ብለው መልሰውላቸዋል። ከዚህም የተነሳ ይህ ቅዱስ ሥፍራ “ጩጊ” ለመባል በቃ።  የጻድቁ በዓት መጸለያ ዋሻም በስማቸው “ምዕመነ ድንግል” ተብሏል። ጻድቁም በሕይወት እንደነ ቅዱስ ሄኖክ፤ ቅዱስ ኤልያስ፤ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ዮሃኒ በህቡዕ አሉ።
  2. የጻድቁ መጸለያ ቦታ በተፈጥሮው የተሸነቆረ መስኮት አለው። በዚህ ቅዱስ ቦታ ላይ መኻን የሆኑ ሁሉ በመስኮቱ ወጥተው ሲመለሱ ማየ ዮርዳኖሱን ጠጥተው ሲሳሉ ልጅ ለማግኘት ይበቃሉ። ይህን ቃል ኪዳን የሚያውቁ ጳጉሜን በሙሉ በማየ ዮርዳኖሱ በመጠመቅ ትልቅ ሃብተ ፈውስ ያገኛሉ። ለእያንዳንዱ ተጠማቂም ሆነ ሱባኤ ይዘው፤ በረከትን አግኝተው ለመመለስ ለሚመጡ ምዕመናንም ሁልጊዜ የሚተላለፍ መልእክት እና ማሳሰቢያዎችም አሉ።  ከማሳሰቢያዎች አንዱ እንዲህ የሚል ነው።  ወደዚህ ቅዱስ ሥፍራ ለመድረስ የተወሰነ ርቀት ሲቀር ከገዳሙ መግቢያ አካባቢ ካለው ዛፍ ላይ የተጫሙትን ጫማ በማውለቅ በባዶ እግር ይሂዱ፤ ለእያንዳንዱ ሴቶች ደግሞ በየወሩ ከሚመጣ የተፈጥሮ ግዴታ ካለባቸው፤ መግባት እንደሌለባቸው  በትልቁ ተጽፎ እናገኛለን።  የገዳሙን ሕግ ማክበር ተገቢ ስለሆነ ማንኛውም ምዕመን ይህን የማድረግ ግዴታ አለበት። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት መጠበቅም ማስጠበቅም የሁላችን ሃላፊነት ስለሆነ እና ቦታው ቅዱስ ስለሆነ እንድንቀደስ ብቻ ነው።
  3. የዮርዳኖሱን ጸበል የጠጣ ሲሞት ሥጋው አይፈርስም አይበሰብስም።  እንኳን በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው እንስሳቱ አንኳን አካላቸው ሳይፈርስ ይቆያል።  ለማስረጃ ያህል 16 የሚሆኑ ፍየሎች አካላቸው ሳይፈርስ 400 ዘመን በላይ ያስቆጠሩ አሉ።
  4. በ1968 ዓ.ም አንድ ዛፍ ከወንዝ ዳር ወድቆ አንድ ገበሬ ለማገዶ ሲፈልጠው እስከነ ምሳሩ ተነስቶ ቆሟል። በስሩም ሰባት ጸበል ፈልቆ ብዙ ህሙማንን ፈውሷል።
  5. ሰኔ 21 ቀን 1988 ዓ.ም አንድ ዛፍ በእርሻ መካከል ስለወደቀ ለማስወገድ ከሥሩ በእሳት ቢያቃጥሉት ሥሩን ትቶ ከጫፍ እየነደደ ከወደቀበት ተነስቶ ቆሟል።
  6. በዚህ ቅዱስ ቦታ ላይ የብዙ ቅዱሳን አጽም ይገኛል።

ስለዚህ ይህንና የመሳሰሉትን መልካም ነገር ለማየትና ከበረከቱ ለመሳተፍ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ እንድትመጡ በምዕመነ ድንግል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ጥሪየን አስተላልፋለሁ።  የበረከቱ ተሳታፊዎች ለመሆን ያብቃን።
                                                   ማሳሰቢያ 
                                      (የገዳሙን ሕልውና ስለመታደግ)

  • ጻድቁ አባታችን አባ ምዕመነ ድንግል ሲያገለግሏትና ሲቀድሱባት የነበረችው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ታቦት ያለችበት ገዳም በአሁኑ ሰዓት በጎርፍ አደጋ ላይ ስለምትገኝ።
  • በኒህ ጻድቅ አባት በአባ ምዕመነ ድንግል ስም በስማቸው የሚጠራው ተራራ ላይ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማሰራት ታስቦ የአቅም ማነስ ስላጋጠመ ከበረከቱ እንድትሳተፉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን።
  • ይህ ታላቅ ጥንታዊ ገዳምና የበረከት ቦታ በአሁኑ ወቅት የሚገኝበት ሁኔታም ከዚህ የሚከተለውን ይመስላል


  1. በገዳሙ ብዙ መነኮሳት የሚገኙ ቢሆንም በቂ መተዳደሪያ የላቸውም።  ይኸውም በቂ የእርሻ መሬት እና የገቢ ምንጭ በማጣት ምክንያት ከዚህ ቀደም የነበረው የገዳሙ መሬት ምንም ሰፊ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በገዳሙ ይዞታነት አይገኝም።  እርዳታም ማንም አይሰጣቸውም።
  2. ይህ ጥንታዊ ገዳም በምዕመናን መታወቅ የጀመረውም በአሁኑ ወቅት ነው። በቅርቡ የገዳሙን ሁኔታ አይተውና ተገንዝበው የሄዱ ምዕመናን የአቅማቸውን ያህል እየረዱ ይገኛሉ።  ቢሆንም ማህበሩ እየሰፋ እና እየተጠናከረ ስለሆነ እገዛው በቂ እና አርኪ አይደለም።  ሆኖም ለአገልግሎት የሚሆን ነዳጅ፤ ጧፍ፤ እጣን፤ ሻማ፤ የግብር ስንዴ እና ሌሎች መገልገያዎች ችግር ያለባቸው ሲሆን፤ አሁን አሁን ስለ ገዳሙ ታሪክ የሚሰሙ ምዕመናን ሁሉ አልፎ አልፎ የእርዳታ እጃቸውን እየዘረጉ ለአንድም፤ ለሁለትም ሰንበት መቀደሻ እየተገኘ ነው።  ለዚህም እግዚአብሔር ይስጥልን።
  3. የቤተ ክርስቲያኑም ሕንጻ በምዕመናን እገዛ ቢሠራም በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ካለው ታላቅ ወንዝ መሙላት በሚያስከትለው የአፈር መሸርሸር ምክንያት በአደጋ ላይ ይገኛል። ለመጭውም ክረምት እንደቆመ የሚከርም አይደለም።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተችና በቅዱሳን አባቶቻችን ተጋድሎ የጸናች ስትሆን በውስጧም ለሚፈጸመው መንፈሳዊ አገልግሎት በእርግጥ ቁሳዊ ድጋፍ ያስፈልጋታል።
“የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለች በታላላቆቹም ፊት ታቆመዋለች” (ምሳ 18፤16)
“በበረከት የሚዘራ በበረከት ያጭዳል” (2ኛ ቆሮ 9፤6)


ይህንን ታላቅ ገዳም ለመርዳት የምትፈልጉ፦
ስልክ፦ 0912 17 45 60
         0918 29 74 05
         0918  18 26 02
         0911 38 41 60
በባንክ ለመርዳት የምትፈልጉ፦
ይቆየን...............


Post Bottom Ad