አመ 5 ለሰኔ በዛቲ ዕለት አዕረፈ አብ ያዕቆብ ምሥራቃዊ ተአማኒ መስተጋድል - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Friday, June 13, 2014

አመ 5 ለሰኔ በዛቲ ዕለት አዕረፈ አብ ያዕቆብ ምሥራቃዊ ተአማኒ መስተጋድል

ሰኔ 5 ቀን 2006 ዓ.ም
ወበዛቲ ዕለት ካዕበ ኮነ ተዝካሮሙ ለአባ አሞን ወሚናስ በረከቶሙ ተሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን።

ዘነግህ፦ ምስባክ
እሙንቱሰ ዘንተ ርእዮሙ አንከሩ፤
ደንገፁ ወፈርሁ ወአኅዞሙ ረዓድ፤
ወሐሙ በህየ ከመ እንተ ትወልድ።
    ትርጉም፤
እነሱስ ይህ አይተው አደነቁ፤
ደነገጡ ፈሩ ብርክ ያዛቸው፤
በዚያም እንደምትወልድ ሴት ተጨነቁ።

የዕለቱ ወንጌል (የሉቃስ ወንጌል ም 21፤20-22)
ኢየሩሳሌምን ወታደሮች ከበዋት ባያችሁ ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ደረሰ ዕወቁ።  ያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሸሻሉ፤ በውስጧም ያሉ ከ እስዋ ይወጣሉ።  በአውራጃዎችዋም ያሉ ወደ ውስጥ አይገቡም።  በ እርስዋ የተጻፈ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እርስዋነንዲቀበሉበት ጊዜዋ ነውና።

የቅዳሴ፤ የሐዋ ም 17፤12-13

ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ሄድን፤ ይህችውም የመቄዶንያ ከተማ ነበረች ይህችም ሃገር ቆሎንያ ናት በዚያችም ሃገር ጥቂት ሰነበትን። በሰንበት ቀንም ከከተማ ውጭ ወደ ባህሩ ዳረ ወጣን በዚያ የጸሎት ቤት ነበርና፤ ከዚያም ተቀመጥን፤ በዚያ ለተሰበሰቡ ሴቶችም እናስተምር ጀመርን።

ቅዳሴ ባስልዮስ

ወበዛቲ ዕለት ካዕበ ኮነ ተዝካሮሙ ለአባ አሞን ወሚናስ በረከቶሙ ተሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አመ 5 ለሰኔ በዛቲ ዕለት አዕረፈ አብ ያዕቆብ ምሥራቃዊ ተአማኒ መስተጋድል።
በዚህች ቀን ታማኝና ተጋዳይ የሆነ ምሥራቃዊው አባት ያዕቆብ አረፈ።  ይህም ቅዱስ ከም እመን ዋልንጦስ ዘመን በኋላ የታላቁ ቆስጠንጢኖስ ልጅ በሆነ በታናሹ በቆስጠንጢኖስ ዘመን በከሃዲው ሉልያኖስ ዘመን በምሥራቅ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም በገድል ተጠምዶ ኖረ።  ዋልንጦስ ከተገደለ በኋላም በእርሱ ፈንታ ወንድሙ ነገሰ እርሱም አርዮሳዊ ነበር።  የጣዖት ቤቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሃይማኖታቸው የቀናውን የም ዕመናንን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲዘጉ አርዮሳውያንን አዘዛቸው።  ወደ ከፋችና ወደ ተበላሸች ሃይማኖታቸው ም ዕመናን በግዳጅ እስኪገቡ ድረስ እንዲሁ አደረጉ።  ይህም የንጉሱ ትዕዛዝ በሚገዛው አገር ሁሉ ደረሰ።  ይህ አባ ያዕቆብም ይህን በሰማ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ።  ያን ጊዜም ተነስቶ ወደ ቁስጥንጥንያ ሄደ።  በምዕራብ በኩል የተነሱበትን ጠላቶቹን ሄዶ ለመውጋት ሲወጣ ንጉሱን አገኘው።  ይህ አባት ያዕቆብም በፊቱ ቆሞ ንጉስ ሆይ በጠላቶችህ ላይ እግዚአብሔር ይረዳህ ዘንድ ም ዕመናንን እንዲጸልዩልህ አብያተ ክርስቲያናትን ክፈትላቸው ብየ እለምንሃለሁ ይህን ካላደረግህ ግን እግዚአብሔር ይጥልሃል፤ ከጠላቶችህም ሸሽተህ በ እሳት ቃጠሎ ትሞታለህ አለው።
ንጉሱም ይዞ ለሚጠብቀው ወታደር በሰላም እና በደህንነት እስክመለስ ጠብቀው ብሎ ሰጠው።  ቅዱስ ያዕቆብም አንተ በደኅና ከተመለስክ በእኔ አንደበት እግዚአብሄሔር አልተናገረም ማለት ነዋ አለው። ያን ጊዜ ቅዱሱን ይዘው ደብድበው አሰሩት፤ ንጉሱም ከሰራዊቱ ጋራ ወደ ጦርነቱ ሔደ በረከሰች ጸሎታቸው አርዮሳውያን ምንም ቢራዱት ክብር ይግባውና ጌታችን በጠላቶቹ አንጻር ጣለው እነርሱም ጠላቶቹ እየተከተሉት ሸሽቶ ከአንዲት ዐፀድ ውስጥ ገባ። በዚያም በረከሰች ሃይማኖቱ ከሚያምኑ ወገኖቹ ጋራ በእሳት አቃጠሉት። የቀሩትም ሰራዊት ሁሉ ሸሽተው ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሱ። ይህንንም መልካም ዜና ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን ተናገሩ። የዚህ ጻድቅ አባት ያዕቆብም ትንቢቱ ተፈጸመ። ከ እስር ቤትም በክብር አወጡት። ም ዕመናንም ከሃድያንም በላዩ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ተረዱ፤ ከአርዮሳውያንም ብዙዎቹ የአባቶቻችን ሐዋርያት ወደ ሆነች ቅን ሃይማኖት ተመለሱ፤ በዚህ አባት እግር በታች ሰግደው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ አመኑ። ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ቦታው ተመለሰ። አርፎ የሕይወትና የሰማዕትነት አክሊልን እስከ ተቀበለ ድረስ እንደ ቀድሞው በገድል ተጠምዶ ኖረ። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን።

እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

Post Bottom Ad