ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (ክፍል አንድ) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, May 31, 2014

ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም (ክፍል አንድ)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው መዝ 118 (119)፤ 129

ጩጊ ማርያም አንድነት ገዳም

ይህ ጽሑፍ የታሪክና የሃማኖት ዓምድ የሆነውን የጩጊ ማርያም አንድነት ገዳምን የሚያስተዋውቅና ከዚያም ባሻገር ቦታውና አባቶች ለሃይማኖታችን ካበረከቱት አስተዋጾ እና እያበረከቱት ካለው እንጻር ከእኛ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ በማመላከት ልናደርገው በምንችለው ሁሉ ለክርስትና ፍሬ ለበረከት እንድንሳተፍ የሚያሳስብ ነው።
        የጩጊ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አጭር ታሪክና አሁን የሚገኝበት ሁኔታ በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት በወገራ ወረዳ ከጎንደር ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ላይ ኮሶዬ ትንሽ ከተማ ሲደርሱ በግምት የሁለት ሰዓት የእግር መንገድ እንደተጓዙ ጩጊ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ትገኛለች።  የገዳሙ መስራች አባ ምዕመነ ድንግል የተወለዱበት በወገራ አውራጃ ሲሆን ገና ከሕጻንነታቸው በእናት በአባታቸው ቤት አያሉ የተራበን በማብላት፤ የተጠማን በማመጣት የታመመን በመጎብኘት በጾም በጸሎት በስግደት ሕገ እግዚአብሔርን እየፈጸሙ በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል።  ምሳ (22፤6)
አባታችን ምዕመነ ድንግል የምንኩስና ልብስና የእግዚአብሔር ጸጋ በመፈለግ አዳጋት ማርያም ወደምትባል ገዳም በመሔድ ምንኩስናን ከአባ ፄዋ ድንግል ተቀብለዋል።  ከዚያም ወደ ዋልድባ ገዳም በመሔድ ብዙ ተጋድለዋል።  ጽናታቸውን ያዩ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት አባትና መምሕር እንዲሆኗቸው ቢጠይቋቸው እራሳቸውን ዝቅ በማድረግ “እኔ መምሕር እና አባት ልሆን አይገባኝም” በማለት እይሆንም ቢሉም መነኮሳቱ አበምኔት አድርገው ሾመዋቸዋል።  አባታችንም በተሾሙበት በዚህ ገዳም በከፍተኛ ተጋድሎና በ እግዚአብሔር ጸጋ ብዙ መንፈሳዊ መነኮሳትንና መምህራንን በትምህርታቸው አፍርተዋል።
ከዚህ በኋላ በጊዜው በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በሃይማኖት ምክንያት በርካታ ቅዱሳን መነኮሳት ሰማ ዕታትን እየተቀበሉ ስለነበረ እሳቸውም ስለ ትክክለኛይቱ ሃይማኖት መስክረው ሰማዕትነት ሊቀበሉ ሲመጡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ጊዜህ ገና ነው፤ የተዋሕዶ ሃይማኖት መመለሷን ሳታይ ሰማ ዕትነትን አተበልም” ብላቸው አሁን በስማቸው በሚጠራው ተራራ ዋሻ ፈልፍለው እንዲጸልዩና እንዲያስተምሩ እስከመቼም ቢሆን በርድኤት እንደማይለያቸው አስረድቷቸው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ዋሻው ውስጥ እያሉ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንና ሃይማኖት ለማጥፋት ያቀደ አረመኔ ካቶሊክ ፈረንጅ መጥቶ፤ “ክርስቶስን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ” ብላችሁ እመኡ እያለና ሕዝቡን እየጨፈጨፈ በሚያቸግርበት ጊዜ በመቃወም “ ክርስቲያን ሁሉ በአበው ሃይማኖት ጽኑ፤ እግዚአብሔር በአካል ሦስት በመለኮት፤ በአገዛዝ፤ በሥልጣን፤…. አንድ ነው እንጂ ከዚህ ውጭ አይደለም፤ በሃይማኖታችሁ ጽኑ” እያሉ ቀን ከሰራዊት ጋር እንደሰራዊት እያስተማሩ፤ ያመኑትን እያጠመቁ፤ ቀድሰው ሥጋ ወደሙን እያቀበሉ በትግሃ ሌሊት በጸሎትና በስግደት የክርስቶስን መከራ በማሰብ ፊታቸውን እየጸፉ በከፍተኛ ገጋድሎ የሃይማኖትን መንገድ በፋናቸው አሳይተዋል (ኤፌ 4፤5-6)።  አንድ ጌታ፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንዲት ጥምቀት ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ እያሉም አስተምረዋል።
በዚያን ዘመን ዐፄ ሱስንዮስ ነግሰው በነበሩበት ወቅት ከፖርቹጋል ጋር ግንኙነት ነበራቸው።  ይህንንም ግንኙነታቸውን ለማዳበርና ለማጠናከር የፖርቹጋል ሴት እንዲያጩ ተገደዱ፤ ዐፄ ሱስንዮስ በዚህ ምክንያት ሃይማኖትቸውን ለውጠው ሲኖሩ በገዳማት የሚኖሩ መነኮሳትና በኢትዮጵያ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት የሚኖሩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስለተቃወሟቸው መነኮሳት ካሉበት ከበአታቸው ሊቃውንትን ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እና አድባራት እያደኑ ያስፈጇቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል።  ለምሳሌ ከቅዱሳን አንስት እነ ቅድስት ፍቅረተ ክርስቶስን የመሳሰሉ ቅዱሳን በዚያን ጊዜ ነበር የተሰውት።

ይቀጥላል……….

Post Bottom Ad