አብሳሪ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Thursday, March 27, 2014

አብሳሪ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል



== ===> ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛምእግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ ይምንልበትን ጸጋ አሰጠን። ጠበቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የሃጢያት እሳትም አጥፋልን፡፡ የኑሮአችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን። ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን። 

=====> ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና አንጌቤናዊቷ እናቱ በንፍር ውሃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን። የሰይጠንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።
== ===> ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ ፡፡ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ፡፡ ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበር ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ (የምሥራች ) ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ላዘንን ለእኛ ከሠማይ ሠረገላ ናልን፡፡ የደስታንም ቃል አሰማን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት ፣ የሞት፣የክስረት፣የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ገን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን፡፡
== ===> እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን። በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን ለዘላለሙ አሜን። ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
=====> “በኡባልም ወንዝ መካከል። “ገብርኤል ሆይ”፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ። እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ። ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ። እንዲህም አለኝ። እነሆ፥ በመቅሠፍቱ በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን አስታውቅሃለሁ፤ ይህ ለተወሰነው ለፍጻሜ ዘመን ነውና።” ት/ዳን.፰፡፲፮-፲፱ (8፡16¬-19)
== ===> ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡
=====> በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
=====> ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡
=====> በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡
=====> በሰማዕትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡
== ===> የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡
=====> ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡

Post Bottom Ad