ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት?? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Monday, March 31, 2014

ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት??

አባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን  የሚዘልፈውአባ ሰላማየተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ 
በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም
የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝበማለት ይመስለናል ለብሎጉ
ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም:: 


አባ ሰላማብሎግ 1992 / ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድንእንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ
ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል::ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል
ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙያዛል” 
የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም:: ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድእንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል
የሚል እምነት አለን::


በአጽዋማት ወቅት በሚሰበሰበው የቁርስ ዳቦ አማካኝነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎችቤተ ክርስቲያን እንደተሰሩ ሰምተናል አይተናልም:: 
የሰንበት ትምህርት ቤተ አዳራሽ በሌለባቸው አጥቢያዎችደግሞ የመማርያ አዳራሾች 
እንደተሰሩ የአይን ምስክሮች ሲናገሩ እንሰማለን:: ታድያ ተሐድሶዎቹ ከቁርስ ዳቦ በመሸጥ የተሰበሰበው ገንዘብበእኛ ኪስ ለምን አልገባምለማለት ይመስላልአባ ሰላማብሎግ አምርሮ ተቃውሞታል::

ለመሆኑአባ ሰላምብሎግ እና ሌሎች መሰሎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው?ለምንስ ይጠሉታል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል:: በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦስት ከፍለን እንያቸው::

. ማኅበረ ቅዱሳን በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ:: እነዚህም:-
 - ተሐድሶ መናፍቃን ( ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ)
 - መናፍቃን የውጭ (“ጴንጤ”)
 -  አክራሪ እስላሞች 
እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል:: እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም 
በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ፤ የማኅበሩን መኖር የእግር
ላይ እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ:: ማኅበረ ቅዱሳንኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናልብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው። ሌሎቹ ሁለቱን የውስጥ(ተሐድሶ) እንዲሁም የውጭ መናፍቃን ግብራቸው እና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ እንደሚቃወማቸው ያውቃሉ:: ስለዚህ የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም
የማኅበረ ቅዱሳን ስም ሲያነሱት እናያቸዋለን:: ለዚሁምአባ ሰላማብሎግ ማየት በቂ ማስረጃ ነው:: ሁለቱንም የመናፍቃን ቡድን የተዋሕዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ፤ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላም ጋር በመተባበርም ቢሆን ማኅበሩን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች

ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠሉታል የሚል እምነት አለን:: እነዚህኞቹ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው።እነ ወይዘሮ እጅጋየሁ እና ቡድኖቻቸውም እዚህ ቡድን ላይ መድበናቸዋል:: ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ደግሞ ተግባራቸውን
ሥለሚቃወም ነው:: እንዲሁም ደግሞ ያጋልጠናል ብለውም ይሰጋሉ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ በተቃራኒው ይህን በማይፈልጉት ጥቅመኞ ማኅበሩን እንዲጠሉ አድርጓቸዋል:: ይኸው እነዚህ ሆዳቸው አምላክየሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ ስም የማጥፋት
ዘመቻ ቀጥለውበታል::

የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች

እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩን ስም እንኳ የሰሙት ከተሐድሶ መናፍቃን፣ ከተለያዩ ሚድያዎች እንዲሁም ደግሞ ከአክራሪ እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ ብቻ የሰሙትን ወሬ ይዘው ማኅበረ ቅዱስንን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው? ዓላማው ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቱስ
የትኛው መዋቅር ሥር ነው? ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ አይጠፉም:: ነገር ግን ለመጠየቅ ተዘጋጅተው ምላሽ ለማግኘት አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እንገምታለን።

ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ ለሚነሱ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ምላሽ ቢሰጥ መልካም ነው እንላለን:: ሐሰት ተደጋግሞ ሲነገር እውነት ይሆናል እንደሚባለው ማኅበሩ በተመለከተ የሚወጡ የሐሰት ውንጀላዎች በተቃራኒ ማሰተባበያ ቢሰጥባቸው የሚል እምነት አለን::



እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።

Post Bottom Ad