በልደት ዋዜማ የፍቅር ማዕድ በጎንደር ቀሃ ኢየሱስ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, January 8, 2014

በልደት ዋዜማ የፍቅር ማዕድ በጎንደር ቀሃ ኢየሱስ

ታኅሣሥ 26 እና 27/2006ዓ.ም.በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥንታዊውና ታሪካዊው ቀሃ ደብረ ስብሐት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እጅግ በጣም  ሚያስደስት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሒዶ ነበር፡፡ ከዓርብ ጀምሮ እኔና ዘማሪ በኃይሉ ተበጀ ከአዲስ አበባ


 አባ ማትያስ የተባሉ መምህር ደግሞ ከባሕር ዳር ተገኝተን ነበር፡፡ የዚህ ጉባዔ ባለቤት በማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማዕከል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች ሲሆኑ የጉባዔው ዓላማም የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ተማሪዎቹ ከአጥቢያው ምዕመናን፣ከአጥቢያው ካህናትና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ጋር በኅብረት ቃለ እግዚአብሔርን  ይመገቡ ዘንድ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡የፍቅር ማዕድ ማለት ነው፡፡ከዚህ ጉባኤ አንድ ሳምንት በፊት በጎንደር ከተማ የተካሔደው የአኮቴት ተዋሕዶ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የገና በዓል ቀረጻና የወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አራቱ ኃያላን መጽሐፍ የምርቃት ዝግጅት ሕዝቡን ለመቀስቀስና ይህንን ጉባዔ ለማስተዋወቅ እንደጠቀማቸው ተማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዚያ መገኘቱና


 ከመጣበት መርሐ ግብር አንጻር ሰፊ ጊዜ ባይኖረውም ባለችው ጠባብ ጊዜ ረፍት ሳይሻ የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት በማስቀደም ተማሪዉቹ ካሉበት ቦታ እየተገኘ በማስተማርና በማወያየት ባስጨበጣቸው መንፈሳዊ ዕውቀት በእጅጉ መርካታቸውንና መደሰታቸውን ጨምረው ገልጸውልኛል፡፡ እኔም ከፊታቸው ላይ ሳነበው የነበረው ይህንኑ የደስታ መንፈስ ነበር፡ይህ ደግሞ ጎንደር ላይ እንደ እባብ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎኩ የተሐድሶ መርዛቸውን ለሚረጩት አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ከባድ ራስ ምታት ነው፡፡

የግቢ ተማሪዎቹ  ለአገልግሎቱ ያላቸው መንፈሳዊ ቅናትና ትጋት በጣም የሚገርም ነው፡፡ በተለይም ሁለት ነገር አስገርሞኛል አስደንቆኛልም፡፡ የመጀመሪያው ለታላላቆቻቸው ማለትም ለማዕከሉ አባላት ያላቸው  አክብሮትና ዕምነት ነው፡፡"እኛ ጉባዔ አዘጋጅተን አናውቅም እንግዶቻችንን ልናጉላላ ስለምንችል እናንተ በጥሩ ሁኔታ አስተናግዱልን" ብለው ሓላፊነቱን ከበቂ ገንዘብ ጋረ ማስረከባቸው የዚሁ አክብሮትና እምነት ውጤት ነው፡፡ ይህ ደግሞ መምህር ከመጣላችወ በኋላ ስለሚያስተምራቸው ትምህርት ብቻ እንጂ መምህሩ ሰው እንደመሆኑ መጠን ስለሚያርፍበትና ሌሎች  ትምህርት ስለሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች ግድ ለማይሰጣቸው አንዳንድ ግቢ ጉባዔያት ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ሁለተኛው ያስደነቀኝ የሰዓት አጠቃቀማቸው ነው ተማሪው በተቀጠረበት ሰዓት ተገኝቶ በታሰበው ሰዓት ይለቀቅ ነበር፡፡ባጠቃላይ ጉባዔው እጅግ መጣም አስደሳችና ማራኪ ነበር፡፡ ውድ አንባቢዎቼ ሌሎች ይማሩበት ዘንድ ሼር በማድረግና ክቡር አስተያየታችሁን በማስፈር ተሳተፉ፡፡የተለመደው የፎቶ ግብዣ እነሆ፡፡

ምንጭ፦ ምትኩ አበራ


ጉባዔው የተዘጋጀበት ቤተ ክርስቲያን ከውጭ ሲታይ
ጉባዔው የተዘጋጀበት ቤተ ክርስቲያን ከውጭ ሲታይ

የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች
የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች

የሰንበት ጸዲቀ መበለት ዳቤ ከቅዳሴ በኋላ ብቻ የሚገኝ
የሰንበት ጸዲቀ መበለት ዳቤ ከቅዳሴ በኋላ ብቻ የሚገኝ

ዘማሪ በኃይሉ
ዘማሪ በኃይሉ

የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች
የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች

ዘማሪ በኃይሉ
ዘማሪ በኃይሉ

የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች
የፍቅር ማዕዱ ተሳታፊዎች

ታሪክ ሠሪው በታሪካዊቷ ከተማ ሲታሰብ
ታሪክ ሠሪው በታሪካዊቷ ከተማ ሲታሰብ


ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት  አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ
ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ

ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት  አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ
ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ

ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት  አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ
ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ

ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት  አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ
ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ

ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት  አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ
ታሪክና ዕድሜ ጠገብ ከሆኑት አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ

ጎንደር ልደታ በ1717ዓ.ም. በአፄ ዮስጦስ ተሰርታ በ1882ዓ.ም.በደርቡሽ ወረራ ፈርሳ በምዕመናን ከ1938-1939 በድጋሚ የታነጸች ከነፍርስራሿ
ጎንደር ልደታ በ1717ዓ.ም. በአፄ ዮስጦስ ተሰርታ በ1882ዓ.ም.በደርቡሽ ወረራ ፈርሳ በምዕመናን ከ1938-1939 በድጋሚ የታነጸች ከነፍርስራሿ

መ/ር አባ ማትያስ ከባሕር ዳር
መ/ር አባ ማትያስ ከባሕር ዳር

የደብሩ ሰ/ት/ቤት መዘምራን የጉባዔው ተሳታፊዎች ነበሩ
የደብሩ ሰ/ት/ቤት መዘምራን የጉባዔው ተሳታፊዎች ነበሩ

Post Bottom Ad