አባ ቴዎድሮስ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Friday, December 20, 2013

አባ ቴዎድሮስ

(በዲያቆን ንጋቱ አበበ)

በእስክንድርያ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ በንጽሕና እና በቅድስና በመልካም መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ከሚኖሩ ታላላቅ አባቶች አንዱ ነው:: አባ ቴዎድሮስ የታመኑና የተቀደሱ አባት ናቸው:: ታናሹ አርዮሳዊ ቆስጠንጢኖስ በነገሰ ጊዜ አርዮሳዊ ጊዮርጊስን በ እስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አድርጎ ሾመው:: ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስንም ከመንበሩ አሳደደ
ው:: ይህ አርዮሳዊ ጊዮርጊስም በማርቆስ ወንበር ላይ ሲቀመጥያን ጊዜ በአርዮሳውያንና በአስክንድርያ ምአመናን መካከል ታላቅ መተላለቅ ሆነ ሃይማኖታቸው የቀና ብዙዎች ምአመናንም ክብር ይግባዉና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተገደሉ:: ከዚህ በኃላም ይህ አርዮሳዊ ጊዮርጊስ ስለ አባ ቴዎድሮስ አርሱ አርዮሳውያንን ተከራክሮ አንደምአሸንፋቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ማስረጃ በማምጣትና በማስፈረድ ያሳፍራቸው ነበር ያን ጊዜይህን መነኮስ አባ ቴዎድሮስን ይዘው በየአይነቱ በሆነ ስቃይ አንዲያሰቃዩት አዘዘ አንዲሁም አደረጉበት ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም:: ከዚህ በኃላም ኃይለኞች ሯጮች በሆኑ ፈረሶች ላይ አግሮቹንና አጆቹን አስረው በሰፊ ሜዳ ዉስጥ አንድያስሮጧቸው አዘዘ ይህንንም በአደረጉ ጊዜ ህዋሳቱ ሁሉ ተበጣጠሱ ራሱም ተቆረጠች አንደዚህም ሆኖ ነፍሱን በአግዚአብሔር አጅ ሰጠ:: ሶስቱ አቅልላትንም ተቀዳጀ አንዱ ድንግልኛውን ጠብቆ ስለ መመንኮሱ ሁለተኛው ሃይማኖትን ስለማስተማሩና ተከራክሮ መናፍቃንን ስለመመለሱ ሦስተኛዉም ስለ ቀናች ሃይማኖት ደሙን በማፍሰሱ ነው:: ከዚህም በኃላ ምአመናን የተቆራረጡና የተበተኑ ሕዋሳቱን ሰብስበው በሣጥን ዉስጥ አደረጉአቸው በዚች አለትም መታሰቢያ በአሉን አደረጉ አንዴ ሌሎቹ ቅዱሳን ሁሉ የምስጋና ድርሰትን በሮማይስጥ ፊደል ደረሱለት በጸሎት መሻፋቸውም ውስጥ ጻፉት:: 

ለአግዝአብህአር ምስጋና ይሁን አኛንም በዚህ ሰማአት ጸሎት ይማረን 

በረከቱም ከአኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን::

Post Bottom Ad