የአብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት /ምኩራብ/፦ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, March 5, 2014

የአብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት /ምኩራብ/፦

፫ኛ ሳምንት ምኩራብ


    በዚህ በሦስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦

በግዕዝ፦

እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

በአማርኛ፦ 

የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ። መዝ.፷፰፡፱

 ዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ 
በዚህ የሦስተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ የወንጌልን ትምህርት እንዳስተማረ፤ ብዙ ድውያንን
እንደፈወሰ፤ የሰንበት ጌታ እንደሆነ፤ የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት እንጂ የንግድ ቦታአይደለም በማለት በቤተ መቅደሱ አካባቢ የሚነግዱ ነጋዴዎችን ስለ መገሰጹ ትምህርትይሰጥበታል። በተለይም በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ጌታ በአይሁድ ምኩራብ ገብቶመጽሐፍ እንዲሰጡት ጠይቆ የሚሰሙት ቃል ዛሬ በጆሯቸው እንደተፈጸመ እንዲህ ሲልእንደነገራቸው ይዘከርበታል፦
ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው
አገር ሁሉ ዝና ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥


ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ
ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤
ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ
ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ
አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት
ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም። ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ
ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው
ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምንይሉ ነበር። እርሱም። ያለ
ጥርጥር ይህን ምሳሌ። ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም
እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ
አላቸው። ሉቃ.፬፡፲፬-፳፫
ጌታችን በምድር ሲመላለስ ከዚህ ቀደም በምኩራቦቻቸው ተሰምቶ
የማይታወቅ የወንጌል ትምህርት እንዳስተማራቸውና ዕውራን እንዲያዩ፤ ደንቆሮዎች
እንዲሰሙ፤ ዲዳዎች እንዲናገሩ በማድረግ እንዲሁም ደግሞ ሙታንን በማሥነሳትየተለያዩ ድንቅ ተኣምራቶችን በማድረግ የወንጌልን ኃይል ስለማሳየቱ ይተረክበታል።የቤትህ ቅናት በላኝ ተብሎ እንደተጻፈ ሕገ እግዚአብሔር እንዲፈጸም፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያንእንዳይፈርስ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳይበላሽ በአይሁድ ምኩራብ በመግባትእንዳስተማረ ሁሉ ዛሬም እያንዳንዳችን የቤተ ክርስቲያንን ነገር ለቤተ ክርስቲያን በማድረግበቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ነገርን ብቻ በመሥራት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርንበመከተል ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንደሚገባን ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል። ቤተክርስቲያን የጌታ ሥጋ እና ደም የሚፈተትባት፤ ሰዎች ዘላለማዊ ሕይወትን የሚያገኙባትመሆኗም ይነገርባታል። ጌታችን በቅፍርናሆም ምኩራብ የሕይወት እንጀራ እርሱ እንደመሆኑ ያስተማረበት አብይ ክፍል በዚህ በሦስተኛው ሳምንት የአብይ ጾም በሰፊውይነገራል። አይሁድ የእውነትን ቃል ሰምተው አንገታቸውን እንዳደነደኑ፤ ሥጋዬን የበላደሜን የጠጣ የዘላላም ሕይወት አለው በሚለው የጌታ ትምህርት እንዴት ሊሆን ይችላልበማለት ማጉረምረማቸው በዚሁ ክፍል አብሮ ተጠቃሽ ነው። ጌታም እስራኤል በምድረበዳ በልተውት የነበሩት መና እና እውነተኛው የሕይወት እንጀራ ያላቸውን ልዩነትበማነፃፀር እንዲህ ሲል
አስተምሯቸዋል፦
አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።
እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። የሕይወት
እንጀራ እኔ ነኝ። አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤ ሰው ከእርሱ በልቶ
እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ
እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት
የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። እንግዲህ አይሁድ። ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ
ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላልብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ። ስለዚህ ኢየሱስ
እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ
ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም
የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ
እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ
በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ
ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል። ከሰማይ
የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን
እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ።
ዮሐ.፮፡፵፮-፶፱
በዚህ በሦስተኛው ሳምንት በቅዳሴ ላይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉውምንባብ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም
ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥
አካሉ ግን የክርስቶስ ነው። ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም
ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ።
እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና
በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ
ያድጋል። ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ
ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም
እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁእነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ይህ
እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥
ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም።
ቆላ.፪፡፲፮-፳፫
ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን
ይጠቅመዋልእምነቱስ ሊያድነው ይችላልንወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን
ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥
ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው።
አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም
እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል። እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ
ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል። አንተ
ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህንአባታችን
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ
ትመለከታለህንመጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ
ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ሰው በእምነት ብቻ
ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ። እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ
መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ
ነው። ያዕ.፪፡፲፬-፳፮
በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ
ሰው ነበረ። እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ
ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ
እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታ
ሆይ፥ ምንድር ነውአለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር
ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ። አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ
የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው
በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።
የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሎዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ
እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ
ኢዮጴም ላካቸው። እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት
ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ። ሐዋ.፲፡፩-
በዚህ በሦስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦

በግዕዝ፦ እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

በአማርኛ፦ የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ። መዝ.፷፰፡፱

በዚህ በሦስተኛው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦

ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ
ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ። የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም
ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ
ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም
ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ
ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። ስለዚህ አይሁድ
መልሰው። ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህአሉት። ኢየሱስም መልሶ።ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው። ስለዚህ አይሁድ። ይህቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀንታነሣዋለህንአሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታንከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውንቃል አመኑ። በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎችበስሙ አመኑ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክርአያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።ዮሐ.፪፡፲፪-፳፭

Post Bottom Ad