ትሕትና - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Wednesday, January 1, 2014

ትሕትናትሕትና ምግባር ትሩፋት እየሰሩና ሕገ እግዚአብሔርን አየፈጸሙ ነገር ግን የማልጠቅምና ከሁሉ የማንስ ነኝ” ብሎ ራስን ዝቅ ማድረግ ነው።  ይኸውም ለሰው ይምሰል ብቻ በአፍ እኔ ከሁሉ አንሳለሁ ማለት ሳይሆን ይህንን በልብ ማመን ነው።  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል” ሲል ራስን ማክበር የውርደት ራስን ማዋረድ ደግሞ የክብር መሠረት መሆኑን ነገረን።  በተግባርም አምላክ ሲሆን በባሪይው እጅ በመጠመቅ፤ የደቀ መዛሙርቱን እእግር በማጠብ፤ በፍጡራኑ በመሰደብ፤ እና የመሳሰለውን የትህትና ሥራ ሰርቶ እንድንሰራ “ ከ እኔ ተማሩ” እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና” ሲል አስተምሮናል።  ማቴ 11፤29።  ትህትና ራስን መናቅና መንቀፍ እንደሆነ ሁሉ ኢዮብ “ እኔ ራሴን እንቃለሁ፤  እኔ ወራዳ ሰው ነኝ ብሏል ኢዮ 40፤4 42፤6።  እግዚአብሔርም “ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሁት መንፈሱም ወደ ተሰበረ በቃሌም ወደ ሚንቀጠቀጥ ሰው እመለክታለሁ”  ይላል ኢሳ 66፤2።  “ለጠቢቡ ግን ሞገስን ይሰጣል“ ይላል ምሳሌ 3፤34።  እንዲሁም ትህትና ወደ ድኅነት የሚመራ መንገድ ነው። “ትሁቱንም ሰው ያድነዋል ኢዮ 22፤9 ።  ትኅትናና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት፤ ክብር ሕይወትም ነው” እንዲል ምሳ 22፤4 ። ቅዱሳን አባቶቻችን ራሳቸውን ባዋረዱና በናቁ መጠን ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ አክብሮአቸዋል።  መጥምቁ ዮሐንስ “እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ ከማይገባኝ “ እያለ ራሱን ያዋርድ ነበር።  በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ለ እኛ ሲል በዮርዳኖስ ሲጠመቅ፤  በእርሱ እጅ በመጠመቅ ዮሐንስን ለማንም ያልተሰጠ ጸጋ “መጥምቀ መለኮት” እንዲባል አድርጎታል። ማቴ 3፤11። ዮሐ 1፤26

ይቆየን.......

Post Bottom Ad