የደብረሃይማኖት መካነ ኢየሱስቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ስቴ ወረዳ የሚገኝ ነው። በዐጼ አድያም ሰገድኡያሱ ዘመነ መንግሥትየተተከለዉ ጥንታዊዉና ታሪካዊዉ ደብረ ሃማኖት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በሦስት ታላላቅጉባኤያቱ የታወቀ ነበር፡፡
1. በብሉይና ሐዲስ ትርጓሜ ቤተ ጉባኤ
2. በቅኔ ቤተ ጉባኤ
3. በድጓ ቤተ ጉባኤ
በሦስቱም አብያተ ጉባኤያት ታላላቅ ሊቃዉንትን ለሀገሪቱም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱሲያበረክት የቆየዉ ይህ ታሪካዊ ቦታ እስከ 1950ዎቹ ሦስቱም ጉባኤያት የነበሩት ቢሆንምበአሁኑ ጊዜ ግን የቅኔ ጉባኤ ቤቱ ታጥፎ የትርጓሜ መጻሕፍቱና የድጓ ጉባኤዎቹ ግን አሁንምሳይታጎሉ የሚሰጥበት ቦታ ነዉ፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ በንግሥተ ንግሥታት ዘዉዲቱ ዘመን በጥሩ ሁኔታ በዘመናዊ መንገድተሠርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያዉኑ ጠላት (ጣልያን) ወደ ሀገራችን በመግባቱ ምክንያት ቤተክርስቲያኑ ተቃጠለ፤ በቦታዉ የነበሩት ታላላቅ ሊቃዉንትም ሰማዕትነት ተቀበሉ፡፡
ከጣሊያን ወረራ በኋላ እንደገና በቦታዉ ላይ የትርጓሜ መምህር በነበሩትና በኋላከመጀመሪያዎቹ ጳጳሳት አንዱ በነበሩት የጥንቱ አቡነ ሚካኤል ( የቅዳሴ ትርጓሜን አዘጋጅተዉያሳተሙት) አሳሳቢነትና አስተባባሪነትም ጭምር በንጉሡ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ፈቃድ እንደገናአሁን በሚታየዉ መልኩ ተሠርቶ በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠናቀቀ፡፡
ይህ አሁን ያለዉ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ መሠረቱ ሲጣል ራሳቸዉ ንጉሠ ነገሥቱእቦታዉ ድረስ የሄዱ ሲሆን በጊዜዉ በቦታዉ ላይ ቅኔዉንና ትርጓሜ መጻሕፍቱን አንድ ላይአድርገዉ ያስተምሩ የነበሩት እጅግ ስመ ጥር የነበሩት የኔታ ኃይለ ጊዮርጊስ የነበሩበት ዘመንነበር፡፡ በዚህ ወቅት በድጓ ቤት ያሉትን ሳይጨምር ከ450 በላይ የቅኔና የትርጓሜ መጻሕፍትተማሪዎች የነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡
![]() |
በጊዜዉ የግብጽ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሳብ ካልዓይ |
ይህ አሁንያለዉ ቤተክርስቲያን ተፈጽሞበሚመረቅበት ጊዜደግሞ ንጉሠ ነገሥቱባይገኙም በጊዜዉየግብጽ ፓትርያርክየነበሩት ብፁዕወቅዱስ አቡነ ዮሳብካልዓይ፣ የኋላዉፓትርያርክ የዚያንጊዜዉ ጳጳስ አቡነቴዎፍሎስና ታላቁአቡነ ዮሐንስከሌሎች የጊዜዉየመንግሥት ባለሥልጣናትናሊቃዉንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተገኝተዋል፡፡
በወቅቱ በቦታዉ በመማር ላይ የነበሩት ብዙዎቹ በወቅቱ የነበረዉን ርቃቄናመንፈሳዊነት የሠለጠነበትን ፍልስፍናዊ የትምህርት ጊዜ በማስታወስ ጊዜዉን ደብረ ሃይማኖትካልዕት እስክንድርያ የነበረችበት ጊዜ ያደርጉታል፡፡ አንዳንዶች ግን ከዚያም በፊት ቢሆን እንዲሁእጅግ ስመ ጥር የሆኑ ሊቃዉንት የነበሩበትና መንፈሳዊ ፍልስፍና ርቃቄ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶየሚሠጥበት በመሆኑ ከጥንት እስካሁን ካልዕት እስክንድርያ ናት ይሏታል፡፡
ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ ካቶሊኮች ገብተዉ ከወጡበት የጥንቱ ጊዜ በኋላ መልኩንቀይሮ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንትን ሲያበጣብጥ የቆየዉ የቅባትና የጸጋ ሰርጎ ገብ ፈጽሞካልረገጣቸዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የትርጓሜ ትምህርት ቤቶች አንዱ ደብረ ሃይማኖት መካነኢየሱስ ነዉ፡፡
![]() |
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ 2ኛው ፓትርያርክ |
ቦታዉ ለቅርቧ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንምያበረከታቸዉ ሊቃዉንት እጅግ ብዙዎች ናቸዉ፡፡ከቀዳሚዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ከሆኑት ከብጹነ አቡነሚካኤል ጀምሮ እነ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ አቡነ ኤልያስ (አሁን ስዊድን ያሉት) የኋላዉ አቡነ ኤልያስ(የቀለም ቀንዱ)፣ ተጠቃሾች ሲሆኑ ከሊቃዉንቱም እነርዕሰ ደብር ጥዑመ ልሣን፣ መልአከ ታቦር ተሾመዘሪሁን፣ ሊቀ ሥዩማን ራደ አስረስ፣ መልአከ ሰላም መርዓዊ ተበጀ፣ … ተቆጥረዉ የማያልቁ የብሉይ፣የሐዲስ፣ የቅኔና የዜማ ሊቃዉንትን አፍርቷል፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ባለፉት ሃምሳ ዐመታትዉስጥም በቦታዉ ብሉይና ሐዲስን በማስተማር፣ የተጣሉትን ከማስታረቅ ጋር በብህትዉና በመኖር የሚታወቁት መጋቤ ሐዲስ ኃይለ ሚካኤል ብዙ ደቀመዛሙርትን በማፍራት ያገለገሉበት ሲሆን እርሳቸዉ በዕርጅና ማስተማሩን ሲያቆሙ በአሁኑጊዜ ደግሞ ሐዲሳቱን ከእርሳቸዉ ብሉያቱን ደግሞ ጎንደር ዐቢየ እግዚእ ከየንታ ፀሐይ የተማሩት የንታ ሐረገወይን ተተክተዉ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡
እግዚአብሔር በአባቶቻችን እግር የምንተካ
የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን
አሜን ፡፡
አሜን ፡፡