"ቅዱስ ማቴዎስ ማነው?" - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Monday, February 3, 2014

"ቅዱስ ማቴዎስ ማነው?"

የማቴዎስ ወንጌል
 • -       በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማቴዎስ ወንጌልን የጻፈው ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ማቴዎስ ነው።  “ማቴዎስ”  ማለት  የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው። 12ቱ ሐዋርያት ስም ዝርዝር የሚገኘው ከአራቱም ትቅሶች ውስጥ ማቴዎስ የሚለው ስም ተመዝግቦ ይገኛል።  ማቴ 10፤2-4


 • -       ቅዱስ ማቴዎስ የጌታን ነገር በእብራይስጥ ቋንቋ ጽፏል።
 • -       የማቴዎስ ስሙ በራሱ ወንጌል “ማቴዎስ” ተብሎ ሲጠራ በማርቆስ እና በሉቃስ ወንጌላት ውስጥ በሚገኘው ትይዩ ታሪክ ደግሞ “ሌዊ” ተብሎ ተጠርቷል። 
 • -       ከትንት ጀምሮ ባለው ታሪክ እና ትውፊት መሠረት “ማቴዎስ” እና “ሌዊ” ከቀድሞ ጀምሮ ይጠራበት የነበረው ስሙ “ማቴዎስ” ደግሞ ጌታን ከተከተለ በኋላ የተጠራበት ስሙ እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ።

የማቴዎስ ነገድ
 • -       ከይሳኮር ነገድ የሆነ፤ ከናዝሬት ሃገር የሆነ
 • -       የአባቱ ስም ዲቁ
 • -       የእናቱ ስም ካሩትያስ
 • -       በዚህ ታሪክ መሰረት የማቴዎስ ነገዱ ነገደ ይሳኮር ሃገሩ ደግሞ ናዝሬት እንደሆነ ስለቤተሰቡ ደግሞ አባቱ ዲቁ እናቱ ደግሞ ከሩትያስ እንደምትባል ተገልጧል
 • -       ነገር ግን በማርቆስ ወንጌል ውስጥ የማቴዎስ አባቱ “እልፍዮስ” እንደሆነ ተመዝግቧል (ከዚያ አልፎም በመቅረጫው የተቀመጠ የእልፍዮስ ልጅ ሌዊን አየው የሚል ነው) ማር 2፤14 ስለዚህ በመቅድመ ወንጌል የተገለጠው “ዲቁ” የሚለው ስም ምናልባት “የማቴዎስ” አባት  “እልፍዮስ” ሌላ ስሙ ሊሆን ይችላል።


ስለ ቅዱስ ማቴዎስ መጠራት

በራሱ ወንጌል ውስ በሚገኘው የሐዋርያት ስም ዝርዝር ውስጥ ወማቴዎስ መጸብሐዊ (ቀራጩ) ማቴዎስም ተብሎ ይጠራል።
ቀራጭ የተባለበት ምክንያት

 • -       ቀራጭ የተባለውም በሥራው የሮማውያን ግብር ሰብሳቢ ስለነበር ነው።  የቀራጭነት ሥራውን ይሰራ የነበረው በገሊላው ገዥ በሄሮድስ አንተጳስ ሥር ሲሆን ቦታውም በገሊላ ባሕር በምትገኘው በቅፍርናሆም ከተማ ነበር።   ማር 1፤1
 • -       ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሲያልፍ በመቅረጫው ተቀምጦ አገኘውና “ተከተለኝ” ብሎ ጠራው
 • -       ቅዱስ ማቴዎስም ሁሉን ትቶ ተከተለው።  በቤቱም  ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ባሉበት ለጌታሽን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ታላቅ ግብዣ አደረገለት።
 • -       ከዚህም የምንረዳው ማቴዎስ ጌታችንን በተከተለ ጊዜ ንብረት የነበረው በመንግስት ባለስልጣኖች ፤ በሥራ ጓደኞቹ፤ በቀራጮች፤ በኃጢአተኞች እንዲሁም በጻፎችና በፈሪሳዊያን ዘንድ ታዋቂ የነበረ ሰው ነው።
 • -       ቅዱስ ማቴዎስ የጌታ ደቀመዝሙር መሆኑን ግብዣ በማድረጉ ለሁሉም ግልጽ አደረገ።


ቅዱስ ማቴዎስ የት አስተማረ?

 • -       4ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው አውሳብዮስ ዘቂሳርያ የተባለው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ ማቴዎስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌልን የሰበከው ለዕብራውያን ሲሆን ከዚያም ለሌሎሽ ሕዝቦች ሰብኳል ብሎ ጽፏል።  
 • -       በገድለ ሐዋርያትና  በመጽሐፈ ስንክሳር ላይ ሐገረ ካህናት በተባለ ቦታ እና በአካባቢው እንደሰበከ ተመዝግቧል።


የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የተጻፈበት ቦታ የት ነው?

 • -       የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈበት ቦታ ፍልስጥኤም ሲሆን ወንጌሉን ጽፎ የፈጸመበት ቦታ ደግሞ ሕንድ ነው
 • -       ወንጌሉን የጻፈበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን ክርስቶስም ያስተማረበት ቋንቋ አርማይክ ነው
 • -       የግዕዝ መጻሕፍት የተተረጎመው ከዕብራይስጥ ነው
 • -       የተጻብፈበትን ዘመን በተመልከተ በግዕዝ መጽሐፍት ውስጥ ከተገኙት ማስረጃዎች ጌታ ካረገ በኋላ 8ኛው ዓመት ተፈጽሞ ዘጠነኛው ዓመት ሲጀምር ቀላውድዮስ ቄሳር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት እንደነበር እንገነዘባለን
 • -       ከጌታ ዕርገት በፊት 33 ዓመት
 • -       ከጌታ ዕርገት በኋላ 8 ዓመት
 • -       በአጠቃላይ ድምር 41 ዓመት ይሆናል

-       ስለዚህ በዚሁ መረጃ መሠረት የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው በ41 ዓ.ም መሆኑ ነው።  ይህም ዘመን የማቴዎስ ወንጌል ከአራቱም ወንጌላት እንዲሁም በጠቅላላ ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ በቅድሚያ የተጻፈ እንደሆነ ያሳያል።


ይቆየን……….

Post Bottom Ad