ጻድቁ አባ ምዕመነ ድንግል
በዚህን ጊዜ ጻድቁ አባ ም ዕመነ
ድንግል ከ 40 ልጆቻቸውና ደቀመዝሙራቸው ጋር ጩጊ ቅድስት ማርያም ገዳምን ጥግ ከለላ አድርገው መኖር ጀመሩ። በዚህም ቦታ ዋሻ ፈልፍለው በጸሎትና በተጋድሎ በሚኖሩበት ወቅት የነገሩትን
የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ በታላቅ ቦታ
እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላ እክት፤ ነቢያት፤ ሐዋርያትን፤ ሰማ ዕታትንና ቅዱሳን አበውን አስከትሎ “ወዳጄ የአባቴ ወዳጅ፤ የመንፈስ
ቅዱስ ወዳጅ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” አላቸው። ጻድቁ ይህንን የመሰለ ብርሃንና ልዩ ንውጽውጽታ በማየት ተደንቀው አምላካቸውን
እጅ ነስተው (ሰግደው) ለ እመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ሰግደው እና እጅ ነስተው ድንቅ ነገር በማየታቸው በሚደሰቱበት ጊዜ
ጌታችን በ እጁ አንስቶ አቅፎ ሳማቸው። የሚከተለውን ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።
“በዚህ ቦታ
አንተ በተጋደልክበት ማህበር መስርቶ የሚኖረውን እና የሚማጸነውን ሁሉ አኗኗሩ እንደ ሰማይ መላ እክት ይሆንለታል። ወደዚህ ቅድስት
ቦታ የመጣውን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደ እቆጥርለታለሁ። ከዚህ ቦታ
ስጋየን ደሜን አምኖ የተቀበለውን ከቅዱሳን መላ እክት ጋር በአባቴ ክብር በምመጣበት ጊዜ ፈጽሞ ገሃነመ እሳት አላሳየውም። ምንም ኃጢአት ቢሰራ አምላከ ምዕመነ ድንግል ይምረኛል ብሎ በፍጹም እምነት
የመጣውን ወደ ተወለድኩበት ቤተልሔም ወደ አደኩበት ናዝሬት፤ ወደ አስተማርኩበት ደብረዘይት፤ ወደ ተጠመኩበት ዮርዳኖስ፤ እና ወደ
ተሰቀልኩበት ቀራንዮ እንደሄደ እቆጥርለታለሁ” በማለት ይህን አማናዊ ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ካሉበት ከበዓታቸው በስተቀኝ በኩል የኪዳነ
ምሕረትን ጸበል በስተግራ ዮርዳኖስን ጸበል አፍልቆላቸዋል። (ገላ 3፤15-18)
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ምዕመነ ድንግል ይህን ቃል ኪዳን በተቀበሉበት በዚህ ቅዱስ ስፍራቸው ተጋድሏቸው
በበለጠ ሲጋደሉ “ፈዋሴ ድውያን” ተብለዋል። ይኸውም በአፄ ሱስንዮስ ኃይማኖታቸውን ወደ ካቶሊክ ለውጠው እንዲሁም “የሃገሪቱን
ሃይማኖት እንዲለውጥ” በማለታቸው ምክንያት 140ሺህ ቅዱሳን አባቶች ይህንን ተቃውመው መስቀል እንደጨበጡ ስለ ሃይማኖታቸው በሰማዕትነት
ሲጋደሉ ንጉሱ በቅዱሳን ላይ ባደረሱት ጭካኔ የተሞላበት ጥፋት ምላሳቸው ተጎልጉሎ ነበር። በዚህ ጊዜ በጣም ደግና ብልህ የነበሩት ልጃቸው አፄ ፋሲል ስለ አባታቸው
መዳን በጣም ተጨንቀው መፍትሔ ለማግኘት የሚነግራቸው ብቁ ሰው ሲያፈላልጉ አንድ የበቁ አባት ከሞት የተረፉ ከጥላ ያረፉ፤ በ እድሜ
የገፉ፤ ግዝቱን ለመፍታት የማይቻል አንድም ወለቴ የተባለችው አገልጋያቸውና የአቡነ ም ዕመነ ድንግል ክብር እንዲገለጽ የተረዱ ታላቅ
ባሕታዊ ተገኙና “ከዚያም ከቤት ከሴት ሰራተኛ አገልጋዮችህ ውስጥ አንዲት የበቃች አለችና እርሷ መፍትሔውን ትነግርሃለች” ብለው
አመላከቷቸው።
ይህችም ወለቴ የተባለች ስትሆን ከብቃቷ የተነሳ በክንፍ እንደ መላ እክት እየበረረች ስትሔድ
ያያት ሁሉ “አሞራየ” ይሏታል። እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በህቡዕ ተሰውራ ትኖራለች። የመጸለያ በአቷና ገዳሟ በባህር ዳር ዙርያ አዴት አካባቢ አዳማ ጊዮርጊስ
አጠገብ ነው። አጼ ፋሲልም በየበሩ ወታደሮቻቸውን አሰልፈው ሲያስጠብቁ
ይህችም አገልጋይ በጸሎት አድራ ስትመለስ አግኝተው ይዘው አቀረቧት።
በዚያን ጊዜ በብዙ መግባባት ቢጠይቋትም ምንም እንደማታውቅ ተራ ሃጢአተኛ እንደሆነች ገለጠችላቸው። ሆኖም በብዙ ልመና ሲማጸኗት “ ድንግል መነኩሴ ቢገኝ አባታችን እንደሚፈውስላቸው
አፄ ፋሲልን እንደሚነግሱ” ነገረቻቸው።
አፄ ፋሲል “ድንግል መነኩሴ ፈልጎ ላመጣልኝ እሸልማለሁ” ብለው አወጁ። አቡነ ም ዕመነ ድንግል ባሉበት አካባቢ የሚኖሩ ይጉይታና ባጅር የሚባሉ ባላባቶች
ውሾቻቸውን አስቀድመው ሲያፈላልጉ ጻድቁን እንደሚፈልጉ ስለሚያውቁ አርድዕቶቻቸውን “ሰው ሲመጣ በበሩ እየተመለከታችሁ እንድትነግሩኝ” ብለው ዳዊታቸውን እየደገሙ ሳሉ እረዳታቸው
ውሻ አዩና “አባ ውሻ መጣ” ብለው አሏቸው። አባም “እ! ብለው ውሻ
መጣ…..ሰው መጣ…..ሰው መጣ ነገር መጣ” ብለው ወደ ባህር ገቡ።
በገቡም ጊዜ እዚህ ነበር የማይባል ድንጋይ ከውሃው ወደ ላይ ገፍቶ (አንስቶ) አወጣቸው። ይህን ድንጋይም በአሁኑ ሰዓት በዚያው ይታያል። ባላባቶችም “አባ ከአፄ ፋሲል ተልከን ነው። የአባቴን ምላስ ግዝቱን ፈቶ የሚመልስ መነኩሴ ካገኘሁ ተዋሕዶ ኃይማኖትን
እመልሳለሁ ብለው ቃል ስለገቡ ነውና ማስረጃ የንጉስ ማህተም ይኸው” ባሳዩአቸው ጊዜ በደስታ አብረዋቸው በመሄድ ከእነ አባ ዓምደ
ሥላሴ ጋር በመጸለይ አዋጅ አስነግረው “ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ….ተዋሕዶ ይመለስ….የአፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ….እግዚአብሔር
ይፍታ” ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ። በዚያን ጊዜ አፄ ሱስንዮስ “ብቆይ አመት ብበላ ገአት/ገንፎ” ብለው በመናገር
ማላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። አፄ ሱስንዮስ ለንስሐ ሞት በቅተው
መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል። በታላቁ ገዳም
ዳጋ እስጢፋኖስ አጽማቸው ከብዙ ነገስታት አጽም ጋር ይገኛል።
ይቀጥላል……………………….