& ‹‹ብዙ ከመብላትና ብዙ ከመጠጣት የማይከለከል ሰዉ ሰይጣነ ዝሙትን ድል አይነሳዉም፡፡››(ማር ይስሀቅ)
& ‹‹መመጽወትና መጾም ለነፍስ ህይወትን ለስጋ ጤንነትን ይሰጣል፡፡››(አንጋረ ፈላስፋ)
& ‹‹ያለ ጸሎት መንፋሰዊ ነኝ የሚል ሰዉ እሳት መካከል ገብቶ የሚጫወትን የ እሳት እራትን ይመስላል፡፡››(ማር ይስሐቅ)
& ‹‹ልጀ ሆይ አንተ በራስህ ላይ ስትፍረድ እግዚአብሔር ፍርዱን ያነሳልሃል አንተ በራሰህ ላይ ባትፈርድ ግን እግዚአብሔር ይፈርድብሀል(ታላቁ መቃሪዮስ)
& ‹‹በወንድሙ ወድቀት የሚደሰት ሰዉ ተመሳሳይ ወድቀት ይጠብቀዋል››(ቅዱስ ኤፍሬም)
& ‹‹የወንድምህን ኃጢአት መሸፈንና ያእርሱን ኃጢአት እንደራስህ አድርግህ በእርሱ ፋንታ መሞት ካልቻልክ ቢያንስ ስለ ኃጢአቱ አትፍረድበት››(ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
& ‹‹በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ታገኝ ዘንድ ታገስ››(ማር ይስሐቅ)