አንድ ብቻውን በበርሃ የሚኖር ባህታዊ አንድ ቀን
ወደ ቤትክርስቲያን ሄዶ በዚያ አኃው ተሰብስበው በጸሎተ ማዕድ ላይ ስላገኛቸው ከእነርሱ ጋር ለመሳተፍ አብሮ ቁጭ አለ።
ከእነዚያ አንዳንዶቹ “ይህንን ሰው የጠራው ማነው? ተነሳና ሂድ” ብለው
አባረሩት። እርሱም ተነስቶ ሄደ። ሌሎቹ ግን በሁኔታው በጣም አዘኑና ሄደው እንዲመለስ ጠሩት እርሱም እሽ ብሎ
ተመልሶ መጣ። ከመጣ በኋላ “ሂድ ተብለህ ስትባረርና ና ተብለህ ስትጠራ ምን ተሰማህ፤ ምንስ ታሰበህ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም “እኔ ሲያባርሩት እንደሚሄድና ሲጠሩት እንደሚመጣ ውሻ እንደሆኩ በልቤ እርግጠኛ ስለሆንኩስባረር ሄድኩ፤ ስጠራ መጣሁ እንጅ ሌላ ምንም ስሜት አልተሰማኝም አላቸው። አሁን ከ እኒህ አባት ምን እንማራለን። ድንገት የተባረርነው እኛ ብንሆንስ?
ምን እናደርግ ነበር?