"ቤተ ክርስቲያን የኔነቴ" - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Tuesday, January 14, 2014

"ቤተ ክርስቲያን የኔነቴ"

የሰንበት ማዕድ

የወጣት የአዛዉንቱ የዕለት ምግብ የዕለት ልብስ ጉርስ ፆታ ሳትለይ
 አንስት ተባእት ሳትይ
መጋቢያችን ቃለ ህይወት ቃለ ሲሳይ
የአባቶች ቅርስ የህይወት ሙዳይ
     ጥንት ገና ያኔ ድሮ የዓለም ዕድሜ ትኩስ ሳለ
     የፍጥረታት ስነ ህላዌ ከቃሉ ለይኩን እንደተባለ
     ከዚያን አዎን ከዚያን ዘመን ከዚያን ወዲያ የቀጠለ
     በተረፈ የዘመን ጉዞ ብዙ ነጉደን
     ወደኃላ ብዙ ርቀን ብዙ ብዙ ጠልቀን ከንፈን
     ሁልቆ መስፍርት የሆነዉን ዓለም ዛሬ በአያሌዉ ገድፈን
    ወደኃላ በሃሳቤ የዓለምን ጉዞ አንድ እንድል እንደገና
                   በስጋ ሳይሆን በልቦና
    በአእምሮ ስነ ህላዌ ምጥቀት ህልዉ በሆነዉ ህሊና
    ተጉዤ የአምላክን ሰዉ መሆን ልደቱን
    ማስተማሩን መዉጣት መዉረድ የማዳን ክንዋኔዉን
    መገረፉን መቸንከሩን መሰቀሉን
    የሞት አበጋዝ ድል አድርጎ መነሳቱን
    ያስተማርሽኝ ቤተክርስቲያን የሰንበት ድግስ
   የወጣት አዛዉንቱ የዕለት ምግብ የዕለት ጉርስ
   የአቡነ ተክለሃይማኖት የጎርጎርዮስ የዉርስ ቅርስ
   አንቺ እኮ ነሽ ቤተክርስቲያን የኔነቴ
አድማስ ሰርጡን አቆራርጠን ሰማይ ምድሩን ላይ ታች ብለን
ቀላየ ቀላያትን ከላይ አፍልሰ አፍለሳትን አሻቅበን
ከምድር በጥልቀቱ የርዕዮተ መንገድ እመቀ እመቃት አቆልቁለን
ሁሉን በአክናፍ እንደ አዕዋፍ ሰነጣጥቀን ወደኃላ
በማካለል ጥንት ሐሳቤን በዛሬዉ በመኖር ጥላ
በመረዋ ድምፅሽ የጠራሽኝ እማምዬ እስኪ ላስተዉላ
     በጥልቀት ሁሉም ፍንትዉ ሲል
    ከፅልመት ብርሃን ሲፈነጥቅ
    የረቀቀዉ ህላዌ ዓለም ከርቀት ግዝፈቱ ሲልቅ
    አዎ እንደዚያ ያለዉ ምስጥር ወደ ገሀድ ዓለም
    ፅንሰተ ምድር በእኛ ህሊና በርቶ ሲሰለመለም
    በአንቺ ነዉና የተፈታዉ ይህ ሁሉ ህልም
    መምህርት ነሽ ቤተክርስቲያን እናት ዓለም
ለይኩን ሲል በቃሉ የተፈጠረበትን ዕለት
እስከ ሰንበት ከመነሻዉ እስከ ክንዋነዉ ማኅለቅት
አዎ እስከዚያ የዓለምን ፅንሰት ከዚያ ወዲያ በዓመተ ዓለም
ዓመተ ፍዳ እንደምንለዉ ከምህረት ዘመን ቀድሞ
አዎ እስከዚያ ብዙ ጠልቀን ወደኃላ ጥንት ህሳቤ
በአዕምሮ የፍልሰት ጎዳና ከዘመናት ጋር ሩካቤ
ብቻ እስከዚያ ሄደን የጉዞ ፍፃሜ ባይኖርም
ይኸ ከሰዎች ህሊና በላይ ያለ ከቶ ሊታሰብ ባይችልም
ባስተማርሽን የፍጥረታት ስነ ህላዌ በሄድነዉ የዘመናት ጎዳና
              በስጋ ሳይሆን በልቦና
አስረዳሽን እንደ አባቶቻችን ጉዞ
እንደ መጀመሪያዉ አሐዱ እንድንል
የማናዉቀዉን ስንቀላቅል
ልጆቼ ያለፈዉን ፍጥረት በጊዜዉ ወንጌል ሳይቀበል
ብቻ በህገ ልቦና ሳለ
ዳግም በኦሪት ቀደሚ ቃል
ለሙሴ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ
በአስርቱ ቃላት እንዲመራ
የብሉይ ዘመን ህገ ቃል ለዘመኑ ሰዉ እንዲያበራ
          አስቀድሞ ህግ ተሰራ
ልጅሽ ቀዳሚሁ ቃል እንዳለ ዮሐንስ በስነወንጌል
መጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ስጋ ሆነ እነዲል
የማያጠያይቅ ነዉና የስነ ወንጌል መነሻዉ
አስቀድሞ የነበረዉ ዛሬም ያለዉ የሚኖረዉ
ክርስቶስ የሰዉን ስጋ ለብሶ ለስቅለት እስኪበቃ
ያሸለበዉ ፍጥረት ሁሉ ከዘመነ ፅልመት እስኪነቃ
እስከ ብርሃነ ልደቱ የዓለም ጌታ እስኪገለፅ
        የሰዉ ልቦና እስኪታነፅ
አዎ ይኸ ሁሉ እንዲያልፍም እንዲያበቃ ዘመነ እስራት
ዘመነ ምህረት እንዲመጣ ተናግሮአልና በነቢያት
ያ ቃለ እግዚአብሔር እንደሆነ ታዬ ፍፃሜዉ ሲከሰት
እግዚአብሔር ከሰማይ ወረደ የሰዉን ስጋ ለበሰ
ከድንግል ማርያም ተወለደ መከራችንን አበሰ
ከዚያ ጀምሮ በዓለም ላይ የህይወት ቃል ተዘራ
የወንጌል ድልድይ ተዘረጋ በሰዎች ህሊና አበራ
በምሳሌ አፍን ከፈተ የሰማይ ምስጥርን ነገረን
ጆሮ ያለዉ ይስማ በማለት የድህነት ቃሉ አበሰራት
ዓመተ ምህረት ተጀመረ
ሐዋርያት እየዞሩ ቃለ ሕይወትን በስብከት
ሰማዕታትና ፃድቃን በስሙ የተጋደሉለት
መከራ መስቀሉን ስለዉ ተሸክመዉ ነዉና ክብር ያገኙት
              ልጄ አንተም በርታ
             እንግዲህ በቃሉ ለመንን
             ለእኛ በቃሉ እንደ ነገረን
በኦሪትም ሆነ በወንጌሉ ፀንተን ቃሉን አፅንተን ለተገኘን
ልጄ የእግዚአብሔር ክብር ለእኛም አለን
እያልሽ አሮጌ ህይወቴን ቀይረሽ ከእናት ቤተክርስቲያን ያስተዋወቅሽኝ
የኔነቴ ምንነት መገለጫዬ ቤተክርስቲያን ደስ ይበልሽ
ዉድዋ እናት ቤተክርስቲያን የሰንበት ድግስ
የወጣት የአዛዉንት የዕለት ምግብ የዕለት ልብስ ጉርስ
ፆታ ሳትለይ አንስት ተባእታይ ሳትይ
መጋቢያችን ቃለ ህይወት ቃለ ሲሳይ
የአባቶች ቅርስ የህይወት መድሃኒት ሙዳይ
ቤተክርስቲያን የእኔ ሲሳይ
             ሲደከረመኝ ማረፊያዬ ጥላዬ ከለላዬ
            ቤተክርስቲያን ጋሻ መከታዬ
            አበርቺን በፀሎት በስግደት በፆም
            ኃይል ሁኝን አማማ ልጅሽ እንዳልደክም
            የዘዉትር ተስፋ መመኪያ ህይወቴ
           የማትሰለችኝ እዉነተኛ እናቴ
           አንቺ እኮ ነሽ ዉዷ ቤቴ


ቤተክርስቲያን የኔነቴ

Post Bottom Ad