ቅዱስ ማቴዎስ ማነው (ክፍል ሁለት) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Saturday, February 22, 2014

ቅዱስ ማቴዎስ ማነው (ክፍል ሁለት)

የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የተጻፈበት ዓላማ

የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌልን ስናጠና ቅዱስ ማቴዎስ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክና ሥራ በወንጌሉ ውስጥ ለዕብራውያን የጻፈው በሚከተሉት ዓላማዎች መሆኑን እንረዳለን።
·         ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳዊት ትውልድ የተወለደ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት ነው።  ይህንንም ሃሳብ ትውልዱን በመቁጠር ጌታ ራሱን “የሰው ልጅ” መጥራቱንና በሌሎች ሰዎች “የዳዊት ልጅ” ተብሎ መጠራቱን በመመዝገብ ያስረዳል። ማቴ 1፤1-17 8፤20 9፤6 9፤27 12፤27 16፤13 17፤12 18፤11 25፤31 26፤64
·         በሰዎች ዘንድ ጌታ ከነቢያት አንዱ ቢባል እንኳ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲታወቅ ለማስረዳት ነው። ማቴ 3፤17 8፤29 11፤25-27 14፤33 16፤13-17 17፤5 27፤40 43፤54

·         
በ   ሕግና በነቢያት መጽሐፍት በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ የተነገሩትን ትንቢታዊ ቃላት እየጠቀሰ ፍጻሜአቸውን ለማሳየት ነው።  ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ውስጥ ከ60 ጊዜ በላይ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን ጠቅሷል።  ከእነዚህም ብዙዎቹ ሕግና ነቢያት ስለ ክርስቶስ መሲህ ምን እንደተናገሩ የሚገልጹ ናቸው።  የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በመጀመሪያ የተዘረዘረው የብሉይ ኪዳንን ፍጻሜ አሳይቶ ወደ ሐዲስ ኪዳን የሚያሸጋግር ድልድይ የሆነ ወንጌል በመሆኑ ነው።  ስለዚህ የማቴዎስ ወንጌል ሕግና ነቢያትን በመጥቀስ ኢየሱስ እርሱ እንደሚመጣ ይጠበቅ የነበረውን መሢህ ክርስቶስ መሆኑን ለዕብራውያን ያስረዳል። ማቴ 1፤22 2፤4 4፤16 11፤2-5 12፤17-21 13፤35 16፤16 21፤522፤41-46 27፤9

የወንጌሉ ጥናት

·         የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል 28 ም ዕራፎች እና 1061 ቁጥሮች ያሉት መጽሐፍት ነው።
·         ከዚህ ክፍል ውስጥ የ እነዚህን ም ዕራፎች ቁጥሮች ቃል በማንበብ የወንጌሉን ይዞታና አከፋፈል እናጠናለን።

        ይዞታው
·         አራቱም ወንጌላት ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ነገሮችን ይዘዋል እነርሱም
1.      የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርቶስን ታሪክ
2.     ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸው ተአምራት
3.     ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምህርቶች ናቸው።
28ቱን የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ም ዕራፋት በማንበብ እነዚህን ሦስት ይዞታዎች እንደሚከተለው እናጠናለን።

ይቆየን……..

Post Bottom Ad