የወንጌል አገልግሎት ሰባኪያን በእነማን? ለእነማን? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, January 29, 2014

የወንጌል አገልግሎት ሰባኪያን በእነማን? ለእነማን?

    “የወንጌል አገልግሎት በእነማን ለእነማን?” የሚለውን ጥያቄ ለመመልከትና መልስ ለመስጠት በቅድሚያ ወንጌልና የአገልግሎት ትርጉምን መመልከት ጠቃሚ ይሆናል፡፡

በዚህም መሠረት “ወንጌል” የሚለው ቃል ዮአንጌሊዮን ከሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የምሥራች ቃል ማለት ነው፡፡ ወንጌል ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፣ በሥጋም እንደተወለደ፣ ስለሰው ልጅ ኃጢአትም ከሞት በኋላ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሣ ያበስራል፡፡ ሮሜ.1÷3-4 ወንጌል በብሉይ ኪዳን የተነገረውን በእምነት የሚገኘውን የእግዚአብሔር ጽድቅ ያበስራል፡፡ ሮሜ.1÷2-2 ገላ.3÷5-81 ማር.10÷44-45
ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሁሉ፡-
ሀ/ የእግዚአብሔር 
ለ/ የክርስቶስ (1ተሰ.32፤ ሮሜ.15 እና 16) 
ሐ/ የወንጌል
መ/ የሐዲስ ኪዳን
ሠ/ ለየቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ናቸው፡፡ (ኤፌ.3÷7 ቆሮ.3÷6 ቆላ.1÷25)

ከነዚህም ሁሉ በላይ ክርስቶስ ለወንጌል አገልግሎት ታላቅ ምሳሌነትንና አብነት የሚፈጸመው በተለያዩና ለዚህ ተግባር በተመረጡ በተዘጋጁም ሰዎች ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ “እኔ ቅዱስ እንደሆንሁ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፤” (ዘሌ.19÷2) ሲል እግዚአብሔር ለሰዎች የተናገረውን ወደ ሰዎች ለማድረስና ሰዎችን ለቅድስና ለማዘጋጀት ከሕዝቡ መካከል ተመርጠው ለቅድስና አገልግሎት  የሚሾሙ ሰዎች ነበሩ፤ዕብ.5÷1-4 እግዚአብሔር በመልኩ በአርአያው የፈጠረው ሰው ቅዱስ ይሆን ዘንድ በትምህርትና በእምነት በመምራት ሰውን ወደ ቅድስና መንገድ የሚያደርስ ንጹሕ የትምህርት አገልግሎት የሚያበረክቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ይፈለጋሉ፡፡ ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ የሚል የእግዚአብሔር ድምፅም ይሰማ ነበር፡፡ ኢሳ.6÷8 በብሉይ ኪዳን የደብተራ ኦሪት አገልግሎት ይፈጽሙት የነበረው አገልግሎት የኃጢአት ሥርየትና የደኅንንት መሥዋዕትን በማቅረብ ሰውን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ማድረግ ነበር፤ ዘሌ.9÷1-4 የብሉይ ካህናትና ነቢያት አገልግሎት ሁሉም በሰውና በእግዚአብሔር በሰውና በሰው መካከል ግንኙነት እንዲኖር የሰውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወት በትምህርት መለወጥ ነበር፡፡ አገልግሎታቸውን የሚፈጽሙበት መንገድና ስልት ግን የተለያየ ነበር፡፡ ይኸውም ነብያት በሕዝብ ፊት በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝብ በመቆም ነበር፡፡ ዘዳ.18÷18፣ ዕብ. 8÷1-5 

ሆኖም እንደ ኦሪቱ ሕግና ሥርዓት ለሕዝቡ የኃጢአትና የደኅንነት መሥዋዕት ለማቅረብና በእግዚአብሔር ፊት ለመጸለይ ከተሠየሙት ካህናትና ሌዋያን መካከል አገልግሎታቸውን በትክክል የፈጸሙ ጸሎታቸው መሥዋዕታቸውና ማዕጠንታቸው ቅድመ እግዚአብሔር እንደደረሰላቸው ከመልአክ ቃል የሰሙና ተስፋ የተነገራቸው አሉ፡፡ ሉቃ. 1÷5-14

አንዳንዶቹ ግን የሚሰጡት አገልግሎት ጠቃሚ በመሆን ፈንታ ራሳቸውንም ሌላውንም የሚጎዳ ሆኖባቸዋል፤ምክንያቱም፡-
1ኛ. የቃል ብቻ እንጂ የተግባር ሰዎች ባለመሆናቸው የሚናገሩትንና የሚያስተምሩት በምሳሌነት በሥራ የማይገልጡ ለሌላው ግን ከባድ ሸክም የሚጭኑ ፡-ስለሆነ ማቴ 23÷3 
2ኛ. ውዳሴ ከንቱ የሚያጠቃቸው አስመሳዮችና ግብዞች ስለነበሩ ቍ.5
3ኛ. በአገልግሎትና ጸሎት ርዝመት በማመካነት የሃይማኖት መበለቶችን ቤት የሚበዘብዙ ጨካኞች የቤተ እግዚአብሔር ቀሳጤዎች ስለሆኑ፤ ቍ.14
4ኛ. በሕግ የታዘዘውን ዋና ዋና ቁም ነገር ፍርድን ምሕረትንና ታማኝነትን ወደ ጎን በመተውና የግል ጥቅምን ብቻ በማሳደድ ገበያ ጠርገው ከሚያድሩ ምስኪናን ሳይቀር የቅመማ ቅመም ማለት የአዝሙድ፣ የእንስላልና የከሙን አሥራት፣ በኲራት በመጠየቅ የእግዚአብሔር ሕዝብ ያስቸግሩ ስለነበረ ማቴ.23÷23
5ኛ. ለመሆኑ ያይደለ መስሎ ለመታየት የሚጥሩ ትምክህተኞችና ተመጻዳቂዎች ጻድቃን ስለነበሩ ማቴ.25÷29 ሉቃ.1811-14 ፍርድ ምሕረትና ታማኝነት የእውነተኛ እምነትና አምልኮተ እግዚአብሔር መመዘኛ የሆነ የቅድስና ተግባሮች ናቸው፡፡ ሆሴዕ.6÷6

በቀና እምነት አምልኮተ እግዚአብሔር ለመፈጸምና ለማስተማር የካህናት ቅን አገልግሎት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ሕይወት ለመጠበቅና የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የአሥራት በኲራት አስተዋጽኦም አስፈላጊ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የዘመነ ብሉይ ፈሪሳዊያን ካህናት ከማገልገል ይልቅ መገልገልን ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የግላቸውን ጥቅም ለማስቀደም በሚያደርጉት ጥረት ፍርድ ምሕረትና ታማኝነት በጎደለው ጥያቄ የኦሪት እምነት ተከታዮችን ሁሉ የአሥራት በኲራት የሚያደርሰውን መንገድ ሁሉ ጥርጊያ ማድረግ ነው፡፡ ማቴ.3÷3፤ ሉቃ. 3÷4-6
የሚቀጥለው አሳብ
“የዘመኑ የወንጌል አገልግሎት በእነማን? ለእነማን?” የሚለው አሳብ ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ማለት ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ሕዝብን በትምህርት ያገለግሉ የነበሩ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ሁነው ተገቢውን አገልግሎት የሰጡ በእግዚአብሔር የተመረጡ የተጠሩና የተላኩ ሰዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ዛሬም የወንጌል አገልግሎት መፈጸም የሚገባው ራሳቸውን በትምህርትና በሥነ ምግባር በአዘጋጁ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ በአላቸውና ከቤተ ክርስቲያን በተላኩ አገልጋዮች ካህናትና መምህራን መሆን አለበት፤ የወንጌል አገልግሎት እንዲደርስባቸው ጥረት የሚደረግላቸውም “አርእዩነ ፍኖተ ወንሑር ቤቶ … መንገድን አሳዩን ወደ ቤቱም እንሂድ፤” (ኢሳ.2÷3 ሚክ. 4÷2) እያሉ ለሚጠይቁና የእግዚአብሔርን ትድግና ለሚፈልጉ ሁሉ ነው፡፡

ብዙዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ትክክለኛውንና ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያደርሰውን መንገድ የሚመራቸው ያላገኙ በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግንኙነት እየተሰነካከለባቸው የሚቸገሩ አሉ፣ በመሆኑም በሰውና በእግዚአብሄር መካከል የሚኖረው ግንኙነት የዘለዓለማዊው ሕይወት መንገድ ስለሆነ ይህ መንገድ የተስተካከለ ጥርጊያ ጎዳና እንዲሆን፤ ወይም ደግሞ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግንኙነት እንደ ዛፍና እንደ ቅርንጫፍ ስለሆነ ቅርንጫፉ ከዛፉ እንዳይለይና ፍሬ ሳያፈራ እንዳይቀር በቤተ ክርስቲያን ወደ ሕዝብ የሚላኩ የዘመኑ የወንጌል አገልጋዮች በማስተዋልና በብህልነት በየዋህነትም የማስተማርና እስከ መሥዋዕትነት ድረስ የማገልገል ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ (ዮ. 15÷4-6፤ ማቴ.10÷16)

በሰውና በሰው መካከል የሚኖረው ግንኙነት የሰላም፣ የፍቅር፣ የመረዳዳትና በመልካም የመተሳሰብ ግንኙነት ፍትሕ፣ ምሕረትና ታማኝነት የሰፈነበት እንዲሆን ማድረግ ከዘመኑ የወንጌል አገልጋዮች የሚጠበቅ አገልግሎት ነው፡፡

የዘመኑን ሕዝብ እንዲያስተምሩና እንዲያገለግሉ የሚላኩ ሁሉ የሚያገለግሉትን ሕዝብ የትምህርት ፍላጎት ለማርካት ይቻሉ ዘንድ በሚከተለው ሁኔታ የተዘጋጁ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ይኸውም፡-
1ኛ. “ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም” እንደተባለው ከሁሉ በፊት በቤተ ክርስቲያናችን የትምህርት ተቅዋማት የሚሰጠውን ትምህርት ለወንጌል አገልግሎት በሚያበቃ ሁኔታ የተማሩና የታወቁ 
2ኛ. አላማቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ÷
3ኛ. አላማቸውን ጠብቀው የሚራመዱ÷
4ኛ. የወንጌል ብርሃን ከዕንቅብ በታች ሳይሆን በመቅረዙ እንዲያበራ ማድረግ የሚችሉ፣ ማለት የወንጌል አገልግሎት ሥራ በግል ጥቅም ሩጫ መጋረጃ በታች እንዳይጣል የሚያደርጉ÷
5ኛ. ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ትምህርትና ታሪክ ቀናኢነት ያላቸው÷
6ኛ. ያሉበትን ጊዜና የጊዜው የወንጌል አገልግሎት የሚጠይቀውን ግዴታ የተረዱ÷
7ኛ. ከቃል ስብከት ጋር የተግባር ስብከት በይበልጥ አስፈላጊና ጠቃሚ መሆኑን የተገነዘቡና በአኗኗራቸው፣ በአሠራራቸውና በአካሄዳቸው ሁሉ ለሚያገለግሉት ሕዝብ መልካም አርአያና ምሳሌ በመሆን ለማገልገል የሚችሉ መሆናቸው÷
8ኛ. በዚህ በተለዋዋጩ ዓለም ላይ ምንጊዜም የማይለወጠውን ቃለ እግዚአብሔር የዘመኑ ሕዝብ የሚረዳው ቋንቋና የአቀራረብ ስልት በመስበክ በሕዝብ ጆሮ ተሰሚነትና ተቀባይነት ያለው ትምህርት ለማስተማር እንደሚችሉ የተመሰከረላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተላኩ መሆን አለባቸው፡፡ “የወንጌል አገልግሎት ለእነማን?” ለሚለው አሳብም መልሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንግዲህ ሂዱና በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ ያዘዝኋችሁንም እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ (ማቴ.28÷19 እና 20) ሲል ለአዘዛቸው ለሰው ልጆች ሁሉ ነው፡፡

የሰው ልጅ እንዲጠፋ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ እርሱ ዓለሙን (ሰውን) ይወድዳልና የሰው ልጆች ሁሉ በእርሱ እንዲያምኑና የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኙ አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ ሰጥቶላቸዋል፡፡ (የሐ.3÷15-18፤ ሮሜ. 5÷8፤ 8÷32) ታዲያ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የክርስቶስንም ቤዛነት በመረዳት ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡና የተዘጋጀላቸውን መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርሱ የሚያበቃ የተሟላ የወንጌል አገልግሎት እንዲደርሳቸው ያስፈልጋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ በርካታ ሕዝቦች ትክክለኛ የወንጌል አገልግሎት ይፈልጋሉ፤ ትክክለኛውን እምነት ማወቅና ማመንም ይፈልጋሉ፤ በመሆኑም የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ለሁሉ ነውና፤ “…የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ ነገር ግን ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?”  ሮሜ.10÷11-14 ተብሎ እንደ ተጻፈ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር እንዲያምኑና ጌታ በሚገለጥበት ጊዜ ከኅፍረት እንዲድኑ ፣ የእግዚአብሔንም ስም በእምነት እብዲጠሩና የጻጋው ተሳታፊዎች እንዲሆኑ መምህር እንዲላክላቸውና የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ማድረግ ከቤተክርስቲያን መጋቢዎች የሚፈለግ ግዴታቸው ብቻ እንዲፈጽሙ በማስገደድ ለግል ጥቅማቸው ብቻ ይተጉ ስለነበሩ “እለ ፃፁተ ወገመለ ትውኅጡ …ትንኝን ወይም ጥቃቅኑን ነገር የምታጠሩ ግመልን የምትውጡ” የሚል የዘለፋ ቃል ተነግሮባቸዋል፡፡

ብዙዎቹን የዘመነ ብሉይ ካህናት ለዚህ ዓይነት ዘለፋ ያጋለጣቸው የግል ጥቅምንና ክብርን ፈላጊነታቸውና ፍርድ÷ የምሕረትና ታማኝነት የጎደላቸው ጨካኞች መሆናቸው ነው፡፡

ለዚህ ጭካኔ የዳረጋቸው ደግሞ ጊዜው ዕውቀትና ሥልጣኔ ያልተስፋፋበት ስለነበረ የነበራቸው ጥቂት ኦሪታዊ ትምህርትና ዕውቀት ለውዳሴ ከንቱና ትምክህት ዳርጓቸው ስለ ነበረ ነው፡፡ እንዲሁም የነበሩበት ሥርዓት ወንጌላዊ ማለት የፍርድ፣ የምሕረትና የይቅርታ ሥርዓት ስላልነበረ ርኅራኄና ምሕረት አልባ አድርጓቸው ነበር፤ (ሉቃ.10÷30-38)

በአንጻሩ ደግሞ በዘመነ ብሉይም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሕግ የሚፈልጉና የሚያደርጉ፣ ለሕዝቡ ፍርድንና ሥርዓትን ለማስተማር ልባቸውን አዘጋጅተው የነበሩና የእግዚአብሔር እጅ እየረዳቸው ቃላቸው፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መልካም አገልግሎት በመስጠት ግዴታቸውን የተወጡ መምህራን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ (ዕዝራ 7÷9 እና 10) “የወንጌል አገልግሎት በእነማን? ለእነማን?” ለሚለው ርዕስ መግቢያ በዘመነ ብሉይ የነበረውን የኦሪት መምህራንና የአገልግሎት ሂደት ከዚህ በላይ በመጠኑ ከተመለከትን ከዚህ ቀጥለን ደግሞ በዘመነ ሐዋርያት የነበረውንና በአሁኑ ጊዜ ያለውን የወንጌል አገልግሎት እንመለከታለን፡፡ 

የወንጌል አገልግሎት በመጀመሪያ የተመሠረተው በራሱ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪትን አሳልፎ መሥዋዕተ ወንጌልን በመተካት ራሱ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ሁኖ በታሱ መሥዋዕትነት በሌላ በማንም ሊፈጸም የማይቻለው ዓለምን የማዳን አገልግሎት በመስቀል ላይ ፈጽሞአል፡፡ የመዳን የምሥራችን የምታበስር ሕገ ወንጌልንም ሠርቶአል፡፡ የምእመናን አንድነት የሚገለጥባት፣ በሁሉ ያለች አንዲት ቤተ ክርስቲያንንም መሥርቶአል፡፡ በራሱ መሥዋዕትነት የተቤዠውን ዓለምና በመስቀል ላይ በአፈሰሰው ደሙ የመሰረታትን ቤተ ክርስቲያንም ያለ አገልጋይና ያለ መምህር አልተውም፡፡ የእርሱን አርአያ ተከትለው ዓለምን የሚቀድሱ ቤተ ክርስቲያንን መንጋውን የሚጠብቁ የወንጌል አገልጋዮች የሚሆኑ ካህናትን ለማስነሣት ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈሳዊ ኃይልን የታጠቁ ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት መረጡ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና የወንጌል አገልጋዮችም የእርሱን አርአያ ተከትለው ለወንጌል አገልግሎት በግዴታ ሳይሆን በውዴታ፣ በኲራት ሳይሆን በትሕትና፣ እንደገዥ ሳይሆን እንደ አገልጋይ፤ ለገንዘብም ሳይሆን ለክርስቶስ ፍቅር ብለው በቅንነትና በትጋት መሥራት እንደሚገባው ምሳሌነትን አሳይቷል፡፡ (ማር.10÷42-45፤ ዮሐ. 13÷4-5 እና 12-16)

በዚህም መሠረት የወንጌል አገልግሎት ወደ ዓለም ሁሉ እንዲደርስ የሆነው በባለቤቱ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ጥሪና ምርጫ በተደረገላቸው ቅዱሳን ሐዋርያት ነው፤ ይህንንም ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ እንዲህ ሲል ይገልጣል፡- “…የወደዳቸውን ጠራ፤ ወደ እርሱም መጡ፤ ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን መርጦ ሐዋርያት አላቸው፡፡” (ማር.3÷13-14)

እነዚህም ጋር ሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ለወንጌል አገልግሎት ተመርጠዋል፣ ተጠርተዋልም፤ ሁለት ሁለትም ሆነው ተልከዋል፡፡ (ሉቃ. 10÷1)

እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትና ሰባ ሁለት ደቀ መዛሙርት ከተጠሩ፣ ከተመረጡና ለወንጌሉ አገልግሎት ከሚልካቸው ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለሦስት ዓመታት ተኩል ለቆዩ፣ ከተማሩና ለወንጌል አገልግሎት ብቃት ያላቸው መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ  ተላኩ፤ ወንጌል አገልግሎትን በተገቢው ሁኔታ ለማዳረስ የሚያስችል ሥልጣንም ተሰጣቸው፡፡ (ማቴ.10÷1፣ ማር. 3÷13-15፣ ሉቃ. 9÷1-3)

እነዚህ ወንጌል አገልጋዮች ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትና ሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ያለ ዋጋ የተቀበላችሁት ያለ ዋጋ ስጡ ተብለው በተላኩት መሠረት በወንጌል አገልግሎት ትርፍና ልዩ ጥቅም ሳይፈልጉ አገልግለዋል፤ እንዲያውም የወንጌል አገልግሎት የራስን ጥቅም ብቻ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የሚደረግ ሩጫ ሳይሆን የሌሎችን መንፈሳዊና ሥጋዊ ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያስችል የመጋቢነት ሥራ መሆኑን በመገንዘብ የነበራቸውን ሁሉ ትተው እውነተኛውን አምላክ ተከትለው መልካም የወንጌል አገልግሎት ፈጽመዋል፡፡ በዚህም እጥፍ ድርብ ዋጋ እንደሚያገኙ የማይታበል ተስፋን ተቀብለዋል፡፡ (ማቴ. 19÷27-30)

የወንጌል አገልግሎት ዋና ዓላማ፡- “የሰው ልጅ ሊያገለግል እንጂ ሊያገለግሉት አልመጣም” (ማቴ.20÷28) በሚለው አምላካዊ መርሆ መሠረት የወንጌልን ትምህርት በተገልጋይነት ሳይሆን በአገልጋይነት፣ ለራስና ለግል ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት ሳይሆን የማኅበረሰብን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወት ጠቀሜታ በማስቀደም ሰዎችን ሁሉ በማስተማር በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ማነጽና ሁሉ በማስተማር የእግዚአብሔርን የማዳን መንገድ መልካም ሥነ ምግባርን በተላበሰ አገልግሎት ማሳየት ነው፡፡ (ማቴ. 5÷16)

ከዚህም ጋር በሰውና በእግዚአብሔር፣ በሰውና በሰው መካከል ሊኖር የሚገባውን የግንኙነት መንገድ ማሳየትና ያም መንገድ የተስተካከለ እንዲሆን መስናክሉንና ዕንቅፋቱን ማስወገድና ወደ እግዚአብሔር “የየአውራጃው ኤጴስ ቆጶሳት ሁሉ አለቃቸው ማን እንደሆነ ያውቁ ዘንድ ይገባቸዋል፤ እንደ አለቃቸውም ያድርጉት፣ ያለ እርሱም ምክር ማንኛውንም ትልቁንም ትንሹንም ሥራ አይሥሩ፤ ዳግመኛም እርሱ /ሊቀ ጳጳሱ/ ያለ ኤጴስ ቆጶሳቱ ሁሉ ምክር ትልልቁን ሥራ አይሥሩ፤ እንደዚሁ በአንድ ኅብረት ይሁኑ፡፡” /ኒቅያ 49፤ ትእዛዝ 25/ ጳጳሳቱ የበላያቸውን ማክበርና ኃላፊነታቸውን አስመልክቶ የሐዋርያት አብጥሊስ 33 እንዲህ ይላል፡፡ “ኤጲስ ቆጶሱ ሊያደርግ የሚገባውን ያውቅ ዘንድ ይገባዋል፡፡ ራሱን ሥነሥርዓት ያለው ያደርግ ዘንድ ታዞአልና፤ ከእርሱ በላይ ያለውን የሊቀ ጳጳሱንም ክብር የሚያውቅ ይሆን ዘንድ ይገባዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ኤጴስ ቆጶሳቱን ማክበር ይገባዋል፡፡” /አብጥሊስ 33/

ሊቃነ ጳጳሳት በቀሳውስት፣ በዲያቆናትና በሕዝብ ሊፈጽሙት ስለሚገባ ቅን አስተዳደር አስመልክቶ ረስጦአ 53 ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ቆጶሱ በቀሳውስትና በዲያቆናት ላይ አይታበይ፣ ቀሳውስትም እንዲሁ በሕዝቡ ላይ አይታበዩ፡፡ /ተስጦአ 53/

ሊቃነ ጳጳሳት በቀሳውስት፣ በዲያቆናትና በሕዝብ ሊፈጽሙት ስለሚገባ ቅን አስተዳደር አስመልክቶ ረስጦአ 53 ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ ኤጴስ ቆጶሱ በቀሳውስትና በዲያቆናት ላይ አይታበይም፣ ቀሳውስትም እንዲሁ በሕዝብ ላይ አይታብዩ፡፡ /ተስጦእ.53/ ኤጲስ ቆጶሱ ከካህናት ወገን የተቸገሩትን ቸል ቢል የሚያስፈልጋቸቸውንም ባይሰጣቸው በቸልተኛነትም ቢኖር ይሻር፡፡ /ትእዛዝ 39/

 የቤተክርስቲያን መሪዎችም በተሰጣቸው ሥልጣን ከሚሠሩ በቀር ያልተሰጣቸውን ሌላ ሥልጣን በመፈለግ እግዚአብሔርን ማሳዘን እንደሌለባቸው የሚገልጸው ቀሌምንጦስ እንዲህ ይላል፡፡ ሁሉም እያንዳንዱ በተሰጠው መዓረግ ይጽና፤ ከእናንተ አንዱም እንኳን ያልተሰጠውን የሌለውን መዓርግ አይንጠቅ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔርን ታሳዝኑታላችሁ፡፡ /ቀሌምንጦስ ሣልስ 79/

ከዚህ በላይ የተቀመጡት የቀኖና አንቀጾች በቤተክርስቲያን የበታቹ የበላዩን ማክበርና እንደሥርዐቱ መታዘዝ፣ የበላዩም መሥራትና ማሠራት፣ የሥራ ጉድለት ሲኖረው መርምሮ ማስተካከል፣ በበላይና በበታች መካከል ያለው የሥረ ግንኙነት ከመታዘዝና፣ ከትሕትና ጋር የበላይ የበታቾቹን እንደ ልጆቹ፣ የበታቾቹም የበላያቸውን እንደ አባት እንዲመለከቱ፣ የሁሉም ዋናው የኃላፊነት ተግባር የእግዚአብሔርን መንጋ በታማኝነት መጠበቅና ማብዛት መሆኑን የሚያስፈዱ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያን እስከ ቅርብ ጊዜ በዚህ ሕግና ሥርዐት ስትሠራ የኖረች ብትሆንም ዛሬ ግን በተለይም በአሁን ጊዜ ሥራ ላይ ያለውን ሕገ ቤተክርስቲያነችን በዚህ በነባሩ ሕግ መንፈስ ተቃኝታ ብትመራ በመንሳዊውም ሆነ በማኅበራዊው የአስተዳደር ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ ሆና እንደምትቀጥል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

በቤተክርስቲያን ነባሩና ከሐዋርያት ጀምሮ ሲያያዝ የመጣው ቀኖና እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በተጨማሪ ለቤተክርስቲያን ሊጠቅም የሚችልና ጊዜውን ያገናዘበ ደምብና ሕግ እየተጠናና እየጸደቀ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግም የተፈቀደ እንጂ የተከለከለ አይደለም፡፡

በተለይም በአሁኑ ጊዜ ብዙ ቀልጣፋና ጥራት ያላቸውን፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያጠናክሩ የአስተዳደርና የአሠራር ዘዴዎች እየተፈጠሩ የመጡበት ዘመን እንደመሆኑ መጠን እንደዚህ ዓይነቱ የአስተዳደር ዘዴ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲኖር የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍና የብዙኃኑ አስተያየትም ጭምር በማስተናገድ ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን አማንያንን ያሳተፈ አሠራር እጅግ በጣም ተወዳጅ እንደሆነ በቅዱሳን መጽሐፍትና በቀኖና መጻሕፍት የተመዘገበ ነውና፤ በተለይም በቅዱሳን ሐዋርያት ዘመን በቅዱስ እስጢፋኖስ እልቅና የተሾሙ ሰባቱ የመጀመሪያዎቹ ዲያቆናት በመላው ሕዝብ ተሳትፎና መራጭነት የተከናወነ ነበር፤ የኒቅያው ጉባኤም ብዙ ሊቃውንትንና ዲያቆናትን ያሳተፈ እንደነበረ ታሪክ ምስክር ነው፤ በዚህም አሠራር ሕዝቡ በጣም መደሰቱ ተጽፎአል፤ የሐዋ.ሥራ. 6÷1-6 

በቀኖና ቤተክርስቲያንም ከዲያቆን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው መዓረግ ያለው የክህነት ሥልጣን በምእመናን ምስክርነትና ምርጫ ሊሾም እንደሚገባ ተደንግጎአል፡፡ ይህ ቀኖና ቤተክርስቲያንን እያመሳት ይገኛል፤ ይህንንም የማስተካከል ኃላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ነውና ጊዜ ሳይወስድና ሥርዓት አልበኝነት ሳይበዛ በጥብቅ ሊያስብበትና ሊያርመው ይገባል፡፡

በሌላ በኩል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር በቤተክርቲያን አስተዳደር ውስጥ ማስፈን መጽሐፍ የተቀመጠ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በዚ ትኩረትን ባለማግኘቱ ችግሮች ሲከሰቱ ይታያ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያንና ሚስቱን የቀጣበት ምክንያት ተቀጪዎቹ ግልጽነትና ተጠያቂነት የጎደለበትን አሠራር በመሥራታቸው እንደነበር በግልጽ ተቀምጦአል፤ የሐ.ሥራ. 5÷1-11 ቤተክርስቲያን የእዝ ሰንሰለትንና የሕግ የበላይነት ጠብቆና አክብሮ መሥራትንም በሚገባ ልታጠናክር ይገባል፤ ዲያቆኑ ለቄሱ፤ ቄሱ ለኢጲስ ቆጶሱ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ለሊቀ ኤጲስ ቆጶሱ ለቅዱስ ፓትርያርኩ የመታዘዝና የበላዩን ማክበር በቀኖና ቤተክርስቲያን በአግባቡ ሊከበር ይገባል፡፡

በመንፈሳዊ አባት ይቅርና በሥጋዊ አባት ላይ የስድብን ቃል የሚናገር በሞት ይቀጣ የሚል ጠንካራና አምላካዊ ሕግ ያላት ቤተ ክርስቲያን ይህ ሕጓ ተጥሶና እንደሌለ ተቆጥሮ ወደላይ አሻቅቦ መንፈሳዊ አባትን ለመዝለፍ የሚደረገው ሙከራ እጅግ አሳዛኝ በመሆኑ ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል፤ ማቴ. 15÷3-6 ፡፡ ቤተክርስቲያናችን ጥንታዊትና የብዙ ዕውቀት ባለቤት እንደመሆኗ የሕግ፣ የቀኖናም ሆነ የአስተዳደር መጻሕፍቱን ተምሮ ዕውቀቱን በመቅሰም ቤተክርስቲያንን ዘመኑ ከሚጠይቀው የተጠያቂነትና የግልጽነት አሠራር ጋር አዋሕዶና አስማምቶ በአግባቡ ለመሥራት ፍላጎቱም ሆነ ተነሣሽነቱ ባለመኖሩ ነው፡፡

ከቀኖና ጋር ቤተ ክርስቲያን ሳይዛመዱና መጻሕፍቱን ሳይረዱ በኢንተርኔትና በጋዜጣ የሚጎርፉትን ብቻ በመመልከት እነርሱም አፍሰን ቤተ ክርስቲያን ላይ እንጨምራቸው የሚለው አመለካከት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የቤተክርስቲያን የአስተዳደር ሥርዓትና ሕግ መመንጨት ያለበት ከቅዱሳን መጻሕፍትና ከቀኖና ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ነው፤ ይህ የሆነ እንደሆነ ቤተክርስቲያን የጥንቱ ሳይጎድልባት የዘመኑን የአሠራር ዘዴ በመጠቀም ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሚበጅ ሥራ መሥራት ትችላለች፡፡
ክብሩ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን አሜን!

Post Bottom Ad