"የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም" - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Friday, February 28, 2014

"የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም"

የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም አለው ምሳሌውን ግልጽ ለማድረግ የሚከተለውን ስዕላዊ መግለጫእንመለከት እና ወደ ትንታኔው እንሂድ።

ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ግራና ቀኝ ሲመታ ስንመለከልት ጌታችንበአይሁድ እጅ በጥፊ መታቱን ያስታውሰናል።



. ሰፊው የከበሮው አፍ
 
የመለኮት ምሳሌ ነው።ይህ የከበሮ አፍ የጌታችንን የባህሪ አምላክነት ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን አስልጣኑ ወሰንድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው።የ አፉን መስፋት ስንመለከት  አጭር ቁመት በጠባብ ደረትተወስኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በህልውና በመለኮት ባሕርይ አባቱ ከአብ ባሕርይ ሕይወቱከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን እናስባለን።

. ጠባቡ የከበሮው አፍ
  
የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ እየተቁረቁረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ የከበሮ አፍ የወልድእግዚአብሔርን በጠባብ ደረት  አጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥ የሚያመለክተን ነው።ፍጥረታትን ሁሉየሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ስጋን ተዋህዶ ተገልጧል።ይህንን ጠባብየከበሮ አፍ ስንመለከት ሁሉን የሚገዛ እሱ  አጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን እናስባለን። ዩሐ፤፩፡፩-፩፬

. ከበሮው የሚለብሰው ጨርቅ
  
ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅ ደግሞ በዕለተ ዓርብአይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ)ምሳሌ ነው። 
''
ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ 26:28

. በከበሮው ላይ የተለጠፈው ጠፍር
 
በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይ ስንመለከት በጌታችንጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን።
''
እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ 21(22):16 እንዲል ጌታችን አጥንቱእስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስል ተገርፏልና የዚያ ምሳሌ ነው።

. የከበሮው ማንገቻ
 
የከበሮውን መምታት ስናስብ  አንገታችን የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው የጎተቱበት ገመድ ምሳሌነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራኒዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድየእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል መንገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን ገመድእናስታውሳለን።

Post Bottom Ad